ኦሪት ዘጸአት 21
21
ለባሪያዎች ሊደረግላቸው የሚገባ አያያዝ
(ዘዳ. 15፥12-18)
1“ለእስራኤላውያን የምትሰጣቸው ሕግ ይህ ነው፤ 2ዕብራዊ ባሪያ ብትገዛ ስድስት ዓመት ያገልግልህ፤ በሰባተኛው ዓመት ያለ ምንም ዕዳ ነጻ እንዲወጣ አድርገው፤ 3ባሪያ እንዲሆንህ አንተ በገዛኸው ጊዜ ሚስት ያላገባ ከሆነ፥ ለቆ በሚወጣበት ጊዜ ብቻውን ይሂድ፤ ባሪያው በገዛኸው ጊዜ ሚስት አግብቶ ከሆነ ግን ሚስቱን ይዞ ይውጣ። 4ጌታው ሚስት የምትሆነው ሴት ሰጥቶት ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወልዳለት ከሆነ ሴትዮዋ ከነልጆችዋ የጌታው ትሁን፤ ሰውየው ግን ብቻውን ነጻ ይውጣ። 5ባሪያው ግን ‘ጌታዬን፥ ሚስቴንና ልጆቼን እወዳለሁ’ ብሎ ነጻ መውጣት ባይፈልግ፥ 6ጌታው የእግዚአብሔር አገልጋዮች ወደ ሆኑ ፈራጆች ዘንድ ይውሰደው፤ እዚያም ከበር ወይም ከበር መቃን አጠገብ አቁሞ ጆሮውን በወስፌ ይብሳው፤ ከዚያም በኋላ እስከ ዕድሜ ልኩ ድረስ ባርያ ሆኖ ያገልግለው። #ዘሌ. 25፥39-46።
7“አንድ ሰው ሴት ልጁን ለባርነት ቢሸጥ እንደ ወንዶቹ አገልጋዮች ነጻ አትውጣ፤ 8ሚስት ሊያደርጋት ለፈለገ ሰው ብትሸጥና በኋላም እርሱ ሳይወዳት ቢቀር ተመልሳ በሕዝብዋ ትዋጅ ጌታዋ የማይገባ ነገር ስላደረገባት ለባዕድ ሊሸጣት አይችልም። 9ሚስት ትሆንለት ዘንድ ለልጁ ሊሰጣት ከፈለገ ግን እንደ ሴት ልጁ አድርጎ ይቊጠራት። 10ሁለተኛ ሚስት ቢያገባ ለመጀመሪያ ሚስቱ ምግብና ልብስ መስጠቱን አይተው፤ ቀድሞ የነበራትንም የጋብቻ መብት አይከልክላት። 11እነዚህን ሦስት ግዴታዎች የማይፈጽምላት ከሆነ ግን ያለ ምንም ዕዳ ነጻ ይልቀቃት።
ዐመፅ የሚፈጽሙ ሰዎች ስለሚቀጡበት ሕግ
12“ሰውን ደብድቦ የሚገድል ሁሉ በሞት ይቀጣ፤ #ዘሌ. 24፥17። 13ሆን ብሎ ደፈጣ በማድረግ ሳይሆን በድንገተኛ አጋጣሚ ቢሞትበት ግን ሸሽቶ በማምለጥ በሰላም የሚኖርበትን ስፍራ እኔ አዘጋጅላችኋለሁ፤ #ዘኍ. 35፥10-34፤ ዘዳ. 19፥1-13፤ ኢያሱ 20፥1-9። 14ይሁን እንጂ ሰው በቊጣ ተነሣሥቶና ሆን ብሎ ሌላ ሰው ቢገድል፥ ሕይወቱን ለማዳን ወደ መሠዊያዬ ሸሽቶ ቢሄድ በሞት ይቀጣ።
15“አባቱን ወይም እናቱን የሚመታ በሞት ይቀጣ፤
16“ሊሸጠው ወይም ባርያ አድርጎ ሊገዛው አስቦ ሰውን አፍኖ የሚወስድ ሁሉ በሞት ይቀጣ። #ዘዳ. 24፥7።
17“አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ በሞት ይቀጣ። #ዘሌ. 20፥9፤ ማቴ. 15፥4፤ ማር. 7፥10።
18“ሁለት ሰዎች ቢጣሉና አንደኛው ሌላውን በድንጋይ ቢፈነክተው ወይም በቡጢ ቢያቈስለው ካልገደለው በቀር በሞት አይቀጣ፤ የተመታው ሰው ታሞ በአልጋ ላይ ቢውል፥ 19በኋላም ተነሥቶ በትር እየተመረኰዘ መራመድ ቢቀጥል፤ ስለ ባከነበት ጊዜ የመታው ሰው ካሣ ይክፈለው፤ በደንብ እስከሚድንም ድረስ ተገቢውን እንክብካቤ ያድርግለት።
20“አንድ ሰው ወንድም ሆነ ሴት ባሪያውን በበትር ቢመታና ወዲያው ቢሞትበት መቀጣት ይገባዋል፤ 21ነገር ግን ባሪያው በአንድ ቀን ወይም በሁለት ቀን ውስጥ ባይሞት አሳዳሪ ጌታው አይቀጣም፤ ባሪያውን ማጣቱ ራሱ ቅጣት ነው።
22“ሁለት ሰዎች ሲጣሉ አንዲት ነፍሰ ጡር መተው ቢያስወርዳትና ሌላ ምንም ጒዳት ሳይደርስባት ቢቀር፥ ያ ጒዳት ያደረሰባት ሰው የሴቲቱ ባል የሚጠይቀውን ያኽል ካሣ ይክፈል፤ ይህም የሚከፍለው ካሣ መጠን በዳኞች የጸደቀ ይሁን። 23ነገር ግን ሴትዮዋ ራስዋ ብርቱ ጒዳት የደረሰባት ከሆነች ቅጣቱ ‘በሕይወት ምትክ ሕይወት፥ 24በዐይን ምትክ ዐይን፥ በጥርስ ምትክ ጥርስ፥ በእጅ ምትክ እጅ፥ በእግር ምትክ እግር፥ #ዘሌ. 24፥19-20፤ ዘዳ. 19፥21፤ ማቴ. 5፥38። 25በቃጠሎ ምትክ ቃጠሎ፥ በቊስል ምትክ ቊስል፥ በመፈንከት ምትክ መፈንከት’ በሚለው ሕግ መሠረት ይወሰን።
26“አንድ ሰው የወንድ ወይም የሴት ባሪያውን ዐይን መትቶ ቢያጠፋ ስለ ዐይኑ ካሣ ባሪያውን ነጻ ይልቀቅ። 27በዚሁ ዐይነት አንድ ጥርሱን እንኳ ቢሰብር፥ ስለ ጥርሱ ካሣ ባሪያውን ነጻ ይልቀቀው።
የባለ ንብረቶች ኀላፊነት
28“በሬ ሰው ወግቶ ቢገድል በድንጋይ ተወግሮ ይሙት፤ ሥጋውም አይበላ፤ ባለ ንብረቱም በነጻ ይለቀቅ። 29በሬው የተዋጊነት ልማድ ያለው ቢሆንና ባለቤቱም ቀደም ሲል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት በበረት ሳይዘው ቀርቶ ቢሆን ግን በሬው ሰው በሚወጋበት ጊዜ በድንጋይ ተወግሮ ይሙት፤ ባለ ንብረቱም በሞት ይቀጣ። 30ሆኖም ባለ ንብረቱ ሕይወቱን ለመዋጀት ካሣ እንዲከፍል ከተፈቀደለት ካሣውን በሙሉ ይክፈል። 31በሬው ወንድ ወይም ሴት ልጅ ወግቶ ቢገድል ቅጣቱ ተመሳሳይ ይሁን። 32በሬው ወንድ ወይም ሴት ባሪያ ወግቶ ቢገድል የበሬው ባለቤት ለባሪያው ጌታ ሠላሳ ብር ይክፈለው፤ በሬውም በድንጋይ ተወግሮ ይሙት።
33“አንድ ሰው የጒድጓድ መክደኛ ቢያነሣ ወይም ጒድጓድ ቆፍሮ ሳይከድነው ቢቀርና በሬ ወይም አህያ ወደዚያ ጒድጓድ ቢገባ፥ 34የእንስሳውን ዋጋ ይክፈል፤ ገንዘቡን ለእንስሳው ባለቤት ከከፈለ በኋላ የሞተውን እንስሳ ለራሱ ያስቀር። 35የአንድ ሰው በሬ የሌላውን ሰው በሬ ወግቶ ቢገድል ሁለቱ ሰዎች በሕይወት ያለውን በሬ ሸጠው ገንዘቡን ለሁለት ይካፈሉት፤ የሞተውንም በሬ ሥጋ ለሁለት ይካፈሉ። 36ነገር ግን በሬው ተዋጊ መሆኑ ታውቆ ሳለ ባለቤቱ በበረት ውስጥ ሳይዘው ቀርቶ ከሆነ፥ በሬው ለሞተበት ሰው አንድ በሕይወት ያለ በሬ ካሣ ይክፈል፤ የሞተውንም በሬ ለራሱ ያስቀር።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘጸአት 21: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997