መጽሐፈ መዝሙር 13
13
ርዳታ ለማግኘት የቀረበ ጸሎት
1እግዚአብሔር ሆይ፥
እስከ መቼ ትረሳኛለህ?
የምትረሳኝ ለዘለዓለም ነውን?
እስከ መቼስ ከእኔ ትሰወራለህ?
2ችግርን እስከ መቼ መቻል ይኖርብኛል?
እስከ መቼ ልቤ ቀንና ሌሊት በሐዘን ይሞላል?
እስከ መቼስ ጠላቴ በእኔ ላይ የበላይነትን ያገኛል?
3እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ!
እባክህ አድምጠኝና መልስ ስጠኝ፤
የሞት እንቅልፍ አንቀላፍቼ እንዳልወድቅ
ብርታቱን ስጠኝ።
4ጠላቶቼ “አሸነፍነው” ብለው እንዲመኩ፥
በእኔም መውደቅ ደስ እንዲላቸው አታድርግ።
5እኔ በማያቋርጥ ፍቅርህ እተማመናለሁ፤
በማዳንህ እደሰታለሁ።
6እግዚአብሔር ሆይ!
በጎ ነገር ስላደረግህልኝ
ለአንተ እዘምራለሁ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 13: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 13
13
ርዳታ ለማግኘት የቀረበ ጸሎት
1እግዚአብሔር ሆይ፥
እስከ መቼ ትረሳኛለህ?
የምትረሳኝ ለዘለዓለም ነውን?
እስከ መቼስ ከእኔ ትሰወራለህ?
2ችግርን እስከ መቼ መቻል ይኖርብኛል?
እስከ መቼ ልቤ ቀንና ሌሊት በሐዘን ይሞላል?
እስከ መቼስ ጠላቴ በእኔ ላይ የበላይነትን ያገኛል?
3እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ!
እባክህ አድምጠኝና መልስ ስጠኝ፤
የሞት እንቅልፍ አንቀላፍቼ እንዳልወድቅ
ብርታቱን ስጠኝ።
4ጠላቶቼ “አሸነፍነው” ብለው እንዲመኩ፥
በእኔም መውደቅ ደስ እንዲላቸው አታድርግ።
5እኔ በማያቋርጥ ፍቅርህ እተማመናለሁ፤
በማዳንህ እደሰታለሁ።
6እግዚአብሔር ሆይ!
በጎ ነገር ስላደረግህልኝ
ለአንተ እዘምራለሁ።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997