የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 21

21
1ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
2 # መዝ. 63፥12። አቤቱ፥ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል፥
በማዳንህም እንዴት አብዝቶ ሐሤትን ያደርጋል!
3የልቡን ፈቃድ ሰጠኽው፥
የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም።
4በበጎ በረከት ደርሰህለታልና፥
ከንጹሕ ወርቅ የተሠራ ዘውድን በራሱ ላይ አኖርህ።
5 # 1ነገ. 3፥14። ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም፥
ለረጅም ዘመን ለዘለዓለም ዓለም።
6በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው፥
ሞገስንና ግርማን በላዩ አኖርህ።
7የዘለዓለም በረከትን ሰጥተኸዋልና፥
በፊትህም ደስ ታሰኘዋለህ።
8ንጉሥ በጌታ ተማምኖአልና፥
በልዑልም ጽኑ ፍቅር አይናወጥም።
9እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ታገኛቸዋለች፥
ቀኝህም የሚጠሉህን ሁሉ ታገኛቸዋለች።
10በተቈጣህም ጊዜ እንደ እሳት እቶን ታደርጋቸዋለህ፥
ጌታ በቁጣው ይውጣቸዋል፥
እሳትም ትበላቸዋለች።
11ፍሬአቸውን ከምድር
ዘራቸውንም ከሰው ልጆች ታጠፋለህ።
12ክፋትን በአንተ ላይ ዘርግተዋልና፥
የማይቻላቸውንም ምክር አሰቡ።
13ወደ ኋላቸው ትመልሳቸዋለህ፥
ፍላጻን በፊታቸው ላይ ታዘጋጃለህ።
14 # ዘኍ. 10፥35። አቤቱ፥ በኃይልህ ከፍ ከፍ በል፥
ጽናትህንም እናመሰግናለን እንዘምርማለን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ