ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 48

48
ያዕ​ቆብ ኤፍ​ሬ​ም​ንና ምና​ሴን መባ​ረኩ
1ከዚ​ህም ነገር በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ “እነሆ፥ አባ​ታ​ችን ደከመ” ብለው ለዮ​ሴፍ ነገ​ሩት፤ እር​ሱም ሁለ​ቱን ልጆ​ቹን ምና​ሴ​ንና ኤፍ​ሬ​ምን ይዞ ሄደ። 2ለያ​ዕ​ቆ​ብም፥ “እነሆ፥ ልጅህ ዮሴፍ መጥ​ቶ​ል​ሃል” ብለው ነገ​ሩት፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ተጠ​ነ​ካ​ከረ፤ በአ​ል​ጋ​ውም ላይ ተቀ​መጠ። 3ያዕ​ቆብ ዮሴ​ፍን አለው፥ “አም​ላኬ በከ​ነ​ዓን ምድር በሎዛ ተገ​ለ​ጠ​ልኝ፤ ባረ​ከ​ኝም። 4እን​ዲ​ህም አለኝ፦ እነሆ፥ አበ​ዛ​ሃ​ለሁ፤ አባ​ዛ​ሃ​ለ​ሁም፤ ለብ​ዙም ሕዝብ ጉባኤ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ ይህ​ች​ንም ምድር ለአ​ንተ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ርስት ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ። 5አሁ​ንም እኔ ወደ አንተ ከመ​ም​ጣቴ በፊት በግ​ብፅ ምድር የተ​ወ​ለ​ዱ​ልህ ሁለቱ ልጆ​ችህ ለእኔ ይሁኑ፤ ኤፍ​ሬ​ምና ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤ​ልና እንደ ስም​ዖን ናቸው። 6ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ የም​ት​ወ​ል​ዳ​ቸው ልጆች ለአ​ንተ ይሁኑ፤ በር​ስ​ታ​ቸው በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ስም ይጠሩ። 7እኔም ከሶ​ርያ መስ​ጴ​ጦ​ምያ በመ​ጣሁ ጊዜ፥ ወደ ኤፍ​ራታ ለመ​ግ​ባት ጥቂት ቀር​ቶኝ በፈ​ረስ መጋ​ለ​ቢ​ያው መን​ገድ ሳለሁ፥ ራሔል በከ​ነ​ዓን ምድር ሞተ​ች​ብኝ፤ በዚ​ያም በኤ​ፍ​ራታ ወደ ፈረስ መጋ​ለ​ቢያ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ላይ ቀበ​ር​ኋት፤ እር​ስ​ዋም ቤተ ልሔም ናት።”
8እስ​ራ​ኤ​ልም የዮ​ሴ​ፍን ልጆች ለይቶ፥ “እነ​ዚህ ምኖ​ችህ ናቸው?” አለው። 9ዮሴ​ፍም ለአ​ባቱ ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ የሰ​ጠኝ ልጆች ናቸው” አለው። ያዕ​ቆ​ብም፥ “እባ​ር​ካ​ቸው ዘንድ ወደ እኔ አቅ​ር​ብ​ልኝ” አለው። 10የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዐይ​ኖች ከሽ​ም​ግ​ልና የተ​ነሣ ከብ​ደው ነበር፤ ማየ​ትም አይ​ች​ልም ነበር፤ ወደ እር​ሱም አቀ​ረ​ባ​ቸው፤ ሳማ​ቸ​ውም፤ አቀ​ፋ​ቸ​ውም። 11እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “ከፊ​ትህ አል​ተ​ለ​የ​ሁም፤#ዕብ. “ፊት​ህን አያ​ለሁ ብዬ አላ​ሰ​ብ​ሁም ነበር” ይላል። እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘር​ህን ደግሞ አሳ​የኝ” አለው። 12ዮሴ​ፍም ከጕ​ል​በቱ ፈቀቅ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ ወደ ምድ​ርም በግ​ን​ባሩ ሰገደ። 13ዮሴ​ፍም ሁለ​ቱን ልጆ​ቹን ወሰደ፤ ኤፍ​ሬ​ም​ንም በቀኙ በእ​ስ​ራ​ኤል ግራ፥ ምና​ሴ​ንም በግ​ራው በእ​ስ​ራ​ኤል ቀኝ አቆ​ማ​ቸው፤ ወደ አባ​ቱም አቀ​ረ​ባ​ቸው። 14እስ​ራ​ኤ​ልም ቀኝ እጁን ዘር​ግቶ በኤ​ፍ​ሬም ራስ ላይ አኖ​ረው፤ እር​ሱም ታናሽ ነበረ፤ ግራ​ው​ንም በም​ናሴ ራስ ላይ አኖረ፤ እጆ​ቹ​ንም አስ​ተ​ላ​ለፈ።#ዕብ. “ምናሴ በኵር ነበ​ርና” የሚል ይጨ​ም​ራል። 15ያዕ​ቆ​ብም ባረ​ካ​ቸው፤#ዕብ. “ያዕ​ቆብ ዮሴ​ፍን ባረከ” ይላል። እን​ዲ​ህም አለ፥ “አባ​ቶች አብ​ር​ሃ​ምና ይስ​ሐቅ በፊቱ ደስ ያሰ​ኙት እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከታ​ና​ሽ​ነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመ​ገ​በኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ 16ከከፉ ነገር ሁሉ የአ​ዳ​ነኝ መል​አክ እርሱ እነ​ዚ​ህን ብላ​ቴ​ኖች ይባ​ርክ፤ ስሜም፥ የአ​ባ​ቶች የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐ​ቅም ስም በእ​ነ​ርሱ ይጠራ፤ በም​ድር ላይ ይብዙ፤ የብዙ ብዙም ይሁኑ፤” 17ዮሴ​ፍም አባቱ ቀኝ እጁን በኤ​ፍ​ሬም ራስ ላይ ጭኖ በአየ ጊዜ ከባድ ነገር ሆነ​በት፤ ዮሴ​ፍም የአ​ባ​ቱን እጅ በም​ናሴ ራስ ላይ ይጭ​ነው ዘንድ ከኤ​ፍ​ሬም ራስ ላይ አነ​ሣው። 18ዮሴ​ፍም አባ​ቱን፥ “አባቴ ሆይ፥ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ በኵሩ ይህ ነውና ቀኝ​ህን በራሱ ላይ አድ​ርግ” አለው። 19አባ​ቱም እንቢ አለ፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አው​ቃ​ለሁ ልጄ ሆይ፥ አው​ቃ​ለሁ፤ ይህም ደግሞ ሕዝብ ይሆ​ናል፤ ታላ​ቅም ይሆ​ናል፤ ነገር ግን ታናሽ ወን​ድሙ ከእ​ርሱ ይበ​ል​ጣል፤ ዘሩም ብዙ ሕዝብ ይሆ​ናል።” 20በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ብሎ ባረ​ካ​ቸው፥ “በእ​ና​ንተ እስ​ራ​ኤል#አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “በእ​ና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ይመ​ሰ​ገ​ናል” ይላል። እን​ዲህ ተብሎ ይባ​ረ​ካል፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ኤፍ​ሬ​ምና እንደ ምናሴ ይባ​ር​ክህ።” ኤፍ​ሬ​ም​ንም ከም​ናሴ ፊት አደ​ረ​ገው። 21እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “እነሆ፥ እኔ እሞ​ታ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ና​ንተ ጋር ይሆ​ናል፤ ወደ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ምድር ይመ​ል​ሳ​ች​ኋል፤ 22እኔም ከአ​ሞ​ራ​ው​ያን እጅ በሰ​ይ​ፌና በቀ​ስቴ የወ​ሰ​ድ​ሁ​ትን ምርኮ ለአ​ንተ ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ የተ​ሻ​ለ​ውን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” አለው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ