ኦሪት ዘጸአት 11
11
በ. ሙሴ የግብጻውያን የበኲር ልጆች እንደሚሞቱ አስታወቀ
1ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በግብጽ ንጉሥና በሕዝቡም ሁሉ ላይ ሌላ መቅሠፍት እልካለሁ፤ ከዚያም በኋላ ከዚህች ምድር እንድትወጡ ይለቃችኋል፤ እንዲያውም አንድ ሳይቀር ሁላችሁንም ያባርራችኋል። 2አሁንም የእስራኤል ሕዝብ ወንዶቹም ሴቶቹም ጐረቤቶቻቸውን ሁሉ የወርቅና የብር ጌጣጌጥ እንዲሰጡአቸው ይጠይቁ ዘንድ ንገራቸው።” 3እግዚአብሔርም እስራኤላውያን በግብጻውያን ዘንድ ሞገስ እንዲያገኙ አደረገ፤ በእርግጥም የንጉሡ ባለሟሎችና ሕዝቡ ሁሉ ሙሴን በግብጽ ምድር ታላቅ ሰው አድርገው ተመለከቱት።
4ሙሴም ንጉሡን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘በእኩለ ሌሊት በግብጽ ምድር እዘዋወራለሁ፤ 5የዙፋኑ ወራሽ ከሆነው ከንጉሡ ልጅ ጀምሮ እህል በመፍጨት ከምታገለግል ድኻ ሴት እስከ ተወለደው ልጅ ድረስ በግብጽ ምድር በኲር የሆነ ወንድ ልጅ ሁሉ ይሞታል፤ እንዲሁም የእንስሶች በኲር ሁሉ ይሞታል። 6በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ከዚህ በፊት ያልነበረ ወደ ፊትም የማይኖር ታላቅ ለቅሶ ይሆናል። 7ነገር ግን በእስራኤላውያንም ሆነ በእንስሶቻቸው ላይ ውሻ እንኳ አይጮኽባቸውም፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር በግብጻውያንና በእስራኤላውያን መካከል ልዩነት የማደርግ መሆኔን ታውቃላችሁ።’ ” 8ሙሴም “መኳንንትህ ሁሉ ወደ እኔ መጥተው እጅ ይነሡኛል፤ ሕዝቤንም ይዤ እንድወጣ ይለምኑኛል፤ ከዚያም በኋላ እሄዳለሁ” በማለት ንግግሩን አበቃ፤ ይህንንም ከተናገረ በኋላ በታላቅ ቊጣ ከንጉሡ ፊት ወጥቶ ሄደ።
9እግዚአብሔር ሙሴን “በግብጽ ምድር ላይ ብዙ ተአምራት አደርግ ዘንድ ንጉሡ እናንተን አይሰማም” ብሎት ነበር፤ 10ሙሴና አሮንም እነዚህን ተአምራት በንጉሡ ፊት አደረጉ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የንጉሡን ልብ ስላደነደነ እስራኤላውያን ከምድሪቱ እንዲወጡ አልፈቀደላቸውም።
Currently Selected:
ኦሪት ዘጸአት 11: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997