1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 3
3
የእግዚአብሔር ለሳሙኤል መገለጥ
1ብላቴናው ሳሙኤል ከዔሊ በታች ሆኖ ጌታን ያገለግል ነበር። በዚያም ዘመን የጌታ ቃል ዘወትር የሚሰማ አልነበረም፤ ራእይም አይታይም ነበር። 2በዚያን ጊዜ ዐይኖቹ ከመድከማቸው የተነሣ ማየት የተሳነው ዔሊ አንድ ሌሊት በስፍራው ተኝቶ ነበር። 3#ዘፀ. 27፥20-21።የእግዚአብሔር መብራትም ገና አልጠፋም ነበር፤ ሳሙኤል ደግሞ የጌታ ታቦት ባለበት፥ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ተኝቶ ነበር። 4ጌታም ሳሙኤልን ጠራው፤ ሳሙኤልም፥ “እነሆኝ” አለ፤ 5ወደ ዔሊም ሮጦ በመሄድ፥ “ስለ ጠራኸኝ እነሆ! መጥቻለሁ” አለው። ዔሊ ግን፥ “እኔ አልተጣራሁም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው፤ እርሱም ሄዶ ተኛ። 6ደግሞም እግዚአብሔር፥ “ሳሙኤል!” ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም ተነሣና ወደ ዔሊ ሄዶ፥ “ስለ ጠራኸኝ እነሆ! መጥቻለሁ” አለው። ዔሊም ግን፥ “ልጄ ሆይ፤ እኔ አልተጣራሁም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው። 7በዚያም ጊዜ ሳሙኤል ጌታን ገና አላወቀም ነበር፤ የጌታም ቃል ገና አልተገለጠለትም ነበር። 8ጌታም ሳሙኤልን ለሦስተኛ ጊዜ ጠራው፤ አሁንም ሳሙኤል ተነሥቶ ወደ ዔሊ በመሄድ፥ “ስለ ጠራኸኝ እነሆ! መጥቻለሁ” አለው። ዔሊም በዚህ ጊዜ ሳሙኤልን ይጠራ የነበረው ጌታ መሆኑን ተረዳ። 9ስለዚህም ዔሊ ሳሙኤልን፥ “ሂድና ተኛ፤ ከእንግዲህ ቢጠራህ ግን፥ ‘ጌታ ሆይ፤ አገልጋይህ ይሰማልና ተናገር’ በል” አለው። ሳሙኤልም ወደ ስፍራው ተመልሶ ተኛ። 10ጌታም መጥቶ በዚያ ቆመ፤ ቀደም ሲል እንዳደረገው ሁሉ “ሳሙኤል! ሳሙኤል!” ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም፥ “አገልጋይህ ይሰማልና ተናገር” አለ። 11#2ነገ. 21፥12።ጌታም ሳሙኤልን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፤ የሰሚውን ጆሮ ሁሉ ዝግንን የሚያደርግ አንድ ነገር በእስራኤል ላይ አደርጋለሁ። 12በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በዔሊና በቤተሰቡ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ እፈጽማለሁ። 13#1ሳሙ. 2፥27-36።ልጆቹ አስጸያፊ ነገር ሲያደርጉ እርሱ ባለመከልከሉ፥ ዔሊ በሚያውቀው ኃጢአት ምክንያት በቤተሰቡ ላይ ለዘለዓለም እንደምፈርድ ነግሬው ነበር። 14ስለዚህ ‘የዔሊ ቤት በደል በመሥዋዕትም ሆነ በቁርባን ፈጽሞ አይሰረይም’ ብዬ በዔሊ ቤት ላይ ምያለሁ።”
15ሳሙኤል እስኪ ነጋ ድረስ ተኛ፤ ከዚያም ተነሥቶ የጌታን ቤት በሮች ከፈተ፤ ራእዩንም ለዔሊ መንገር ፈራ፤ 16ዔሊ ግን ሳሙኤልን፥ “ልጄ ሳሙኤል ሆይ” ሲል ጠራው። ሳሙኤልም፥ “እነሆኝ” ሲል መለሰ። 17ዔሊም፥ “እርሱ የነገረህ ነገር ምንድነው? አትደብቀኝ፤ ከነገረህ ውስጥ አንዲቱን እንኳ ብትደብቀኝ እግዚአብሔር እንደዚያው ያድርግብህ፤ ከዚያ የከፋም ያምጣብህ” አለው። 18ስለዚህ ሳሙኤል ምንም ነገር ሳይደብቅ ሁሉንም ነገረው። ዔሊም፥ “እርሱ ጌታ ነው፤ ደስ ያሰኘውን ያድርግ” አለ።
19 #
1ሳሙ. 2፥21። ሳሙኤል አደገ፤ ጌታም ከእርሱ ጋር ነበረና፥ ከሚናገረው ቃል አንዳች በምድር አይወድቅም ነበር። 20#መሳ. 20፥1፤ 2ሳሙ. 3፥10፤ 17፥11፤ 24፥2።ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እስራኤላውያን በሙሉ ሳሙኤል የታመነ የጌታ ነቢይ መሆኑን ዐወቁ። 21ጌታም በሴሎ ይገለጥ ነበር፤ በዚያም ጌታ በቃሉ አማካይነት ራሱን ለሳሙኤል ገለጠ።
Currently Selected:
1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 3: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ