ትንቢተ ኤርምያስ 20:8-9

ትንቢተ ኤርምያስ 20:8-9 መቅካእኤ

በተናገርሁ ቍጥር እጮኻለሁ፤ “ግፍና ጥፋት” ብዬ እጮኻለሁ፤ የጌታ ቃል ቀኑን ሁሉ ስድብና መዘበቻ ሆኖብኛልና። እኔም፦ “የጌታን ስም አላነሣም፥ ከእንግዲህ ወዲህም በስሙ አልናገርም” ብል፥ በአጥንቶቼ ውስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ፤ ደከምሁ፥ መሸከምም አልቻልሁም።