ወደ ሮም ሰዎች 12
12
እግዚአብሔርን ለማገልገል እንዴት መኖር እንደሚገባ
1እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፥ ሕያውና የተቀደሰ መሥዋዕት አድርጋችሁ ሁለንተናችሁን እንድታቀርቡ በመሐሪው በእግዚአብሔር ስም እለምናችኋለሁ፤ ይህም ማቅረብ የሚገባችሁ ቅንነት ያለው እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልግሎት ነው። 2መልካሙንና ደስ የሚያሰኘውን ፍጹም የሆነውንም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ እንድትችሉ አእምሮአችሁን በማደስ ሕይወታችሁ ይለወጥ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉት።
3ደግሞም እያንዳንዳችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁ እምነት መጠን በትሕትና አስቡ እንጂ ከሚገባችሁ በላይ ስለ ራሳችሁ በትዕቢት አታስቡ ብዬ በተሰጠኝ ጸጋ እነግራችኋለሁ። 4በአንዱ አካላችን ብዙ ክፍሎች አሉ፤ እያንዳንዱም የአካል ክፍል የተለየ ሥራ አለው። 5እንዲሁም እኛ ብዙዎች ሆነን ሳለ በክርስቶስ አንድ አካል ነን፤ የአንድ አካል ክፍሎች እንደ መሆናችንም እርስ በርሳችን ተጣምረናል። #1ቆሮ. 12፥12። 6ስለዚህ እግዚአብሔር በጸጋው የሰጠንን ልዩ ልዩ ስጦታ በሥራ ላይ እናውል፤ ስጦታችን የእግዚአብሔርን ቃል ማወጅ ከሆነ በእምነታችን መጠን የእግዚአብሔርን ቃል እናውጅ። 7ስጦታችን ሌሎችን ማገልገል ከሆነ በትጋት እናገልግል፤ ስጦታችን ማስተማር ከሆነ በሚገባ እናስተምር፤ 8ስጦታችን መምከር ከሆነ እንምከር፤ ስጦታችን መለገሥ ከሆነ ከልብ እንለግሥ፤ ስጦታችን ማስተዳደር ከሆነ በትጋት እናስተዳድር፤ ስጦታችን ርኅራኄ ማድረግ ከሆነ ይህንኑ በደስታ እናድርግ። #1ቆሮ. 12፥4-11።
9ግብዝነት የሌለበት እውነተኛ ፍቅር ይኑራችሁ፤ ክፉውን ነገር ጥሉ፤ መልካሙን ነገር ተከተሉ። 10እርስ በርሳችሁ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ለመከባበርም ተሽቀዳደሙ፤ 11ሳትታክቱ የጋለ መንፈስን ተከትላችሁ ጌታን አገልግሉ። 12በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ጊዜ ታገሡ፤ ሁልጊዜ ጸልዩ። 13አማኞች ወንድሞችን በችግራቸው እርዱ፤ በእንግድነት የሚመጡትንም ተቀበሉ።
14የሚያሳድዱአችሁንም መርቁ፤ መርቁአቸው እንጂ አትርገሙአቸው። #ማቴ. 5፥44፤ ሉቃ. 6፥28። 15ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ። 16እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማምታችሁ ኑሩ፤ ራሳችሁን ከፍ ከማድረግ ይልቅ ትዕቢትን አስወግዳችሁ ከድኾች ጋር በአንድነት ኑሩ፤ በራሳችሁ ዐዋቂዎች ነን አትበሉ። #12፥16 ከድኾች ጋር በአንድነት ኑሩ፦ ወይም “ዝቅተኛ ሥራ ለመሥራት ፈቃደኞች ሁኑ።” #ምሳ. 3፥7።
17በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን ነገር አድርጉ እንጂ፥ ሰዎች ክፉ ነገር ሲያደርጉባችሁ፥ እናንተም መልሳችሁ ክፉ ነገር አታድርጉባቸው። 18የሚቻላችሁ ቢሆን ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር በእናንተ በኩል የሚያስፈልገውን ሁሉ አድርጉ። 19ወዳጆቼ ሆይ! ቊጣን ለእግዚአብሔር ተዉ እንጂ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ “የምበቀልና የበቀልንም ብድራት የምከፍል እኔ ነኝ ይላል ጌታ እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአል። #ዘዳ. 32፥35። 20ስለዚህ ከመበቀል ይልቅ ጠላትህን ቢርበው አብላው፤ ቢጠማውም አጠጣው፤ ይህን ብታደርግ በዕፍረት እሳት ታቃጥለዋለህ። #ምሳ. 25፥21-22። 21ስለዚህ ክፉውን ነገር በመልካም ነገር አሸንፍ እንጂ በክፉ ነገር አትሸነፍ።
Currently Selected:
ወደ ሮም ሰዎች 12: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997