1
ትንቢተ ኤርምያስ 23:24
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
ሰው በስውር ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል እግዚአብሔር።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ኤርምያስ 23:5-6
እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እርሱም እንደ ንጉሥ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል። በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ የሚጠራበትም ስም፦ እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው።
3
ትንቢተ ኤርምያስ 23:1
የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር።
4
ትንቢተ ኤርምያስ 23:3-4
የመንጋዬም ቅሬታ ካባረርኋቸው ምድር ሁሉ ወደ በረታቸው ሰብሰቤ እመልሳቸዋለሁ፥ እነርሱም ያፈራሉ ይበዙማል። የሚጠብቋቸውን እረኞች አስነሣላቸዋለሁ፥ ዳግመኛም አይፈሩምና አይደነግጡም፥ ከእነርሱም አንድ አይጐድልም፥ ይላል እግዚአብሔር።
5
ትንቢተ ኤርምያስ 23:16
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ትንቢት የሚናገሩላችሁን የነቢያትን ቃል አትሰሙ፥ ከንቱነትን ያስተምሩአችኋል፥ ከእግዚአብሔር አፍ ሳይሆን ከገዛ ልባቸው የወጣውን ራእይ ይናገራሉ።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች