1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 2
2
የሐና ዝማሬ
1 #
ዘዳ. 33፥17፤ 2ሳሙ. 22፥3፤ መዝ. 18፥2፤ 89፥18፤ ኢሳ. 61፥10፤ ሉቃ. 1፥47፤69። ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፦
“ልቤ በጌታ ደስ ይለዋል፥
ቀንዴም በጌታ ከፍ ከፍ ብሏል፤
በማዳንህ ደስ ብሎኛልና፥
አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ።
2 #
2ሳሙ. 22፥3፤ መዝ. 18፥2። እንደ ጌታ ያለ ቅዱስ የለም፥
እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤
አምላካችንን የሚመስልም ዓለት#2፥2 መጠጊያ ምሽግ የለም።
3 #
መዝ. 75፥5-6። እጅግ በመኩራራት አትናገሩ፥
የእብሪትም ቃል ከአፋችሁ አይውጣ፥
ጌታ አምላክ አዋቂ ነውና፥
በእርሱም ሥራዎች ይመዘናሉ።
4 #
ኢሳ. 40፥29። የኀያላን ቀስቶች ተሰበሩ፤
ደካሞች ግን በብርታት ታጥቀዋል።
5 #
ሩት 4፥15፤ ኤር. 15፥9። ጠግበው የነበሩ አጥተው ለእንጀራ ተገዙ፤
ተርበው የነበሩ ግን ከራብ ዐርፈዋል።
መካኒቱ ሰባት ወለደች፥
ብዙ የወለደችው ግን ብቻዋን ቀረች።
6 #
ዘዳ. 32፥39፤ ጦቢ. 4፥19፤ ኢዮብ 5፥11፤ መዝ. 30፥4፤ ጥበ. 16፥13፤ ሉቃ. 1፥52። ጌታ ይገድላል፤ ያድናልም፤
ወደ ሲኦል ያወርዳል፤ ከሲኦልም ያወጣል።
7ጌታ ድሀ ያደርጋል፤ ሀብታምም ያደርጋል፤
ያዋርዳል ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል።
8 #
ኢዮብ 9፥6፤ 38፥6፤ መዝ. 75፥4፤ 104፥5፤ 113፥8፤ 121፥3። ወደ ልዑላንም ደረጃ ከፍ ሊያደርጋቸው፥
የክብርንም ዙፋን ሊያወርሳቸው፥
እርሱ ድኾችን ከትቢያ፥
ምስኪኖችንም ከዐመድ ላይ ያነሣል፤
የምድር መሠረቶች የጌታ ናቸውና፥
በእነርሱ ላይም ዓለምን አኖረ።
9እርሱ የታማኞቹን እግር ይጠብቃል
ሰው በኃይሉ አይበረታምና፥
ኃጥአን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይጣላሉ።
10 #
መዝ. 98፥9። ጌታ! እርሱን የሚቃወሙ ይደቅቃሉ፥
ከሰማይም ያንጐደጉድባቸዋል፥
ጌታ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፥
ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል፥
የመሢሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”
የዔሊ ልጆች ክፉ ሥራ
11ሕልቃናም ወደ ቤቱ ወደ ራማ ሄደ፤ ብላቴናውም በካህኑ በዔሊ ፊት ጌታን ያገለግል ነበር።
12የዔሊም ልጆች ለጌታ ክብር የማይሰጡ ስድ አደጎች ነበሩ። 13#ዘፀ. 29፥27-28፤ ዘሌ. 7፥29-36፤ ዘዳ. 18፥3።የካህናትም ልማድ በሕዝቡ ዘንድ እንዲህ ነበረ፥ ሰው ሁሉ መሥዋዕት ሲያቀርብ ሥጋው በተቀቀለ ጊዜ የካህኑ አገልጋይ ይመጣ ነበረ፥ በእጁም ሦስት ጣት ያለው ሜንጦ ነበረ፥ 14ወደ ድስቱም ወይም ወደ ምንቸቱ ወይም ወደ አፍላሉ ወይም ወደ ቶፋው ይከተው ነበር፤ ሜንጦውም ያወጣውን ሁሉ ካህኑ ለእርሱ ይወስደው ነበር። ይህንንም ወደዚያም በመጡት በእስራኤላውያን ላይ በሴሎ ያደርጉ ነበር። 15ከዚህም ሌላ፥ ስቡን ሳያቃጥሉ የካህኑ አገልጋይ መጥቶ የሚሠዋውን ሰው፦ “ጥሬውን እንጂ የተቀቀለውን ሥጋ ከአንተ አይወስድምና እጠብስለት ዘንድ ለካህኑ ሥጋ ስጠኝ” ይለው ነበር። 16#ዘሌ. 3፥3-5፤ ዘኍ. 18፥17።ሰውየውም፦ “አስቀድሞ ስቡን ያቃጥሉት፥ ከዚያም በኋላ ሰውነትህ ደስ የሚያሰኛትን ያህል ትወስዳለህ” ቢለው፥ እርሱ፦ “አይሆንም፥ አሁን ልትሰጠኝ ይገባል፤ ካልሆነ ግን በግድ እወስዳለሁ!” ይለው ነበር። 17በዚህም ዓይነት የጌታን መሥዋዕት ስላቃለሉ፥ የዔሊ ልጆች ኃጢአት በጌታ ፊት ከፍተኛ ነበር።
ሳሙኤል በሴሎ
18ሳሙኤል ግን ገና ብላቴና ሳለ ከበፍታ የተሠራ ኤፉድ ለብሶ በጌታ ፊት ያገለግል ነበር። 19እናቱም በየዓመቱ ከባሏ ጋር ዓመታዊውን መሥዋዕት ለማቅረብ በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ ትንሽ መደረቢያ ካባ እየሠራች ታመጣለት ነበር። 20ዔሊም ሕልቃናንና ሚስቱን፦ “ለጌታ ስለ ተሳለችው ስጦታ ፋንታ ከዚህች ሴት ጌታ ዘር ይስጥህ” ብሎ ባረካቸው፤ እነርሱም ወደ ቤታቸው ይመለሱ ነበር። 21#1ሳሙ. 3፥19።ጌታም ሐናን አሰበ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ሦስት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ልጆች ወለደች። ብላቴናውም ሳሙኤል በጌታ ፊት አደገ።
ዔሊና ልጆቹ
22ዔሊም እጅግ አረጀ፤ ልጆቹም በእስራኤል ሁሉ ላይ ያደረጉትን ሁሉ፥ በመገናኛውም ድንኳን ደጅ ከሚያገለግሉት ሴቶች ጋር እንደ ተኙ ሰማ። 23እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “ስለ ክፉ ሥራችሁ ከዚህ ሕዝብ ሁሉ ሰምቻለሁና፥ ስለምን እንዲህ ያለ ነገር ታደርጋላችሁ? 24ልጆቼ ሆይ፥ የጌታን ሕዝብ ኃጢአተኛ በማድረጋችሁ ስለ እናንተ የደረሰኝ ወሬ መልካም አይደለምና ይህ አይሆንም። 25ሰውስ በሰው ቢበድል እግዚአብሔር ይታደገዋል፤ ሰው ግን ጌታን ቢበድል ስለ እርሱ የሚለምን ማን ነው?” እነርሱ ግን ጌታ ሊገድላቸው ወድዷልና የአባታቸውን ቃል አልሰሙም። 26#ሉቃ. 2፥52።ብላቴናው ሳሙኤልም እያደገና፥ በጌታም በሰውም ፊት ሞገስ እያገኘ ሄደ።
በዔሊ ቤተሰብ ላይ የተነገረ ትንቢት
27አንድ እግዚአብሔር ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘በግብጽ በፈርዖን ቤት ባርያ ሳሉ ለአባትህ ቤት ተገለጥሁ፤ 28#1ሳሙ. 23፥9፤ 30፥7-8፤ መሳ. 17፥5።ከእስራኤልም ነገድ ሁሉ ካህን ይሆነኝ ዘንድ፥ በመሠዊያዬ ላይ ይሠዋ ዘንድ፥ ዕጣንንም ያጥን ዘንድ ኤፋድንም በፊቴ እንዲለብስ ለእኔ መረጥሁት፤ የእስራኤልንም ልጆች የሚያቀርቡትን የሚቃጠል መሥዋዕት ለአባትህ ቤት ሰጠሁ። 29በማደሪያዬ እንዲያቀርቡት ያዘዝሁትን መሥዋዕቴንና ቁርባኔን ስለምን ረገጣችሁ? ሕዝቤ እስራኤል ካቀረበው ቁርባን ሁሉ ምርጥ ምርጡን በልታችሁ ራሳችሁን በማወፈር፥ ከእኔ ይልቅ ለልጆችህ ስለምን ክብር ሰጠህ?’ 30#2ሳሙ. 22፥26፤ 1ነገ. 2፥27፤ መዝ. 18፥25።ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በእውነት ቤትህ፥ የአባትህም ቤት ለዘለዓለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ፤’ አሁን ግን ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ ከእኔ ይራቅ። 31እነሆ፥ ለቤትህ ሽማግሌ እንዳይገኝ፥ የአንተንም ክንድ፥ የአባትህንም ቤት ክንድ የምሰብርበት ዘመን ይመጣል። 32እነሆ በእስራኤል በረከት ሁሉ በማደሪያዬ ጠላትህን ታያለህ፤ በቤትህም ለዘለዓለም ሽማግሌ አይገኝም። 33በመሠዊያዬ ከምታገለግሉት ከእናንተ መካከል ሳላጠፋ የማስቀረው አንድ ሰው ዐይንህን በእንባ የሚያጠፋና ልብህን የሚያሳዝን ይሆናል፤ የቤተሰብህ አባሎች ሁሉ ግን በሰዎች ሰይፍ ያልቃሉ። 34#1ሳሙ. 4፥11።ይህ በሁለቱ ልጆችህ በሖፍኒና በፊንሐስ ላይ የሚመጣ ለአንተ ምልክት ነው፤ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ። 35የታመነም ካህን ለእኔ አስነሣለሁ፤ እንደ ልቤና እንደ ሐሳቤም የሚያደርግ ይሆናል፤ እኔም የጸና ቤት እሠራለታለሁ፥ ዘመኑንም ሁሉ እኔ በቀባሁት ሰው ፊት ይሄዳል። 36#2ነገ. 23፥9።ከቤትህም የቀረው ሁሉ ይመጣል፤ በፊቱም ሰግዶ፦ ቁራሽ እንጀራ እንድበላ ከካህናት ስፍራ ወደ አንዲቱ፥ እባክህ፥ ስደደኝ ብሎ የዕለት ምግብ ብቻ ለማግኘት ይለምናል።’”
Currently Selected:
1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 2: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ