ኦሪት ዘዳግም 23
23
ከእግዚአብሔር ጉባኤ የሚለይ ሁኔታ
1 #
ዘዳ. 27፥20፤ ዘፍ. 9፥20-27፤ 49፥4፤ ዘሌ. 18፥6-19፤ 20፥11፤ ሕዝ. 22፥10። “የተኰላሸ ወይም ብልቱም የተሰለበ ሰው ወደ ጌታ ጉባኤ አይግባ።
2 #
ዘሌ. 21፥16-24። “ከጋብቻ ውጪ የተወለደ ወደ ጌታ ጉባኤ አይግባ፤ እስከ ዐሥር ትውልድ ድረስ እንኳን ቢሆን ወደ ጌታ ጉባኤ አይግባ።
3 #
ዘፍ. 19፥30-38፤ ዘሌ. 18፥6-18። “አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወይም ማናቸውም የእርሱ ዘር፥ እስከ ዐሥር ትውልድ እንኳን ቢሆን ወደ ጌታ ጉባኤ አይግባ። 4#ዘኍ. 22፥1—24፥25፤ ሩት 4፥9-17፤ ዕዝ. 10፥10-44፤ ነህ. 13፥1-3፤23-27።ምክንያቱም ከግብጽ ከወጣችሁ በኋላ በጉዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እህል ውሃ ይዘው አልተቀበሏችሁም፤ በመስጴጦምያ በምትገኘው በፐቶር ይኖር የነበረውን የቢዖርን ልጅ በለዓምም አንተን እንዲረግም በገንዘብ ገዝተውት ነበር። 5ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔር በለዓምን መስማት አልፈለገም፥ ጌታ እግዚአብሔር ወድዶሃልና እርግማኑን በረከት አደረገልህ። 6በዘመንህ ሁሉ ለዘለዓለም ሰላምና ልማት ለእነርሱ አትሻ።
7 #
ዕዝ. 9፥12። “ኤዶማዊ ወንድምህ ነውና አትጸየፈው፥ ግብፃዊውንም በአገሩ ስደተኛ ነበርህና አትጸየፈው። 8#ዘዳ. 2፥2-8፤ 26፥5፤ ዘፍ. 12፥10-20፤ 25፥19-26፤ 36፥6-9፤ 46፥5-7፤ 47፥27።ከእነርሱም በሦስተኛው ትውልድ የሚወለዱ ልጆች ወደ ጌታ ጉባኤ ይግቡ።”
ሰፈርን በንጽሕና ስለ መጠበቅ
9“ጠላቶችህን ልትወጋ በወጣህ ጊዜ ከክፉ ነገር ሁሉ ሰውነትህን ጠብቅ። 10ከእናንተ መካከል ሌሊት ዘር በማፍሰስ የረከሰ ሰው ቢኖር ከሰፈር ወደ ውጭ ይውጣ፥ እዚያው ይቆይ። 11#ዘሌ. 15፥16-17።በመሸም ጊዜ በውኃ ይታጠብ፥ ፀሐይም በገባ ጊዜ ወደ ሰፈር ይመለስ።
12“ለመጸዳጃ የሚሆንህን ቦታ ከሰፈር ውጭ አዘጋጅ። 13ከመሣሪያህም ጋር መቆፈሪያ ያዝ፥ በሜዳም በተቀመጥህ ጊዜ ትምስበታለህ፥ ዞረህም ከአንተ የወጣውን በአፈር ትከድነዋለህ። 14ጌታ እግዚአብሔር ሊያድንህ ጠላቶችህንም በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥ በሰፈርህ መካከል ይሄዳልና ስለዚህ ነውረኛ ነገር እንዳያይብህ፥ ፊቱንም ከአንተ እንዳይመልስ ሰፈርህ የተቀደስ ይሁን።”
ልዩ ልዩ ሕግጋት
15 #
ዘዳ. 1፥30፤ 20፥4፤ 31፥6፤ 8፤ 2ሳሙ. 7፥6። “ከጌታው ኮብልሎ ወደ አንተ የመጣውን ባርያ ለጌታው አሳልፈህ አትስጥ። 16#1ነገ. 2፥39-40።ከደጆችህ በሚመርጣት በአንዲቱ በሚወድዳት ስፍራ ከአንተ ጋር በመካከልህ ይቀመጥ፥ አንተም አታስጨንቀው።
17“ከእስራኤል ወንድ ወይም ሴት የቤተጣዖት አመንዝራ አይሁን። 18#ዘፍ. 38፥21-22፤ 1ነገ. 14፥24፤ 15፥12፤ 22፥46፤ 2ነገ. 23፥7፤ ሆሴዕ 4፥14።ስለ ተሳልኸው ስእለት ሁሉ የአመንዝራይቱን ዋጋና የውሻውን ዋጋ ወደ አምላክህ ወደ ጌታ ቤት አታቅርብ፥ ሁለቱም በጌታ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያጸይፉ ናቸውና።
19 #
ዘዳ. 7፥25-26፤ ኢሳ. 23፥17-18። “ለወንድምህ በወለድ አታበድር፥ የብር ወይም የእህል ወይም የማናቸውንም ነገር ሁሉ ወለድ አትውሰድ። 20#ዘዳ. 15፥1-11፤ 24፥10-13፤ ዘፀ. 22፥25፤ ዘሌ. 25፥35-38፤ ሕዝ. 18፥8፤ 13፤ 17፤ 22፥12፤ ሉቃ. 6፥34-35።ለእንግዳው በወለድ አበድረው፥ ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔር ልትወርሳት በምትገባባት ምድር በሥራህ ሁሉ እንዲባርክህ ለወንድምህ በወለድ አታበድር። 21ለእግዚአብሔር ለጌታ ስእለት በተሳልህ ጊዜ እግዚአብሔር ጌታ ከአንተ ፈጽሞ ይሻዋልና፥ ኃጢአትም ይሆንብሃልና ከመክፈል አታዘገይ። 22#ዘፍ. 28፥20-22፤ ዘኍ. 21፥2-3፤ 30፥1-15፤ መሳ. 11፥30-40፤ 1ሳሙ. 1፥11፤ መዝ. 56፥12-13፤ 66፥13-15፤ 132፥1-5፤ መክ. 5፥3-5።ባትሳል ግን ኃጢአት የለብህም። 23በአፍህ የተናገርኸውን ለእግዚአብሔር ለጌታ በፈቃድህ ተስለሃልና ከከንፈርህ የወጣውን ታደርግ ዘንድ ጠብቅ።
24“ወደ ባልንጀራህ ወይን ቦታ በገባህ ጊዜ እስክትጠግብ ድረስ ከወይኑ ብላ፥ ወደ ዕቃህ ግን ከእርሱ ምንም አትውሰድ። 25ወደ ባልንጀራህ እርሻ በገባህ ጊዜ እሸቱን በእጅህ ቀጥፈህ ብላ፥ ወደ አልታጨደው ወደ ባልንጀራህ እህል ግን ማጭድ አታስገባ።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 23: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ