መጽሐፈ ሩት 1
1
ኤቤሜሌክና ቤተሰቡ ወደ ሞአብ አገር ተሰደዱ
1በእስራኤል አገር መሳፍንት ይገዙ በነበረበት ዘመን በሀገሩ ላይ ረሀብ ሆነ፤ ከዚህም የተነሣ በይሁዳ ክፍለ ሀገር ከቤተልሔም አንድ ሰው ከሚስቱና ከሁለት ወንዶች ልጆቹ ጋር ለመኖር ወደ ሞአብ አገር ሄደ። 2የሰውዬው ስም ኤቤሜሌክ፥ የሚስቱ ስም ናዖሚ፥ የሁለቱ ልጆች ስም ማሕሎንና ኬሌዎን ይባል ነበር፤ በትውልዱ ኤፍራታዊ ሆኖ በቤተልሔም ከተማ የሚኖር ነበር፤ እርሱም ከቤተሰቡ ጋር ወደ ሞአብ አገር ሄዶ ኖረ። #1፥2 ናዖሚ፦ በዕብራይስጥ “አስደሳች” ማለት ነው። 3የናዖሚ ባል ኤቤሜሌክ ሞተ፤ ናዖሚም ከሁለቱ ልጆችዋ ጋር ብቻዋን ቀረች፤ 4ልጆችዋም ዖርፋና ሩት የተባሉትን የሞአብ አገር ልጃገረዶች አግብተው ዐሥር ዓመት ያኽል ኖሩ። 5ማሕሎንና ኬሌዎንም ሞቱ፤ ናዖሚም ባልዋንና ልጆችዋን አጥታ ብቻዋን ቀረች።
የናዖሚ ከሩት ጋር ወደ ቤተልሔም መመለስ
6ናዖሚ በሞአብ አገር ሳለች፥ እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ምሕረት እንዳደረገላቸውና ብዙ መከር እንደ ሰጣቸው ሰማች፤ ስለዚህ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ከሞአብ ወደ እስራኤል ለመመለስ ተነሣች። 7ወደ ይሁዳ አገር ለመሄድም አብረው መጓዝ ጀመሩ፤ ነገር ግን በመንገድ ላይ ሳሉ፥ 8ናዖሚ ምራቶችዋን እንዲህ አለቻቸው፤ “እንግዲህ ወደየቤታችሁ ተመለሱና ከእናቶቻችሁ ጋር ኑሩ፤ ለእኔና ለሟቾቹ ባሎቻችሁ መልካም ነገር እንዳደረጋችሁ፥ እንዲሁም እግዚአብሔር ለእናንተ መልካም ነገር ያድርግላችሁ፤ 9እያንዳንዳችሁ እንደገና ባል አግብታችሁ ትዳር እንድትመሠርቱ እግዚአብሔር ይርዳችሁ።”
ከዚህ በኋላ ናዖሚ ለመሰናበት ሳመቻቸው፤ እነርሱ ግን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ። 10“አይሆንም! እኛ ከአንቺ ጋር ወደ ወገኖችሽ እንሄዳለን” አሉአት።
11ናዖሚም እንዲህ አለቻቸው፤ “ልጆቼ ሆይ! እባካችሁ ተመለሱ፤ ከእኔ ጋር ለመሄድ የምትፈልጉት ለምንድነው? ለእናንተ ባሎች የሚሆኑ ልጆች እንደገና መውለድ የምችል ይመስላችኋልን? 12ልጆቼ ሆይ! ወደየቤታችሁ ተመለሱ፤ እኔ ሌላ ባል እንዳላገባ ዕድሜዬ አይፈቅድልኝም፤ ለመሆኑ ለማግባት ተስፋ ቢኖረኝና ዛሬውኑ አግብቼ ልጆች ብወልድስ፥ 13እነርሱ ለአካለ መጠን እስኪደርሱ መጠበቅ ትችላላችሁን? በዚህስ ምክንያት ሌሎች ባሎች ሳታገቡ ትቀራላችሁን? ልጆቼ ሆይ! ይህ የማይሆን ነው፤ እኔን እግዚአብሔር ተቈጥቶኛል፤ በእናንተም ላይ በደረሰው ነገር በጣም አዝኜአለሁ” አለቻቸው።
14እነርሱም እንደገና ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ በዚህ ጊዜ ዖርፋ ዐማትዋን ስማ ተሰናበተች፤ ሩት ግን ከዐማትዋ ላለመለየት ወሰነች። 15ስለዚህ ናዖሚ “ሩት ሆይ! የባልሽ ወንድም ሚስት ወደ ወገኖችዋና ወደ አማልክትዋ ተመልሳለች፤ አንቺም ከእርስዋ ጋር ተመለሺ” አለቻት።
16ሩት ግን እንዲህ አለቻት፦ “ተለይቼሽ እንድመለስ አታስገድጅኝ! አንቺ ወደምትሄጂበት ሁሉ እሄዳለሁ፤ አንቺ በምትኖሪበት እኖራለሁ፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ፥ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፤ 17በምትሞቺበት እሞታለሁ፤ በምትቀበሪበትም እቀበራለሁ፤ ከሞት በቀር ከአንቺ የሚለየኝ ነገር ቢኖር እግዚአብሔር ይፍረድብኝ!”
18ሩት ከእርስዋ ጋር ለመሄድ ቊርጥ ሐሳብ ማድረጓን በተረዳች ጊዜ፥ ናዖሚ ሌላ ነገር አልተናገረችም።
19ስለዚህ ሁለቱም አብረው ወደ ቤተልሔም ተጓዙ፤ ቤተልሔም ሲደርሱም የከተማው ሰዎች ሁሉ ተገረሙ፤ እዚያም ያሉ ሴቶች በመደነቅ “በእርግጥ ይህች ናዖሚ ናትን?” አሉ።
20እርስዋም እንዲህ አለች፦ “ሁሉን የሚችል አምላክ ሕይወቴን መራራ ስላደረገው ‘ማራ’ በሉኝ እንጂ ‘ናዖሚ’ ብላችሁ አትጥሩኝ፤ #1፥20 ማራ፦ በዕብራይስጥ “መራራ ወይም ሬት” ማለት ነው። 21ከዚህ አገር በሄድሁ ጊዜ ብዙ ነገር ነበረኝ፤ እግዚአብሔር ግን ባዶ እጄን መልሶኛል፤ ታዲያ ሁሉን የሚችል አምላክ ሲፈርድብኝና ይህን ሁሉ ችግር ሲያደርስብኝ ‘ናዖሚ’ ብላችሁ ለምን ትጠሩኛላችሁ?”
22እንግዲህ ናዖሚ ከሞአባዊት ምራትዋ ከሩት ጋር ከሞአብ አገር የተመለሰችው በዚህ ሁኔታ ነበር፤ እነርሱ ቤተልሔም በደረሱ ጊዜ የገብስ መከር የሚሰበሰብበት ወቅት መጀመሩ ነበር።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሩት 1: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997