የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 20

20
የእ​ስ​ራ​ኤል እን​ቢ​ተ​ኛ​ነት
1እን​ዲ​ህም ሆነ፥ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይጠ​ይቁ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰዎች መጡ፤ በፊ​ቴም ተቀ​መጡ። 2የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 3“የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔን ትጠ​ይቁ ዘንድ መጥ​ታ​ች​ኋ​ልን? እኔ ሕያው ነኝ! አል​መ​ል​ስ​ላ​ች​ሁም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 4ነገር ግን በቀ​ልን እበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የሰው ልጅ ሆይ! የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ኀጢ​አት አስ​ታ​ው​ቃ​ቸው። 5እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት በመ​ረ​ጥ​ሁ​በት፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ቤት ዘር በታ​ወ​ቅ​ሁ​በት#ዕብ. “በማ​ል​ሁ​በት” ይላል። ቀን፥ በግ​ብ​ፅም ምድር በተ​ገ​ለ​ጥ​ሁ​ላ​ቸው ጊዜ እጄን አን​ሥቼ፦ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ#ዕብ. “ብዬ በማ​ል​ሁ​ላ​ቸው ጊዜ” ይላል። አል​ኋ​ቸው። 6በዚያ ቀን ከግ​ብፅ ምድር ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ላ​ቸው፥ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው፥ ከም​ድር ሁሉ ወደ​ም​ት​በ​ልጥ ምድር አወ​ጣ​ቸው ዘንድ እጄን አነ​ሣሁ።#ዕብ. “ማል​ሁ​ላ​ቸው” ይላል። 7እኔም፦ ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ ርኵ​ሰ​ቱን ከፊቱ ያስ​ወ​ግድ፤ በግ​ብ​ፅም ጣዖ​ታት አት​ር​ከሱ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ አል​ኋ​ቸው። 8እነ​ርሱ ግን ዐመ​ፁ​ብኝ፤ ይሰ​ሙ​ኝም ዘንድ አል​ወ​ደ​ዱም፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ ርኵ​ሰ​ቱን ከፊቱ አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ የግ​ብ​ጽ​ንም ጣዖ​ታት አል​ተ​ወም፤ በዚ​ህም ጊዜ በግ​ብፅ ምድር መካ​ከል ቍጣ​ዬን እፈ​ጽ​ም​ባ​ቸው ዘንድ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ። 9ነገር ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው በአሉ፥ ከግ​ብ​ጽም ምድር አወ​ጣ​ቸው ዘንድ በፊ​ታ​ቸው በተ​ገ​ለ​ጥ​ሁ​ላ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ ፊት ስሜ እን​ዳ​ይ​ረ​ክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።
10“ከግ​ብ​ፅም ምድር አወ​ጣ​ኋ​ቸው#“ከግ​ብ​ፅም ምድር አወ​ጣ​ኋ​ቸው” የሚ​ለው በግ​እ​ዝና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ወደ ምድረ በዳም አመ​ጣ​ኋ​ቸው። 11ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ሥር​ዐ​ቴ​ንም ሰጠ​ኋ​ቸው፤ ፍር​ዴ​ንም አስ​ታ​ወ​ቅ​ኋ​ቸው። 12የም​ቀ​ድ​ሳ​ቸ​ውም እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያውቁ ዘንድ፥ በእ​ኔና በእ​ነ​ርሱ መካ​ከል ምል​ክት ይሆኑ ዘንድ ሰን​በ​ታ​ቴን ሰጠ​ኋ​ቸው። 13ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት በም​ድረ በዳ በት​እ​ዛዜ ሂዱ አል​ኋ​ቸው፤ አል​ሄ​ዱ​ምም፤ ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው ኖሮ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ት​ንም ሕጌን አፈ​ረሱ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ፈጽ​መው አረ​ከሱ። በዚ​ህም ጊዜ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ቍጣ​ዬን በም​ድረ በዳ አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ። 14ነገር ግን በፊ​ታ​ቸው ባወ​ጣ​ኋ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ ፊት ከሁሉ በላይ የሚ​ሆን ስሜን እን​ዳ​ያ​ረ​ክሱ አደ​ረ​ግሁ። 15ወተ​ትና ማርም ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ከም​ድር ሁሉ ወደ​ም​ታ​ምር ወደ ሰጠ​ኋ​ቸው ምድር እን​ዳ​ላ​ገ​ባ​ቸው በም​ድረ በዳ በእ​ነ​ርሱ ላይ ፈጽሜ እጄን አነ​ሣሁ።#ዕብ. “ማል​ሁ​ላ​ቸው” ይላል። 16ፍር​ዴ​ንም ጥሰ​ዋ​ልና፥ በሥ​ር​ዐ​ቴም አል​ሄ​ዱ​ምና፥ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አር​ክ​ሰ​ዋ​ልና በል​ባ​ቸው ዐሳብ ሄዱ።#ዕብ. “ልባ​ቸው ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ተከ​ት​ሎ​አ​ልና” ይላል። 17ነገር ግን እኔ እንደ አላ​ጠ​ፋ​ቸው፥ በም​ድረ በዳም ፈጽሜ እንደ አል​ጨ​ር​ሳ​ቸው ዐይኔ ራራ​ች​ላ​ቸው።
18“ለል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም በም​ድረ በዳ እን​ዲህ አል​ኋ​ቸው፦ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ልማድ አት​ሂዱ፤ ሥር​ዐ​ታ​ቸ​ው​ንም አት​ጠ​ብቁ፤ በበ​ደ​ላ​ቸ​ውም አንድ አት​ሁኑ፤ አት​ር​ከ​ሱም። 19እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ፤ በት​እ​ዛዜ ሂዱ፤ ፍር​ዴ​ንም ጠብቁ፤ አድ​ር​ጓ​ትም። 20ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ቀድሱ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ምል​ክት ይሁኑ። 21ልጆ​ቻ​ቸው ግን አማ​ረ​ሩኝ፤ ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው ኖሮ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ፍር​ዴን ጠብ​ቀው አላ​ደ​ረ​ጉ​ትም፤ በሥ​ር​ዐ​ቴም አል​ሄ​ዱም፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አረ​ከሱ፤ በዚ​ህም ጊዜ፦ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬ​ንም በም​ድረ በዳ እፈ​ጽ​ም​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ። 22ነገር ግን በፊ​ታ​ቸው ባወ​ጣ​ኋ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ ፊት ከሁሉ የሚ​በ​ል​ጠው ስሜ እን​ዳ​ይ​ረ​ክስ አደ​ረ​ግሁ። 23ደግ​ሞም ወደ አሕ​ዛብ እበ​ት​ና​ቸው ዘንድ፥ በሀ​ገ​ሮ​ችም እበ​ት​ና​ቸው ዘንድ በም​ድረ በዳ በእ​ነ​ርሱ ላይ እጄን አነ​ሣሁ። 24ፍር​ዴን አላ​ደ​ረ​ጉ​ምና፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንም ጥሰ​ዋ​ልና፥ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አር​ክ​ሰ​ዋ​ልና፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ዐሳብ ተከ​ት​ለ​ዋ​ልና። 25ደግ​ሞም መል​ካም ያል​ሆ​ነ​ውን ሥር​ዐት፥ በሕ​ይ​ወት የማ​ይ​ኖ​ሩ​በ​ት​ንም ፍርድ ሰጠ​ኋ​ቸው። 26እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ እን​ዲ​ያ​ውቁ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ማኅ​ፀን የሚ​ከ​ፍ​ተ​ውን ሁሉ በአ​መ​ጡ​ልኝ ጊዜ፥ በመ​ባ​ቸው አረ​ከ​ስ​ኋ​ቸው።
27“ስለ​ዚህ የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዚ​ህም ደግሞ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ በአ​ደ​ረ​ጉት ዐመፅ አስ​ቈ​ጡኝ። 28እሰ​ጣ​ቸ​ውም ዘንድ እጄን ወደ አነ​ሣ​ሁ​ላ​ቸው ምድር አገ​ባ​ኋ​ቸው፤ ከፍ ያለ​ውን ኮረ​ብታ ሁሉ፥ ቅጠ​ላ​ማ​ው​ንም ዛፍ ሁሉ አዩ፤ በዚ​ያም ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ሠዉ፤ በዚ​ያም የሚ​ያ​ስ​ቈ​ጣ​ኝን፤ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን አቀ​ረቡ፤ በዚ​ያም ደግሞ ጣፋ​ጩን ሽታ​ቸ​ውን አደ​ረጉ፤ በዚ​ያም የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን አፈ​ሰሱ። 29እኔም፦ እና​ንተ ወደ እርሱ የም​ት​ሄ​ዱ​በት ከፍታ ምን​ድን ነው? አል​ኋ​ቸው። እስከ ዛሬም ድረስ ስሙ ባማ ተብሎ ተጠ​ር​ቶ​አል። 30ስለ​ዚህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እና​ንተ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ኀጢ​አት ረከ​ሳ​ችሁ፤ አመ​ነ​ዘ​ራ​ችሁ፤ ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ው​ንም ተከ​ተ​ላ​ችሁ። 31ቍር​ባ​ና​ች​ሁን በአ​ቀ​ረ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም በእ​ሳት ባሳ​ለ​ፋ​ችሁ ጊዜ፥ እስከ ዛሬ ድረስ በዐ​ሳ​ባ​ችሁ ሁሉ ረከ​ሳ​ችሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እኔስ እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለ​ሁን? እኔ ሕያው ነኝ! አል​መ​ል​ስ​ላ​ች​ሁም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።#ምዕ. 20 ቍ. 31 ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. ይለ​ያ​ያል። 32ለእ​ና​ን​ተም፦ እንደ አሕ​ዛ​ብና እንደ ምድር ወገ​ኖች እን​ሆ​ና​ለን፤ እን​ጨ​ትና ድን​ጋ​ይም እና​መ​ል​ካ​ለን የሚል ከል​ባ​ችሁ የወጣ ዐሳብ አይ​ፈ​ጸ​ም​ላ​ች​ሁም።
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅጣ​ትና ምሕ​ረት
33“እኔ ሕያው ነኝ! በበ​ረ​ታች እጅና በተ​ዘ​ረ​ጋች ክንድ፥ በፈ​ሰ​ሰ​ችም መዓት እነ​ግ​ሥ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 34ከአ​ሕ​ዛ​ብም ዘንድ አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከተ​በ​ተ​ና​ች​ሁ​ባ​ትም ሀገር ሁሉ በበ​ረ​ታች እጅና በተ​ዘ​ረ​ጋች ክንድ፥ በፈ​ሰ​ሰ​ችም መዓት እሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ። 35ወደ አሕ​ዛ​ብም ምድረ በዳ አመ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ፊት ለፊት ከእ​ና​ንተ ጋር እፋ​ረ​ዳ​ለሁ። 36በግ​ብፅ ምድረ በዳ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ጋር እንደ ተፋ​ረ​ድሁ እን​ዲሁ ከእ​ና​ንተ ጋር እፋ​ረ​ዳ​ለሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 37ከበ​ት​ሬም በታች አሳ​ል​ፋ​ች​ኋ​ለሁ፤ በቍ​ጥ​ርም እወ​ስ​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።#ዕብ. “ወደ ቃል ኪዳ​ንም እስ​ራት አገ​ባ​ች​ኋ​ለሁ” ይላል። 38ከእ​ና​ን​ተም ዘንድ ዐመ​ፀ​ኞ​ች​ንና የበ​ደ​ሉ​ኝን እለ​ያ​ለሁ፤ ከኖ​ሩ​ባ​ትም ምድር አወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ እስ​ራ​ኤል ምድር ግን አይ​ገ​ቡም፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። 39እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ፥ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሁላ​ችሁ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁን ተዉ፤ ከዚህ በኋላ ስሙኝ፤ ቅዱ​ሱን ስሜ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በኀ​ጢ​አ​ታ​ች​ሁና በመ​ባ​ችሁ አታ​ር​ክሱ።
40“በቅ​ዱሱ ተራ​ራዬ፥ ከፍ ባለው በእ​ስ​ራ​ኤል ተራራ ላይ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በዚያ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ሁላ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይገ​ዙ​ል​ኛል፤ በዚ​ያም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ቀዳ​ም​ያ​ታ​ች​ሁን፥ በኵ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ የቀ​ደ​ሳ​ች​ሁ​ት​ንም ነገር ሁሉ እጐ​በ​ኛ​ለሁ። 41ከአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ባወ​ጣ​ኋ​ችሁ ጊዜ፥ ከተ​በ​ተ​ና​ች​ሁ​ባ​ትም ሀገር ሁሉ በሰ​በ​ሰ​ብ​ኋ​ችሁ ጊዜ እንደ ጣፋጭ ሽታ እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ፊት እቀ​ደ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ። 42ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም እሰ​ጣት ዘንድ እጄን ወደ አነ​ሣ​ሁ​ላ​ቸው ምድር ወደ እስ​ራ​ኤል ሀገር ባገ​ባ​ኋ​ችሁ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። 43በዚ​ያም የረ​ከ​ሳ​ች​ሁ​ባ​ትን መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና ሥራ​ች​ሁን ሁሉ ታስ​ባ​ላ​ችሁ፤ በፊ​ታ​ች​ሁም አይ​ታ​ችሁ ስለ ሠራ​ች​ሁት ክፋ​ታ​ችሁ ሁሉ ታፍ​ራ​ላ​ችሁ። 44የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እንደ ክፉ መን​ገ​ዳ​ች​ሁና እንደ ርኩስ ሥራ​ችሁ ሳይ​ሆን ስለ ስሜ ስል በሠ​ራ​ሁ​ላ​ችሁ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
45የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፤ 46“የሰው ልጅ ሆይ! ፊት​ህን ወደ ቴማን#ዕብ. “ደቡብ” ይላል። አቅና፤ ወደ ዳሮ​ምም#ዕብ. “ደቡብ” ይላል። ተመ​ል​ከት፤ በና​ጌ​ብም ምድረ በዳ ዱር ንጉሥ ላይ ትን​ቢት ተና​ገር። 47ለና​ጌ​ብም ዱር እን​ዲህ በለው፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በአ​ንተ ውስጥ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በው​ስ​ጥ​ህም ያለ​ውን የለ​መ​ለ​መ​ው​ንና የደ​ረ​ቀ​ውን ዛፍ ሁሉ ይበ​ላል፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም ነበ​ል​ባል አይ​ጠ​ፋም፤ ከደ​ቡ​ብም ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ ፊት ሁሉ ይቃ​ጠ​ል​በ​ታል። 48እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ነ​ደ​ድ​ሁት ሥጋ ለባሽ ሁሉ ያያል፥ እር​ሱም አይ​ጠ​ፋም። 49እኔም፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ይህ አይ​ሁን አልሁ፤ እነ​ርሱ ግን፦ ይህ የነ​ገ​ረን ምሳሌ አይ​ደ​ለ​ምን? ይሉ​ኛል።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ