መጽሐፈ መዝሙር 64
64
የመማጠኛ ጸሎት
1አምላክ ሆይ! በችግሬ ምክንያት ወደ አንተ ስጸልይ ስማ፤
ከጠላት ማስፈራራትም ጠብቀኝ።
2ከክፉዎች ምሥጢራዊ ሤራና
ከክፉ አድራጊዎች ዕቅድ ጠብቀኝ።
3እነርሱ ምላሳቸውን እንደ ሰይፍ ይስላሉ፤
እጅግ የከፋ ቃላትን እንደ ፍላጻ አነጣጥረው ይወረውራሉ።
4እነርሱም ያለ ፍርሀት ንጹሑን ሰው
ሸምቀው ይነድፉታል።
5ክፉ ሤራ ለማቀነባበር እርስ በርሳቸው ይመካከራሉ፤
ወጥመዳቸውንም የት እንደሚዘረጉ ያቅዳሉ፤
ይህን ሁሉ ሲያደርጉ “ማንም ሊያየን አይችልም” ይላሉ።
6እነርሱ ክፉ ዕቅድ ዐቀዱ፤
“በሐሳባቸውም የተቀናጀ ወንጀል እንሠራለን” ይላሉ፤
ይህም የሰው ልብና የሰው አእምሮ
በተንኰል የተሞላ መሆኑን ያሳያል።
7እግዚአብሔር ግን ፍላጻዎችን
ወደ እነርሱ ይወረውራል፤
እነርሱም በድንገት ይቈስላሉ።
8እግዚአብሔር ንግግራቸው በራሳቸው ላይ ተመልሶ እንዲወድቁ ያደርጋቸዋል።
የሚያዩአቸው ሁሉ በፍርሃት ከእነርሱ ይሸሻሉ።
9ሰዎች ሁሉ ይፈራሉ፤
ስለ እግዚአብሔር ሥራ ይናገራሉ፤
ስላደረገውም ነገር ያሰላስላሉ።
10ጻድቃን በእግዚአብሔር ደስ ይበላቸው
እርሱንም ከለላ ያድርጉ፤
ልባቸውም ቅን የሆነ ሁሉ ያመስግኑት።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 64: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 64
64
የመማጠኛ ጸሎት
1አምላክ ሆይ! በችግሬ ምክንያት ወደ አንተ ስጸልይ ስማ፤
ከጠላት ማስፈራራትም ጠብቀኝ።
2ከክፉዎች ምሥጢራዊ ሤራና
ከክፉ አድራጊዎች ዕቅድ ጠብቀኝ።
3እነርሱ ምላሳቸውን እንደ ሰይፍ ይስላሉ፤
እጅግ የከፋ ቃላትን እንደ ፍላጻ አነጣጥረው ይወረውራሉ።
4እነርሱም ያለ ፍርሀት ንጹሑን ሰው
ሸምቀው ይነድፉታል።
5ክፉ ሤራ ለማቀነባበር እርስ በርሳቸው ይመካከራሉ፤
ወጥመዳቸውንም የት እንደሚዘረጉ ያቅዳሉ፤
ይህን ሁሉ ሲያደርጉ “ማንም ሊያየን አይችልም” ይላሉ።
6እነርሱ ክፉ ዕቅድ ዐቀዱ፤
“በሐሳባቸውም የተቀናጀ ወንጀል እንሠራለን” ይላሉ፤
ይህም የሰው ልብና የሰው አእምሮ
በተንኰል የተሞላ መሆኑን ያሳያል።
7እግዚአብሔር ግን ፍላጻዎችን
ወደ እነርሱ ይወረውራል፤
እነርሱም በድንገት ይቈስላሉ።
8እግዚአብሔር ንግግራቸው በራሳቸው ላይ ተመልሶ እንዲወድቁ ያደርጋቸዋል።
የሚያዩአቸው ሁሉ በፍርሃት ከእነርሱ ይሸሻሉ።
9ሰዎች ሁሉ ይፈራሉ፤
ስለ እግዚአብሔር ሥራ ይናገራሉ፤
ስላደረገውም ነገር ያሰላስላሉ።
10ጻድቃን በእግዚአብሔር ደስ ይበላቸው
እርሱንም ከለላ ያድርጉ፤
ልባቸውም ቅን የሆነ ሁሉ ያመስግኑት።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997