ኦሪት ዘፍጥረት 49
49
ያዕቆብ ልጆቹን ሲመርቅ የተናገረው ቃል
1ያዕቆብ ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በአንድነት ተሰብሰቡና ወደ ፊት የሚገጥማችሁን ነገር ልንገራችሁ፤
2እናንተ የያዕቆብ ልጆች፥
በአንድነት ተሰብስባችሁ ስሙ፤
አባታችሁ እስራኤል የሚነግራችሁንም አድምጡ።
3“ሮቤል፥ ኀይልና የጐልማሳነት ብርታት በነበረኝ ጊዜ፥
የወለድኩህ የበኲር ልጄ ነህ።
ከልጆቼ ሁሉ በክብርና በኀይል
የምትበልጥ አንተ ነህ።
4ይሁን እንጂ እንደ ውሃ የምትዋልል ስለ ሆንክ፥
የበላይ አለቅነት ለአንተ አይገባም፤
ወደ አባትህ አልጋ ወጥተሃል፤
የአባትህንም ቁባት ደፍረሃል።
5“ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች ናቸው፤
ዐመፅ ለመፈጸም የጦር መሣሪያቸውን ያነሣሉ።
6እነርሱ በቊጣቸው ብዙ ወንዶችን ስለ ገደሉ፥
ከንቱ ምኞታቸውን ለማርካት ብዙ ኰርማዎችን ስለ ሰባበሩ፥
በእነርሱ ምክር አልገባም፤
የጉባኤውም ተካፋይ አልሆንም።
7እጅግ አስፈሪ የሆነ ቊጣቸው፥
እጅግ ጨካኝ የሆነ መዓታቸው፥
የተረገመ ይሁን።
በእስራኤል ምድር ሁሉ እበታትናቸዋለሁ፤
በሕዝቡም መካከል እከፋፍላቸዋለሁ።
8“ይሁዳ፥ ወንድሞችህ ያመሰግኑሃል፤
እጅህ በጠላቶችህ አንገት ላይ ይበረታል፤
ወንድሞችህ በፊትህ ራሳቸውን
ዝቅ አድርገው እጅ ይነሡሃል።
9ይሁዳ እንደ ደቦል አንበሳ ነው፤
ልጄ መብል የሚሆነውን አድኖ፥
ወደ ዋሻው ይመለሳል፤
እንደ አንበሳ ተዝናንቶ ይተኛል፤
ሊቀሰቅሰው የሚደፍር ማነው? #ዘኍ. 24፥9፤ ራዕ. 5፥5።
10‘ሴሎ’ ተብሎ የሚጠራው፥ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለትና
ለዘለዓለም የሚነግሠው እስኪመጣ ድረስ፥
በትረ መንግሥት (የገዢነት ሥልጣን) ከይሁዳ እጅ አይወጣም።
11አህያውን በወይን ግንድ ላይ፥
ውርንጫውን በወይን ሐረግ ላይ ያስራል፤
ልብሱን በወይን ጠጅ፥
መጐናጸፊያውን እንደ ደም በቀላ የወይን ጭማቂ ያጥባል።
12ዐይኖቹ ከወይን ጠጅ ይልቅ ይቀላሉ፤
ጥርሶቹ ከወተት ይልቅ ይነጣሉ።
13“ዛብሎን በባሕር ዳር ይኖራል፤
ወደቡም የመርከቦች ማረፊያ ይሆናል፤
የመኖሪያውም ወሰን እስከ ሲዶና ይደርሳል።
14“ይሳኮር በበጎች መካከል እንደሚተኛ
ብርቱ አህያ ነው።
15ነገር ግን ማረፊያው መልካም
ምድሩም አስደሳች መሆኑን ባየ ጊዜ፥
ጭነቱን ለመሸከም ትከሻውን ዝቅ ያደርጋል፤
እንደ አገልጋይ ሆኖም ከባድ የጒልበት ሥራ ይሠራል።
16“ዳን፥ ከእስራኤል ነገዶች አንዱ ለሆነው ሕዝብ ፈራጅ ይሆናል።
17ፈረሰኛው ሰው ወደኋላው ይወድቅ ዘንድ፥
ዳን እንደ ነዳፊ እባብ ሆኖ፥
በመተላለፊያው መንገድ ላይ
የፈረሱን ሰኰና ይነክሳል።
18“አምላክ ሆይ፥
አዳኝነትህን እጠባበቃለሁ።
19“ጋድን ቀማኞች ያጠቁታል፤
እርሱም ዱካቸውን በመከተል
መልሶ ያሳድዳቸዋል።
20“አሴር ከምድሩ ብዙ ሀብት አግኝቶ ይበለጽጋል፤
በነገሥታት ፊት መቅረብ የሚችል ጥሩ ምግብ ያዘጋጃል።
21“ንፍታሌም በነጻነት እየተዘዋወረች እንደምትኖር፥
ደስ የሚያሰኙ ግልገሎችን እንደምትወልድ
ሚዳቋ ነው።
22“ዮሴፍ፥ በውሃ ምንጭ አጠገብ ተተክሎ፥
ሐረጎቹ በግድግዳ ላይ እንደሚዘረጉ ፍሬያማ ዛፍ ነው።
23ቀስተኞቹ በብርቱ ያጠቁታል፤
በቀስታቸውም እየነደፉ ያሳድዱታል።
24ነገር ግን ብርቱ በሆነ በያዕቆብ አምላክ ኀይል፥
በእስራኤል እረኛና ጠባቂ ብርታት፥
የእርሱ ቀስት ጽኑ ይሆናል፤
ክንዱም ይበረታል።
25የአባትህ አምላክ ይረዳሃል፤
ሁሉን የሚችል አምላክ ከላይ ከሰማይ ዝናብን፥
ከምድርም ጥልቀት ውሃን በመስጠት ይባርክሃል፤
ብዙ ከብትና ብዙ ልጆችም ይሰጥሃል።
26ከጥንት ጀምሮ ጸንተው ከሚኖሩት
ተራራዎችና ዘለዓለማውያን ከሆኑት ኮረብታዎችም
ከሚገኘው ደስ ከሚያሰኝ በረከት ሁሉ
የአባትህ በረከት ይበልጣል።
እንግዲህ ይህ ሁሉ በረከት በዮሴፍ ራስ ላይ ይሁን፤
በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነውም በዮሴፍ አናት ላይ ይውረድ።
27“ብንያም እንደ ነጣቂ ተኲላ ነው፤
በማለዳ ያደነውን ራሱ ይበላል፤
በምሽት ያደነውን ግን ያካፍላል።”
28እንግዲህ እነዚህ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው፤ አባታቸው በባረካቸው ጊዜ ለእያንዳንዱ ተስማሚ የሆነውን የበረከት ቃል የተናገረው በዚህ ሁኔታ ነበር።
የያዕቆብ መሞትና መቀበር
29ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልጆቹን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፤ “እኔ በሞት ወደ ወገኖቼ የምሄድበት ጊዜ ደርሶአል፤ ስለዚህ በሒታዊው በዔፍሮን እርሻ ላይ ባለው ዋሻ ውስጥ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ፤ 30ይህም ዋሻ በከነዓን ምድር ከመምሬ በስተምሥራቅ በኩል በማክፌላ የሚገኘው ነው፤ አብርሃም ይህ ዋሻ የሚገኝበትን እርሻ ለመቃብር ቦታ የገዛው ከሒታዊው ከዔፍሮን ነው። #ዘፍ. 23፥3-20። 31አብርሃምና ሚስቱ ሣራ፥ ይስሐቅና ሚስቱም ርብቃ የተቀበሩት እዚያ ነው፤ እኔም ልያን የቀበርኳት እዚያው ነው። #ዘፍ. 25፥9-10፤ 35፥29። 32እርሻውና ዋሻው በአንድነት የተገዙት ከሒታውያን ነው፤ ስለዚህ እኔንም እዚያው ቅበሩኝ።”
33ያዕቆብ ለልጆቹ ትእዛዝ መስጠቱን ካበቃ በኋላ፥ እግሮቹን በመኝታው ላይ ሰብሰብ አድርጎ ጋደም እንዳለ በሞት ወደ ወገኖቹ ተሰበሰበ። #ሐ.ሥ. 7፥15።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 49: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
ኦሪት ዘፍጥረት 49
49
ያዕቆብ ልጆቹን ሲመርቅ የተናገረው ቃል
1ያዕቆብ ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በአንድነት ተሰብሰቡና ወደ ፊት የሚገጥማችሁን ነገር ልንገራችሁ፤
2እናንተ የያዕቆብ ልጆች፥
በአንድነት ተሰብስባችሁ ስሙ፤
አባታችሁ እስራኤል የሚነግራችሁንም አድምጡ።
3“ሮቤል፥ ኀይልና የጐልማሳነት ብርታት በነበረኝ ጊዜ፥
የወለድኩህ የበኲር ልጄ ነህ።
ከልጆቼ ሁሉ በክብርና በኀይል
የምትበልጥ አንተ ነህ።
4ይሁን እንጂ እንደ ውሃ የምትዋልል ስለ ሆንክ፥
የበላይ አለቅነት ለአንተ አይገባም፤
ወደ አባትህ አልጋ ወጥተሃል፤
የአባትህንም ቁባት ደፍረሃል።
5“ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች ናቸው፤
ዐመፅ ለመፈጸም የጦር መሣሪያቸውን ያነሣሉ።
6እነርሱ በቊጣቸው ብዙ ወንዶችን ስለ ገደሉ፥
ከንቱ ምኞታቸውን ለማርካት ብዙ ኰርማዎችን ስለ ሰባበሩ፥
በእነርሱ ምክር አልገባም፤
የጉባኤውም ተካፋይ አልሆንም።
7እጅግ አስፈሪ የሆነ ቊጣቸው፥
እጅግ ጨካኝ የሆነ መዓታቸው፥
የተረገመ ይሁን።
በእስራኤል ምድር ሁሉ እበታትናቸዋለሁ፤
በሕዝቡም መካከል እከፋፍላቸዋለሁ።
8“ይሁዳ፥ ወንድሞችህ ያመሰግኑሃል፤
እጅህ በጠላቶችህ አንገት ላይ ይበረታል፤
ወንድሞችህ በፊትህ ራሳቸውን
ዝቅ አድርገው እጅ ይነሡሃል።
9ይሁዳ እንደ ደቦል አንበሳ ነው፤
ልጄ መብል የሚሆነውን አድኖ፥
ወደ ዋሻው ይመለሳል፤
እንደ አንበሳ ተዝናንቶ ይተኛል፤
ሊቀሰቅሰው የሚደፍር ማነው? #ዘኍ. 24፥9፤ ራዕ. 5፥5።
10‘ሴሎ’ ተብሎ የሚጠራው፥ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለትና
ለዘለዓለም የሚነግሠው እስኪመጣ ድረስ፥
በትረ መንግሥት (የገዢነት ሥልጣን) ከይሁዳ እጅ አይወጣም።
11አህያውን በወይን ግንድ ላይ፥
ውርንጫውን በወይን ሐረግ ላይ ያስራል፤
ልብሱን በወይን ጠጅ፥
መጐናጸፊያውን እንደ ደም በቀላ የወይን ጭማቂ ያጥባል።
12ዐይኖቹ ከወይን ጠጅ ይልቅ ይቀላሉ፤
ጥርሶቹ ከወተት ይልቅ ይነጣሉ።
13“ዛብሎን በባሕር ዳር ይኖራል፤
ወደቡም የመርከቦች ማረፊያ ይሆናል፤
የመኖሪያውም ወሰን እስከ ሲዶና ይደርሳል።
14“ይሳኮር በበጎች መካከል እንደሚተኛ
ብርቱ አህያ ነው።
15ነገር ግን ማረፊያው መልካም
ምድሩም አስደሳች መሆኑን ባየ ጊዜ፥
ጭነቱን ለመሸከም ትከሻውን ዝቅ ያደርጋል፤
እንደ አገልጋይ ሆኖም ከባድ የጒልበት ሥራ ይሠራል።
16“ዳን፥ ከእስራኤል ነገዶች አንዱ ለሆነው ሕዝብ ፈራጅ ይሆናል።
17ፈረሰኛው ሰው ወደኋላው ይወድቅ ዘንድ፥
ዳን እንደ ነዳፊ እባብ ሆኖ፥
በመተላለፊያው መንገድ ላይ
የፈረሱን ሰኰና ይነክሳል።
18“አምላክ ሆይ፥
አዳኝነትህን እጠባበቃለሁ።
19“ጋድን ቀማኞች ያጠቁታል፤
እርሱም ዱካቸውን በመከተል
መልሶ ያሳድዳቸዋል።
20“አሴር ከምድሩ ብዙ ሀብት አግኝቶ ይበለጽጋል፤
በነገሥታት ፊት መቅረብ የሚችል ጥሩ ምግብ ያዘጋጃል።
21“ንፍታሌም በነጻነት እየተዘዋወረች እንደምትኖር፥
ደስ የሚያሰኙ ግልገሎችን እንደምትወልድ
ሚዳቋ ነው።
22“ዮሴፍ፥ በውሃ ምንጭ አጠገብ ተተክሎ፥
ሐረጎቹ በግድግዳ ላይ እንደሚዘረጉ ፍሬያማ ዛፍ ነው።
23ቀስተኞቹ በብርቱ ያጠቁታል፤
በቀስታቸውም እየነደፉ ያሳድዱታል።
24ነገር ግን ብርቱ በሆነ በያዕቆብ አምላክ ኀይል፥
በእስራኤል እረኛና ጠባቂ ብርታት፥
የእርሱ ቀስት ጽኑ ይሆናል፤
ክንዱም ይበረታል።
25የአባትህ አምላክ ይረዳሃል፤
ሁሉን የሚችል አምላክ ከላይ ከሰማይ ዝናብን፥
ከምድርም ጥልቀት ውሃን በመስጠት ይባርክሃል፤
ብዙ ከብትና ብዙ ልጆችም ይሰጥሃል።
26ከጥንት ጀምሮ ጸንተው ከሚኖሩት
ተራራዎችና ዘለዓለማውያን ከሆኑት ኮረብታዎችም
ከሚገኘው ደስ ከሚያሰኝ በረከት ሁሉ
የአባትህ በረከት ይበልጣል።
እንግዲህ ይህ ሁሉ በረከት በዮሴፍ ራስ ላይ ይሁን፤
በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነውም በዮሴፍ አናት ላይ ይውረድ።
27“ብንያም እንደ ነጣቂ ተኲላ ነው፤
በማለዳ ያደነውን ራሱ ይበላል፤
በምሽት ያደነውን ግን ያካፍላል።”
28እንግዲህ እነዚህ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው፤ አባታቸው በባረካቸው ጊዜ ለእያንዳንዱ ተስማሚ የሆነውን የበረከት ቃል የተናገረው በዚህ ሁኔታ ነበር።
የያዕቆብ መሞትና መቀበር
29ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልጆቹን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፤ “እኔ በሞት ወደ ወገኖቼ የምሄድበት ጊዜ ደርሶአል፤ ስለዚህ በሒታዊው በዔፍሮን እርሻ ላይ ባለው ዋሻ ውስጥ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ፤ 30ይህም ዋሻ በከነዓን ምድር ከመምሬ በስተምሥራቅ በኩል በማክፌላ የሚገኘው ነው፤ አብርሃም ይህ ዋሻ የሚገኝበትን እርሻ ለመቃብር ቦታ የገዛው ከሒታዊው ከዔፍሮን ነው። #ዘፍ. 23፥3-20። 31አብርሃምና ሚስቱ ሣራ፥ ይስሐቅና ሚስቱም ርብቃ የተቀበሩት እዚያ ነው፤ እኔም ልያን የቀበርኳት እዚያው ነው። #ዘፍ. 25፥9-10፤ 35፥29። 32እርሻውና ዋሻው በአንድነት የተገዙት ከሒታውያን ነው፤ ስለዚህ እኔንም እዚያው ቅበሩኝ።”
33ያዕቆብ ለልጆቹ ትእዛዝ መስጠቱን ካበቃ በኋላ፥ እግሮቹን በመኝታው ላይ ሰብሰብ አድርጎ ጋደም እንዳለ በሞት ወደ ወገኖቹ ተሰበሰበ። #ሐ.ሥ. 7፥15።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997