የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳግም 27

27
በጌባል ተራራ ላይ የቆመ ድንጋይና መሠዊያ
1ሙሴና የእስራኤል ሽማግሌዎች ሕዝቡን እንዲህ ብለው አዘዙ፦ “ዛሬ የማዛችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ ጠብቁ፤ 2ጌታ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ፥ ጥቂት ትልልቅ ድንጋዮችን አቁምና በኖራም ምረጋቸው። 3#ኢያ. 8፥32።የአባቶችህ አምላክ ጌታ በሰጠህ ተስፋ መሠረት፥ ማርና ወተት ወደምታፈሰው ጌታ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን ስትሻገር፥ የዚህን ሕግ ቃላት ሁሉ ጻፍባቸው። 4ዮርዳኖስን እንደ ተሻገርህም፥ ዛሬ ባዘዝሁህ መሠረት እነዚህን ድንጋዮች በጌባል ተራራ ላይ ትከላቸው፤ በኖራም ምረጋቸው። 5#ዘፀ. 20፥24-25፤ ኢያ. 8፥30-31።እዚያም ለጌታ ለእግዚአብሔር የድንጋይ መሠዊያ ሥራ፤ በድንጋዮቹም ላይ ማናቸውንም የብረት መሣሪያ አታሳርፍባቸው። 6ካልተጠረበም ድንጋይ የጌታን የእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ፥ ለጌታ እግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን አቅርብበት። 7የደኅንነትም መሥዋዕት ሠዋበት፥ በዚያም ብላ፤ በጌታም እግዚአብሔር ፊት ደስ ይበልህ። 8የዚህንም ሕግ ቃሎች ሁሉ ግልጽ አድርገህ በድንጋዮቹ ላይ ጻፍ።”
9 # ዘዳ. 26፥17-19። ሙሴና ሌዋውያን ካህናትም ለእስራኤል ሁሉ እንዲህ አሉ፦ “እስራኤል ሆይ፥ ዝም ብለህ አድምጥ! አንተ ዛሬ የጌታ እግዚአብሔር ሕዝብ ሆነሃል። 10ጌታ እግዚአብሔርን ታዘዝ፤ ዛሬ የምሰጥህን ትእዛዙንና ሥርዓቱን ጠብቅ።”
ዐሥራ ሁለቱ መርገሞች
11ሙሴም በዚያኑ ዕለት ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዘ፦ 12#ዘዳ. 11፥29፤ ኢያ. 8፥33-35።“ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዮሴፍና ብንያም ሕዝቡን ለመባረክ በገሪዛን ተራራ ላይ ይቁሙ። 13ለእርግማንም በዔባል ተራራ ላይ መቆም የሚገባቸው ሮቤል፥ ጋድ፥ አሴር፥ ዛብሎን፥ ዳንና ንፍታሌምም ናቸው። 14ሌዋውያን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብለው ይናገሩ፦
15 # ዘፀ. 20፥4፤ 34፥17፤ ዘሌ. 19፥4፤ 26፥1፤ ዘዳ. 4፥15-18፤ 5፥8። “‘በጌታ ዘንድ የተጠላ የሠራተኛ እጅ ሥራን የተቀረጸ ወይም ቀልጦ የተሠራ ምስልን የሚያደርግ፥ በስውርም የሚያቆመው ሰው የተረገመ ይሁን!’
“ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።
16 # ዘፀ. 20፥12፤ ዘዳ. 5፥16። “‘አባቱን ወይም እናቱን የሚያቃልል የተረገመ ይሁን!’
“ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።
17 # ዘዳ. 19፥14። “‘የባልንጀራውን የድንበር ምልክት ከቦታው የሚያንቀሳቅስ የተረገመ ይሁን!’
“ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።
18 # ዘሌ. 19፥14። “‘ዐይነ ስውሩን በተሳሳተ መንገድ የሚመራ፥ የተረገመ ይሁን!’
“ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።
19 # ዘፀ. 22፥21፤ 23፥9፤ ዘሌ. 19፥33፤34፤ ዘዳ. 24፥17፤18። “‘በመጻተኛው፥ አባት በሌለውና በመበለቲቱ ላይ ፍትሕ የሚያዛባ የተረገመ ይሁን!’
“ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።
20 # ዘሌ. 18፥8፤ 20፥11፤ ዘዳ. 22፥30። “‘ከአባቱ ሚስት ጋር የሚተኛ የአባቱን ሚስት ገልቧልና የተረገመ ይሁን!’
“ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።
21 # ዘፀ. 22፥19፤ ዘሌ. 18፥23፤ 20፥15። “‘ከማናቸውም እንስሳ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የተረገመ ይሁን!’
“ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።
22 # ዘሌ. 18፥9፤ 20፥17። “‘የአባቱ ወይም የእናቱ ልጅ ከሆነችው እኅቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን!’
“ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።
23 # ዘሌ. 18፥17፤ 20፥14። “‘ከዐማቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን!’
“ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።
24“‘በድብቅ ባልንጀራውን የሚገድል የተረገመ ይሁን!’
“ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።
25“‘ንጹሕን ሰው ለመግደል ጉቦ የሚቀበል የተረገመ ይሁን!’
“ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።
26 # ገላ. 3፥10። “‘የዚህን ሕግ ቃሎች በመፈጸም የማይጸና የተረገመ ይሁን!’
“ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ