የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 19

19
1ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
2 # መዝ. 8፥1፤ 50፥6፤ 97፥6። ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥
ጠፈርም የእጁን ሥራ ያወራል።
3ቀን ለቀን ንግግርን ታወጣለች፥
ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች።
4ንግግር የለም መናገርም የለም፥
ድምፃቸውም አይሰማም።
5 # ሮሜ 10፥18። ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፥
ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ። በእነርሱም ውስጥ የፀሐይን ድንኳን አደረገ፥
6እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል፥
እንደ አርበኛ በመንገዱ መሮጥ ደስ ይለዋል።
7አወጣጡ ከሰማያት ዳርቻ ነው፥
ዙሪቱም እስከ ዳርቻቸው ነው፥
ከትኩሳቱም የሚሰወር የለም።
8 # መዝ. 12፥7፤ 119። የጌታ ሕግ ፍጹም ነው፥ ነፍስን ይመልሳል፥
የጌታ ምስክር የታመነ ነው፥ የዋሆችን#19፥8 ልምድና እውቀት የሌላቸውን። ጠቢባን ያደርጋል።
9የጌታ ሥርዓት ቅን ነው፥ ልብንም ደስ ያሰኛል፥
የጌታ ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ ዓይንንም ያበራል።
10ጌታን መፍራት ንጹሕ ነው፥ ለዘለዓለም ይኖራል፥
የጌታ ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ናቸው።
11 # ሲራ. 24፥19። ከወርቅና ከክቡር ዕንቁ ይልቅ ይወደዳል፥
ከማርና ከማር ወለላም ይጣፍጣል።
12አገልጋይህ ደግሞ ይጠብቀዋል፥
በመጠበቁም እጅግ ይጠቀማል።
13ስሕተትን ማን ያስተውላታል?
ከተሰወረ ኃጢአት አንጻኝ።
14የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ አገልጋይህን ጠብቅ፥
የዚያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ፥
ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ።
15አቤቱ፥ ዓለቴና ቤዛዬ፥
የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ
በፊትህ ያማረ ይሁን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ