ትንቢተ ኤርምያስ 20
20
ኤርምያስ ፖሽሑር ከተባለው ካህን ጋር ያደረገው ክርክር
1የቤተ መቅደሱ አለቃ የሆነው የኢሜር ልጅ ፖሽሑር ይህን ስናገር በሰማ ጊዜ፥ 2ተይዤ እንድደበደብ አዘዘ፤ ከቤተ መቅደሱም በላይኛው በኩል ባለው በብንያም የቅጽር በር በእግር ግንድ እንድታሰር አደረገ። 3በማግስቱም ከሰንሰለት እስራት ከፈታኝ በኋላ እንዲህ አልኩት፥ “ከእንግዲህ ወዲህ እግዚአብሔር ስምህን ፓሽሑር ብሎ አይጠራህም፤ ለአንተ ያወጣልህ ስም ‘ሽብር በየስፍራው’ የሚል ነው። 4እግዚአብሔር ራሱ እንዲህ ብሎአል፦ ‘ለራስህና ለጓደኞችህም ጭምር አሸባሪ ላደርግህ ነው፤ እነርሱም ሁሉ በጠላቶቻቸው ሰይፍ ሲገደሉ ታያለህ፤ የይሁዳን ሕዝብ ሁሉ በባቢሎን ንጉሥ ሥልጣን ሥር አደርጋለሁ፤ እርሱ እኩሌቶቹን እስረኛ አድርጎ ወደ ባቢሎን ይወስዳቸዋል፤ እኩሌቶቹንም እዚሁ ይገድላቸዋል። 5እንዲሁም ጠላቶቻቸው የዚህችን ከተማ ሀብት ሁሉ እንዲዘርፉት፥ ያካበተችውንም ሀብትና ንብረት አጋብሰው የይሁዳን ነገሥታት የሀብት መዛግብት እንኳ ሳይቀር ጠራርገው ወደ ባቢሎን እንዲወስዱት አደርጋለሁ፤ 6ፓሽሑር ሆይ! አንተም ራስህና ቤተሰብህ በሙሉ ተማርካችሁ ወደ ባቢሎን ትወሰዳላችሁ፤ በሐሰት ከተነበይክላቸው ከወዳጆችህ ሁሉ ጋር ሞተህ በዚያው ትቀበራለህ።’ ”
ኤርምያስ ለእግዚአብሔር የገለጠው ብሶት
7እግዚአብሔር ሆይ! አታለልከኝ፤
እኔም ተታለልኩ፤
አንተ ከእኔ ትበረታለህ፤
ኀይልህም በእኔ ላይ እጅግ ከፍ ያለ ነው፤
ሰው ሁሉ በየዕለቱ በማሽሟጠጥ ይዘባበትብኛል።
8እኔ በምናገርበት ጊዜ ሁሉ
የምናገረው ዐመፅንና ጥፋትን ነው፤
አምላክ ሆይ! አንተ ያዘዝከኝን የትንቢት ቃል በመናገሬ፥
እኔ ዘወትር እሰደባለሁ፤ መላገጫም ሆኛለሁ።
9ነገር ግን “ከእንግዲህ እግዚአብሔርን አላስታውስም፤
በስሙም አልናገርም” በምልበት ጊዜ፥
ከእርሱ የተሰጠኝ የትንቢት ቃል
በውስጤ እንደ እሳት ይነዳል፤
በውስጤ ሰውሬ ልይዘው ብሞክርም፤
አፍኜ ላስቀረው አይቻለኝም።
10ብዙ ሰዎች ፈርተው በሹክሹክታ እንዲህ ሲሉ ሰማሁ፤
“አሁን ኤርምያስን ለመክሰስ መልካም አጋጣሚ ነው!”
ወዳጆቼ ናቸው የሚባሉት እንኳ ስሕተት እንዳደርግ ይጠባበቃሉ፤
“ኤርምያስ ሊታለል ይችል ይሆናል፤ ይህም ከሆነ እርሱን ይዘን እንበቀለዋለን፤” ይላሉ።
11እግዚአብሔር ግን እንደ ጀግና ወታደር ከእኔ ጋር ነው፤
ስለዚህ አሳዳጆቼ በመደናቀፍ ኀይል አጥተው ይወድቃሉ።
በሚወድቁበትም ጊዜ ክፉኛ ይዋረዳሉ፤
ውርደታቸውም ለረጅም ጊዜ ይታወሳል።
12የሠራዊት አምላክ ሆይ!
ጻድቅን ፈትነህ ታረጋግጣለህ፤
የልብንም ጥልቅ ሐሳብ ትመረምራለህ፤
አቤቱታዬን ለአንተ አቅርቤአለሁ፤
ስለዚህ ጠላቶቼን ስትበቀል እንዳይ አድርገኝ።
13ለእግዚአብሔር ዘምሩ!
ጌታን አመስግኑ!
እርሱ ችግረኞችን ከክፉ ሰዎች ኀይል ይታደጋል።
14የተወለድኩበት ቀን የተረገመ ይሁን!
እናቴ እኔን የወለደችበትም ዕለት የተባረከ አይሁን!
15ለአባቴ “ወንድ ልጅ ተወልዶልሃልና ደስ ይበልህ”
ብሎ ያበሠረው ሰው የተረገመ ይሁን!
16ያ ሰው፥ እግዚአብሔር ያለምሕረት እንደ ደመሰሳቸው ከተሞች ሆኖ ይቅር፤
በማለዳ የዋይታ ጩኸት ይስማ፤
በቀትርም በጦርነት ወሬ ይሸበር።
17መቃብር እንድትሆነኝ ምነው በእናቴ ማሕፀን በገደለኝ ኖሮ!
የእናቴ ማሕፀንም ለሁልጊዜ ትልቅ ሆኖ በኖረ ነበር።
18ሐዘንና ልፋትን ለማየት፥
ዘመኔንም በዕፍረት ለመፈጸም
ስለምን ተወለድኩ? #ኢዮብ 3፥1-19።
Currently Selected:
ትንቢተ ኤርምያስ 20: አማ05
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997