2 የጴጥሮስ መልእክት 1
1
1የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፥ ከአምላካችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው ጽድቅ አማካይነት እኛ እንዳገኘነው እምነት ያለ የከበረ እምነት ላገኛችሁት፤
2እግዚአብሔርንና ጌታችንን ኢየሱስን በማወቅ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
የእግዚአብሔር ጥሪና ምርጫ
3በክብሩና በደግነቱ የጠራንን እርሱን በማወቃችን መለኮታዊ ኀይሉ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለማምለክ የሚያስፈልገንን ሁሉ ሰጥቶናል። 4በክብሩና በቸርነቱ ክቡር ዋጋ ያለውንና እጅግ ታላቅ የሆነውን ተስፋውን አግኝተናል፤ በእነዚህም አማካይነት እናንተ በክፉ ምኞት ምክንያት በዚህ ዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ የመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች ሆናችኋል። 5በዚህ ምክንያት የሚከተሉት ነገሮች እንዲጨመሩላችሁ ትጉ፦ በእምነት ላይ ደግነትን፥ በደግነት ላይ ዕውቀትን፥ 6በዕውቀት ላይ ራስ መቈጣጠርን፥ በራስ መቈጣጠር ላይ በትዕግሥት መጽናትን፥ በትዕግሥት በመጽናት ላይ እግዚአብሔርን ማምለክን፥ 7እግዚአብሔርን በማምለክ ላይ የወንድማማችነት መዋደድን፥ በወንድማማችነት መዋደድ ላይ ፍቅርን ጨምሩ። 8እነዚህ ነገሮች በብዛት ቢኖሩአችሁ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለማወቅ የማትጠቅሙ ፍሬቢሶች እንዳትሆኑ ይጠብቁአችኋል። 9እነዚህ ነገሮች የሌሉት ግን የሩቁን ነገር ማየት የማይችል ዕውር ነው፤ ካለፉት ኃጢአቶቹም መንጻቱን ረስቶአል።
10ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ለማረጋገጥ በይበልጥ የምትጓጉ ሁኑ፤ ይህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም። 11በዚህ ዐይነት ዘለዓለማዊት ወደሆነችው ወደ ጌታችንና ወደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት ለመግባት ሙሉ መብት ይሰጣችኋል።
12እነዚህን ነገሮች ብታውቁአቸውና በያዛችሁት እውነት ጸንታችሁ ብትኖሩም እንኳ እነርሱን ለእናንተ ከማሳሰብ ቸል አልልም። 13በዚህ ሕይወት እስካለሁበት ጊዜ ድረስ እናንተን ዘወትር ማነቃቃት ትክክል መስሎ ይታየኛል። 14ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ገለጠልኝ በቶሎ ከዚህ ዓለም በሞት እንደምለይ ዐውቃለሁ። 15እኔ አሁን የምተጋው በሞት ከተለየኋችሁ በኋላ እንኳ እነዚህን ነገሮች ዘወትር ማስታወስ እንድትችሉ ነው።
ስለ ክርስቶስ ክብር የዐይን ምስክሮች
16ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኀይልና ስለ ዳግመኛ መምጣቱም በነገርናችሁ ጊዜ ራሳችን ግርማውን በዐይናችን አይተን የምንመሰክር እንጂ በሰው ተንኰል የታቀደውን ተረት ተከትለን አይደለም። 17“በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው!” የሚል ድምፅ ከታላቁ ክብር በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ገናናነትን ተቀብሎአል። 18ከእርሱ ጋር በተቀደሰው ተራራ ላይ በነበርንበት ጊዜ ይህን ከሰማይ የመጣውን ድምፅ እኛ ራሳችን ሰምተናል። #ማቴ. 17፥1-5፤ ማር. 9፥2-7፤ ሉቃ. 9፥28-35።
19ይህ ሁሉ ነቢያት የተናገሩት እውነት መሆኑን በበለጠ ያረጋግጡልናል፤ ስለዚህ በጨለማ ቦታ ለሚገኝ መብራት ትኲረት እንደምትሰጡ ነቢያት ለተናገሩት ትኲረት ስጡት፤ ይህንንም የምታደርጉት ጎሕ እስኪቀድና አጥቢያ ኮከብ በልባችሁ እስኪገለጥ ድረስ ነው። 20ከሁሉ በፊት ማስተዋል የሚገባችሁ በቅዱስ መጽሐፍ የሚገኘውን ማንኛውንም ትንቢት ማንም ሰው በራሱ ግላዊ አስተሳሰብ ሊተረጒመው የማይችል መሆኑን ነው። 21ማንኛውም ትንቢት በሰው ፈቃድ ከቶ አልመጣም፤ ነገር ግን ትንቢት በመንፈስ ቅዱስ የተመሩ ሰዎች ከእግዚአብሔር ተቀብለው የተናገሩት ነው።
Currently Selected:
2 የጴጥሮስ መልእክት 1: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997