1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች መግቢያ
መግቢያ
ተሰሎንቄ የሮማውያን ጠቅለይ ግዛት ለነበረችው ለመቄዶንያ ዋና ከተማዋ ነበረች። ይህች ከተማ ከመላው ዓለም የመጡ ሕዝቦች የሚኖሩባት፤ ለንግድም አመቺ የሆነችና የራስ ገዝ አስተዳደር የነበራት የወደብ ከተማ ነበረች። የተሰሎንቄ መልእክት ቅዱስ ጳውሎስ ከጻፋቸው መልእክቶች መካከል የመጀመርያው ነው። ቅዱስ ጳውሎስ በ 2 ኛው የስብከት ጉዞው በመንፈስ ቅዱስ ምሪት (የሐዋ. 16፥9-10) ወደ መቄዶንያ ከአጋሮቹ ከሲላስና ከጢሞቴዎስ ጋር በመሄድ በፊልጵስዩስ ወንጌልን ሰበከ (የሐዋ. 16፥11-40)። ከዚያም በደረሰበት ስደት ወደ ተሰሎንቄ መጥቶ ወንጌልን አስተማረ (የሐዋ. 17፥1-4)፤ በዚያም የምትገኘውን ቤተ ክርስትያን መሠረተ። ከአይሁዳውያንና ከአሕዛብ በደረሰበት ተቃውሞ ተሰሎንቄን ለቅቆ ወደ ቤርያ ቢሄድም ተመሳሳይ ተቃውሞ ደርሶበት ወደ አቴና ተጓዘ (የሐዋ. 17፥16-35)። አቴናም ሳለ በተሰሎንቄ ያሉት ክርስትያኖች በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ፥ በመከራና በስደት ውስጥ የእምነታቸውን ጽናት ለማወቅ (1ተሰ. 3፥1-5) እንዲሁም እነርሱን ለማጽናናት ጢሞቴዎስን ወደ ተሰሎንቄ ላከው። ከዚያም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ አቴናን ለቆ ወደ ቆሮንቶስ መጣ። በቆሮንቶስ በነበረም ጊዜ ጢሞቴዮስ ከተሰሎንቄ ቤተ ክርስትያን መልካም ዜናን ወደ እርሱ ይዞለት መጣ (1ተሰ. 3፥6-7።) ቅዱስ ጳውሎስም በዚህ ተነሣሥቶ 50 ዓ.ም. ገደማ የመጀመርያውን የተሰሎንቄ መልእክት ጻፈ።
በተጨማሪም ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ መልእክት የተሰሎንቄ ቤተ ክርስትያን ላላት ጤናማ የመንፈሳዊ ሕይወት ለእግዚአብሔር ምስጋናን አቀረበ፤ የራሱንም ደስ መሰኘት ለመግለጽ፥ ጠንካራም ተቃውሞና መከራ የደረሰባቸውን የተሰሎንቄ ክርስትያኖች በእምነት ለማጽናት ጻፈ። እንዲሁም ይህ መልእክት ቅዱስ ጳውሎስ ከአማኞች ጋር በነበረው ጉርብትናና በአገልግሎቱ እውነተኛነት ላይ የሚነሣን ሐሰተኛ አሉባልታን ሞገተ። በክርስቶስ ዳግም ምጽአትና በሙታን ዳግም ትንሣኤ ላይ የነበረውን የግንዛቤ ስሕተት አረመ። የተሰሎንቄ ክርስትያኖች በግለሰብና በማኅበር እንዴት ክርስትያናዊውን ሕይወት እንደሚኖሩ መመርያ እየሰጠ አበረታታቸው።
የመጀመርያው የተሰሎንቄ መልእክት በአራት ዐበይት ክፍሎች ይከፈላል። አንደኛው ክፍል ምዕራፍ አንድን የሚያጠቃልል ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ቤተ ክርስትያን ያቀረበውን ሰላምታና ምስጋና የያዘ ነው። ሁለተኛው ክፍል ከምዕራፍ ሁለት እስከ ምዕራፍ ሦስት ያለው ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ ከተሰሎንቄ ክርስትያኖች ጋር ቀድሞ የነበረውን የጠበቀ ትስስር የሚያወሳ ነው። ሦስተኛው ክፍል ከምዕራፍ አራት እስከ ምዕራፍ አምስት ቊጥር ሀያ አምስት ያለው ሲሆን በተለያዩ ርእሰ ጕዳዮች ላይ ስለተሰጠ ምክር ይገልጻል። አራተኛው ክፍል ከምዕራፍ አምስት ቊጥር ሀያ ስድስት እስከ ቊጥር ሀያ ስምንት ያለው ሲሆን ጳውሎስ ስላደረገው የስንብት ሰላምታ ይናገራል።
ቅዱስ ጳውሎስ በመጀመርያው የተሰሎንቄ መልእክቱ ውስጥ ስለ ክርስቶስ ዳግም ምጽአትና ስለ ሙታን ትንሣኤ፤ ቅዱሳት መጻሕፍት በመንፈስ ቅዱስ ምሪትና አነሣሽነት ስለ መጻፋቸው፤ ስለ ምሥጢረ ሥላሴም፤ የመዳን አስተምህሮ በክርስቶስ ሕማማት ላይ ስለመመሥረቱና ክርስቶስ አምላክ ስለ መሆኑ ያስተምራል። እንዲሁም ሌሎችን በክርስትና ሕይወት ማነጽ እንደሚገባ፥ ክርስትያኖች ነቅተው መጠበቅ እንዳለባቸው በመልእክቱ ያሳስባል። እርሱም ስለ ፍቅርና ስለ ጸሎት ያስተምራል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ (1፥1)
የጳውሎስ ደስታና ምስጋና (1፥2—3፥13)
የክርስቲያን ሕይወት መመሪያ (4፥1-12)
ስለ ክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት ትምህርት (4፥13—5፥11)
የመጨረሻ ምክር (5፥12-22)
ማጠቃለያ (5፥23-28)
ምዕራፍ
Currently Selected:
1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች መግቢያ: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ