2 የጴጥሮስ መልእክት 2
2
ሐሰተኞች መምህራን
1ነገር ግን በቀድሞ ዘመን በሕዝቡ መካከል ሐሰተኞች ነቢያት እንደ ነበሩ፥ እንዲሁም በእናንተ መካከል ሐሰተኞች መምህራን ይኖራሉ፤ እነርሱ ጥፋትን የሚያስከትል ሐሰተኛ ትምህርት በስውር እንዲሠራጭ ያደርጋሉ፤ የዋጃቸውንም ጌታ ክደው ፈጣን ጥፋትን በራሳቸው ላይ ያመጣሉ። 2በዚህ ዐይነት ብዙዎች የእነርሱን አሳፋሪ መንገድ ይከተላሉ፤ ከእነርሱም አድራጎት የተነሣ የእውነት መንገድ ይሰደባል። 3እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ ራሳቸው ያዘጋጁትን ታሪክ እያወሩ ይበዘብዙአችኋል። ከብዙ ዘመን በፊት ጀምሮ ፍርድ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ ጥፋትም በእርግጥ ይጠብቃቸዋል!
4መላእክትን እንኳ ኃጢአት በሠሩ ጊዜ እግዚአብሔር ሳይራራላቸው በጨለመ ጥልቅ ጒድጓድ ውስጥ ሆነው የፍርድን ቀን እንዲጠባበቁ ወደ ገሃነም ጣላቸው፤ 5እንዲሁም የጽድቅ ሰባኪ የነበረውን ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር አድኖ እግዚአብሔርን የማያመልኩ ሰዎች በነበሩበት ዓለም ላይ የጥፋትን ውሃ ሲያመጣ ራርቶ የቀድሞውን ዓለም አልማረውም፤ #ዘፍ. 6፥1—7፥24። 6ደግሞም እግዚአብሔርን ለማያመልኩ ሁሉ የመቀጣጫ ምሳሌ እንዲሆኑ የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ዐመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎ እንዲጠፉ ፈረደባቸው፤ #ዘፍ. 19፥24። 7በሕገ ወጦች አሳፋሪ ድርጊት እየተሠቀቀ ይኖር የነበረውን ጻድቁን ሎጥን ግን አዳነው፤ #ዘፍ. 19፥1-16። 8ያም ጻድቅ ሰው በመካከላቸው ሲኖር በየቀኑ ያየውና ይሰማው በነበረው ሕገ ወጥ ድርጊታቸው ጻድቅ ነፍሱ ትጨነቅ ነበር። 9እንግዲህ ይህ ሁሉ እንዲህ ከሆነ ጌታ እርሱን በማምለክ የሚኖሩትን ሰዎች ከፈተና እንደሚያድናቸው፥ ኃጢአተኞችንም እንዴት እንደሚቀጣና ለፍርድ ቀንም እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል ማለት ነው። 10በተለይም እነዚያን ርኩስ የሆነውን የሥጋ ፍትወታቸውን የሚከተሉትንና የእግዚአብሔርን ሥልጣን የሚንቁትን ለፍርድ ጠብቆ ያቈያቸዋል።
እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ደፋሮችና ትዕቢተኞች ስለ ሆኑ የሰማይ ሥልጣናትን ሲሳደቡ አይፈሩም። 11መላእክት ከእነርሱ በኀይልና በሥልጣን የሚበልጡ ቢሆኑም እንኳ በጌታ ፊት በእነርሱ ላይ ዘለፋን የተመላ ክስ አያቀርቡባቸውም። 12እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ግን ለማስተዋል ያቃታቸውን ነገር ይሳደባሉ፤ እነርሱ ለመጠመድና ለመገደል እንደ ተወለዱ፥ በተፈጥሮ ስሜት እንደሚኖሩና አእምሮ እንደሌላቸው እንስሶች ናቸው፤ እንስሶች እንደሚጠፉ እነርሱም ፈጽመው ይጠፋሉ። 13በደል ስለ ፈጸሙ ዋጋቸውን ይቀበላሉ፤ የእነርሱ ደስታ በጠራራ ፀሐይ መስከርና ያለ ቅጥ መፈንጠዝ ነው፤ በዚህ ቅጥ ባጣ ፈንጠዝያቸው ከእናንተ ጋር በሚጋበዙበት ጊዜ አታላይ በሆነው ሥጋዊ ድርጊታቸው ነውረኞችና አሳፋሪዎች ናቸው። 14ኃጢአት ከማድረግ የማይቈጠብ ቅንዝረኛ ዐይን አላቸው፤ የኃጢአት መሥራት ፍላጎታቸው መቼም አይረካም፤ በእምነት ጸንተው ያልቆሙትን ሰዎች ያታልላሉ፤ ለገንዘብ ይስገበገባሉ። የተረገሙ ሰዎች ናቸው። 15እነርሱ የቀናውን መንገድ ትተው ጠፍተዋል፤ ክፉ በመሥራት የሚገኘውን ገንዘብ የወደደውን የቢዖርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከትለው ተሳስተዋል። 16በለዓም ግን ስለ ኃጢአቱ ተገሥጾአል፤ መናገር የማትችል አህያ በሰው ቃል ተናግራ የነቢዩን የእብደት ሥራ ተቃውማለች። #ዘኍ. 22፥4-35።
17እነዚህ ሰዎች ውሃ እንደሌለባቸው ምንጮች ናቸው፤ በዐውሎ ነፋስ እንደሚወሰዱ ደመናዎች ናቸው፤ ድቅድቅ ጨለማም ይጠብቃቸዋል። 18በስሕተት ከሚኖሩት ሰዎች መካከል አምልጠው ከመጡ ገና ብዙ ያልቈዩትን ሰዎች ከንቱ የሆነ የዕብሪት ቃል በመናገር፥ በሥጋዊ ፍትወትና በሴሰኛነት በማባበል ያታልሉአቸዋል። 19“ነጻ ትወጣላችሁ” እያሉ ተስፋ ይሰጡአቸዋል። ሰው ሲሸነፍ ላሸናፊው ባሪያ ሆኖ ስለሚገዛ እነርሱም ራሳቸው የኃጢአት ባሪያዎች ናቸው። 20ጌታችንንና አዳኛችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ ከዓለም ርኲሰት ካመለጡ በኋላ ተመልሰው በዚያው ርኲሰት ተይዘው ቢሸነፉ ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ሁኔታቸው የባሰ ይሆንባቸዋል፤ 21የጽድቅን መንገድ ካወቁ በኋላ ከተሰጣቸው ቅዱስ ትእዛዝ ወደ ኋላ ከሚመለሱ ይልቅ የጽድቅን መንገድ ሳያውቁ ቀርተው ቢሆን ኖሮ በተሻላቸው ነበር። 22“የተፋውን ለመዋጥ ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል።” እንዲሁም “ዐሣማ ከታጠበ በኋላ ተመልሶ በጭቃ ላይ ይንከባለላል” የሚለው እውነተኛ ምሳሌ ደርሶባቸዋል። #ምሳ. 26፥11።
Currently Selected:
2 የጴጥሮስ መልእክት 2: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997