ኦሪት ዘጸአት 12
12
የሞት መቅሠፍት አልፎ መሄድ
1እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን በግብጽ ምድር እንዲህ ሲል ተናገራቸው፤ 2“ይህ ወር ለእናንተ የዓመቱ መጀመሪያ ወር ይሁንላችሁ፤ 3ለመላው የእስራኤል ሕዝብ ይህን ሥርዓት አስተምሩ፤ ይህ ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን እያንዳንዱ ሰው በቤተሰቡ ደረጃ አንድ ጠቦት ይምረጥ። 4ቤተሰቡ አነስተኛ ከመሆኑ የተነሣ እንስሳውን በልቶ ለመጨረስ የማይችል ከሆነ ግን እርሱና የቅርብ ጐረቤቱ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ሊመገበው የሚችለውን ያኽል ተመጥኖ እንስሳውን በአንድነት አብረው ይብሉት። 5የምትመርጡት እንስሳ በግ ወይም ፍየል መሆን ይችላል፤ ነገር ግን ምንም ነውር የሌለበትና አንድ ዓመት የሞላው ተባዕት ይሁን። 6እነዚህንም እስከ ዐሥራ አራተኛው ቀን ጠብቁአቸው። በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት ላይ የእስራኤል ኅብረተሰብ ሁሉ እንስሶቹን ይረዱ። 7ሕዝቡም ከደሙ ወስደው የእንስሶቹ ሥጋ የሚበላበትንም እያንዳንዱን ቤት ደጃፍ መቃኑንና ጉበኑን ሁሉ ይቀቡት፤ 8ሥጋውንም በዚያኑ ሌሊት እየጠበሱ ከመራር ቅጠልና ካልቦካ ቂጣ ጋር ይብሉት። 9ከሥጋውም ጥሬውን ወይም ቅቅሉን አትብሉ፤ ራሱን፥ እግሮቹን የሆድ ዕቃውንም ጭምር በሙሉ ጠብሳችሁ ሥጋውን ብሉት። 10እስከሚነጋም ድረስ ከሥጋው ምንም ነገር አታስተርፉ፤ የተረፈ ነገር ቢኖር ሁሉንም በእሳት አቃጥሉት። 11ለጒዞ እንደ ተዘጋጀ ሰው ሆናችሁ ወገባችሁን በመታጠቅ ጫማችሁን አድርጋችሁ፥ በትራችሁን በእጃችሁ ይዛችሁ በችኰላ ብሉት፤ እርሱም እኔን እግዚአብሔርን የምታከብሩበት የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ።
12“በዚያችም ሌሊት እኔ በግብጽ ምድር ሁሉ እየተላለፍኩ እያንዳንዱን የሰውም ሆነ የእንስሳ ዘር የሆነውን የበኲር ልጅ ሁሉ እገድላለሁ፤ የግብጽንም አማልክት ሁሉ እቀጣለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። 13በደጃፎቻችሁ መቃኖች ላይ የሚታየው ደም እናንተ የምትኖሩባቸውን ቤቶች ለይቶ የሚያሳይ ምልክት ይሆናል፤ እኔም ደሙን በማይበት ጊዜ አልፌአችሁ እሄዳለሁ፤ በዚህም ዐይነት ግብጻውያንን በመቅሠፍት በምመታበት ጊዜ፥ በእናንተ ላይ ምንም ዐይነት መቅሠፍት አይደርስባችሁም። #ዘሌ. 23፥5፤ ዘዳ. 16፥3-8። 14እኔ እግዚአብሔር ያደረግኹላችሁን ሁሉ በማስታወስ ይህ ቀን መንፈሳዊ ክብረ በዓል ይሁንላችሁ፤ እርሱንም በሚመጡት ዘመናት ሁሉ እንድታከብሩት ቋሚ ሥርዓት ይሁንላችሁ።”
የቂጣ በዓል
15እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ሰባት ቀን ሙሉ እርሾ ያልነካውና ፈጽሞ ያልቦካ ቂጣ ብቻ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያው ቀን እርሾውን ሁሉ ከየቤታችሁ ታስወግዳላችሁ፤ ማንም ሰው በነዚያ ሰባት ቀኖች እርሾ ያለበትን እንጀራ ቢበላ ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ይወገዳል። 16ከዚያም ሰባት ቀኖች በመጀመሪያውና በሰባተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ታደርጋላችሁ፤ በነዚያም ቀኖች ምግባችሁን ከማዘጋጀት በቀር ምንም ሥራ አትሠሩም። 17መላውን የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር መርቼ ያወጣሁት በዚህ ቀን ስለ ሆነ ይህን የቂጣ በዓል ትጠብቃላችሁ፤ በሚመጡትም ዘመናት ሁሉ ይህን በዓል ማክበር ቋሚ ሥርዓት ይሁንላችሁ። 18ከመጀመሪያው ወር ከዐሥራ አራተኛው ቀን ዋዜማ ምሽት ጀምሮ እስከ ኻያ አንደኛው ቀን ምሽት ድረስ ያልቦካ እንጀራ ትበላላችሁ። 19እስከ ሰባት ቀን ምንም እርሾ በቤታችሁ መገኘት የለበትም፤ የአገር ተወላጅም ሆነ ወይም መጻተኛ ማንኛውም ሰው የቦካ እንጀራ ቢበላ፥ ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ይወገዳል፤ 20በማንኛውም ስፍራ ብትሆኑ እርሾ የሌለበት ቂጣ ብሉ እንጂ እርሾ ያለበት ምንም ነገር አትብሉ።”
የመጀመሪያው ፋሲካ
21ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ አለቆች ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ቤተሰባችሁ ሁሉ የፋሲካን በዓል እንዲያከብር ከእናንተ እያንዳንዱ ጠቦት መርጦ ይረድ፤ 22ጭብጥ የሚሞላ የሂሶጵ ቅጠል ውሰዱ፤ በሳሕን ያለውንም ደም በቅጠሉ እየነከራችሁ የቤታችሁን በር መቃኖችና በላይ በኩል ያለውን ጉበን ቀቡ፤ እስከ ማግስቱ ጠዋት ድረስ ማንም ሰው ከቤቱ አይውጣ። 23እግዚአብሔር ግብጻውያንን በሞት ለመቅጣት በግብጽ ምድር ያልፋል፤ በጉበንና በመቃኖቹ ላይ ያለውንም ደም በሚያይበት ጊዜ አልፎ ይሄዳል፤ የሞት መልአክም ወደየቤታችሁ ገብቶ እናንተን እንዳይገድል ያደርጋል፤ #ዕብ. 11፥28። 24እናንተና ልጆቻችሁ ይህን ሥርዓት ለዘለዓለም ትጠብቁታላችሁ፤ 25እግዚአብሔር ሊያወርሳችሁ ተስፋ ወደ ሰጣችሁ ምድር ስትገቡም ይህን ሥርዓት ትፈጽማላችሁ። 26ልጆቻችሁ ‘ይህ ሥርዓት ምንድን ነው?’ ብለው በሚጠይቁአችሁ ጊዜ፥ 27እናንተም እንዲህ ብላችሁ ትመልሱላቸዋላችሁ፤ ‘ይህ እግዚአብሔርን ለማክበር የሚደረግ የፋሲካ መሥዋዕት ነው፤ እግዚአብሔር በግብጽ ምድር የእስራኤላውያንን መኖሪያ ቤቶች አልፎ በመሄድ ግብጻውያንን ሲገድል እኛን አድኖናል።’ ”
እስራኤላውያንም ይህን በሰሙ ጊዜ ተንበርክከው ሰገዱ፤ 28ሄደውም በሙሴና በአሮን አማካይነት እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ሁሉ አደረጉ።
የግብጻውያን የበኲር ልጆች በሞት መቀሠፍ
29እኩለ ሌሊት ሲሆን እግዚአብሔር ከንጉሡ አልጋ ወራሽ ጀምሮ ከምድር በታች ባለ እስር ቤት ውስጥ እስከ ተጣለው የእስረኛ ልጅ ድረስ በግብጽ ምድር በኲር የሆነውን ወንድ ልጅ ሁሉ በሞት ቀጣ፤ በኲር ሆነው የተወለዱ እንስሶችም ተገደሉ። 30በዚያኑ ሌሊት ንጉሡና መኳንንቱ፥ መላውም የግብጽ ሕዝብ ሁሉ ከእንቅልፋቸው ነቁ፤ ወንድ ልጅ ያልሞተበት አንድ ቤት እንኳ ስላልነበረ በግብጽ ምድር ሁሉ ታላቅ የለቅሶ ጩኸት አስተጋባ። 31በዚያኑ ሌሊት ንጉሡ ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተና እስራኤላውያን ወገኖቻችሁ ሁሉ ከዚህ ውጡ! አገሬን ለቃችሁ ሂዱ! በጠየቃችሁትም መሠረት ለእግዚአብሔር ስገዱ! 32የበግ፥ የፍየልና የቀንድ ከብት መንጋችሁን ሁሉ ይዛችሁ ሂዱ፤ እኔንም ባርኩኝ።”
33አገሪቱን ለቀውላቸው እንዲወጡ ግብጻውያን ራሳቸውም ሕዝቡን በማጣደፍ “በአስቸኳይ ለቃችሁ ካልወጣችሁልን እነሆ ሁላችንም ማለቃችን ነው” አሉአቸው። 34ስለዚህም ሕዝቡ ያልቦካውን ሊጥ በቡሆ ዕቃ ሞልተው በልብስ በመጠቅለል በትከሻቸው ተሸከሙ፤ 35እስራኤላውያን ሙሴ እንዳዘዛቸውም አደረጉ፤ ይኸውም የወርቅና የብር ጌጣጌጥ እንዲሁም ልብስ እንዲሰጡአቸው ግብጻውያንን ጠየቁ። 36እግዚአብሔርም እስራኤላውያን በግብጻውያን ዘንድ ሞገስ እንዲያገኙና የጠየቁትንም ሁሉ ማግኘት እንዲችሉ አደረገ፤ በዚህም ዐይነት እስራኤላውያን የግብጽን ሀብት በዝብዘው ሄዱ። #ዘፀ. 3፥21-22።
የእስራኤላውያን ከግብጽ መውጣት
37እስራኤላውያንም ከራምሴ ተነሥተው ወደ ሱኮት ለመሄድ በእግር ጒዞ ጀመሩ፤ የሰዎቹም ብዛት ሴቶችና ልጆች ሳይቈጠሩ ስድስት መቶ ሺህ ነበር። 38ከእነርሱ ጋር ቊጥሩ የበዛ ሌላ ድብልቅ ሕዝብ ብዙ የበግ፥ የፍየልና የቀንድ ከብት መንጋ እየነዳ ወጣ። 39ከግብጽ በድንገት ተጣድፈው ስለ ወጡ ምግባቸውን ለማዘጋጀትም ሆነ በእርሾ የቦካ እንጀራ ለመጋገር ጊዜ ስላልነበራቸው ከግብጽ ይዘው ካወጡትም ሊጥ ቂጣ ጋገሩ።
40እስራኤላውያን በግብጽ ምድር የኖሩት አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ነበር፤ #ዘፍ. 15፥13፤ ገላ. 3፥17። 41አራት መቶ ሠላሳው ዓመት በተፈጸመበትም ቀን የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ የግብጽን ምድር ለቆ ወጣ። 42እግዚአብሔር ሕዝቡን እየጠበቀ ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ዕለት ጊዜው ሌሊት ነበር፤ ያም ሌሊት እስራኤላውያን በመጠባበቅ ተግተው የሚያድሩበት ለሚመጣው ትውልድ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሌሊት ነው።
የፋሲካ በዓል አከባበር ሥርዓት
43እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ “የፋሲካ በዓል አከባበር ሥርዓት ይህ ነው፤ ማንኛውም የባዕድ አገር ሰው የፋሲካን ራት አይብላ፤ 44ባሪያ እንዲሆናችሁ በገንዘባችሁ የገዛችሁት ሰው ግን አስቀድማችሁ ከገረዛችሁት በኋላ መብላት ይችላል። 45በዚያን ጊዜ በሀገር ውስጥ የሚኖር እንግዳ ሰው ወይም አዲስ ቅጥር ሠራተኛ አይብላ። 46ምግቡ በሙሉ በዚያው በተዘጋጀበት ቤት ውስጥ መበላት ስላለበት ወደ ውጪ አይውጣ፤ ከጠቦቱም አጥንቶቹን አትስበሩ። #ዘኍ. 9፥12፤ ዮሐ. 19፥36። 47መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ይህን በዓል ያክብረው። 48ነገር ግን ያልተገረዘ ማንም ሰው አይብላ፤ የውጪ አገር ሰው በመካከላችሁ ቢኖርና የእግዚአብሔርን የፋሲካ በዓል ማክበር ቢፈልግ፥ አስቀድማችሁ በቤተሰቡ ያሉትን ወንዶች ሁሉ ግረዙ፤ ከዚያም በኋላ የሀገር ተወላጅ እስራኤላዊ እንደ ሆነ ተቈጥሮ የፋሲካን በዓል ለማክበር ከእናንተ ጋር ይተባበር። 49እንግዲህ ይህ ሕግ ለእናንተ ለእስራኤላውያኑም ሆነ በመካከላችሁ ለሚኖሩት መጻተኞች በተመሳሳይ ሁኔታ ይፈጸም።” 50እስራኤላውያን ሁሉ ታዛዦች በመሆን እግዚአብሔር በሙሴና በአሮን አማካይነት ያዘዘውን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁዎች ሆኑ፤ 51በዚያን ቀን እግዚአብሔር መላውን የእስራኤል ሕዝብ በክፍል በክፍል ከግብጽ ምድር መርቶ አወጣ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘጸአት 12: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997