የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 15

15
1ከጊ​ዜም በኋላ በስ​ንዴ መከር ጊዜ ሶም​ሶን የፍ​የል ጠቦት ይዞ ሚስ​ቱን ሊጠ​ይቅ ሄደና፥ “ወደ ጫጕላ ቤት ወደ ሚስቴ ልግባ” አለ፤ አባቷ ግን እን​ዳ​ይ​ገባ ከለ​ከ​ለው። 2አባ​ቷም፥ “ፈጽ​መህ ጠላ​ህ​ዋት ያልህ መስ​ሎኝ ለሚ​ዜህ አጋ​ባ​ኋት፤ ታናሽ እኅቷ ከእ​ር​ስዋ ይልቅ የተ​ዋ​በች አይ​ደ​ለ​ች​ምን? እባ​ክህ በእ​ር​ስዋ ፋንታ አግ​ባት” አለው። 3ሶም​ሶ​ንም፥ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ ክፉ ባደ​ርግ እኔ ንጹሕ ነኝ” አላ​ቸው። 4ሶም​ሶ​ንም ሄዶ ሦስት መቶ ቀበ​ሮ​ችን ያዘ፤ ችቦም ወስዶ ሁለት ሁለ​ቱን ቀበ​ሮ​ዎች በጅ​ራ​ታ​ቸው አሰረ፤ በሁ​ለ​ቱም ጅራ​ቶች መካ​ከል አንድ ችቦ አደ​ረገ። 5ችቦ​ው​ንም አን​ድዶ በቆ​መው በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እህል መካ​ከል ሰደ​ዳ​ቸው፤ ነዶ​ው​ንም፥ ክም​ሩ​ንም፥ የቆ​መ​ዉ​ንም እህል፥ ወይ​ኑ​ንም፥ ወይ​ራ​ዉ​ንም አቃ​ጠለ። 6ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ “ይህን ያደ​ረገ ማን ነው?” አሉ። እነ​ር​ሱም፥ “ሚስ​ቱን ወስዶ ለሚ​ዜው አጋ​ብ​ቶ​በ​ታ​ልና የቴ​ም​ና​ታ​ዊዉ አማች ሶም​ሶን ነው” አሉ​አ​ቸው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ወጥ​ተው የአ​ባ​ቷን ቤትና እር​ስ​ዋን አባ​ቷ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠሉ። 7ሶም​ሶ​ንም አላ​ቸው- “ይህን ብታ​ደ​ር​ጉም ደስ አይ​ለ​ኝም፤ በቀሌ ከአ​ንድ ሰው ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ሁላ​ች​ሁ​ንም እበ​ቀ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ አር​ፋ​ለሁ።” 8ሶም​ሶ​ንም ጭን ጭና​ቸ​ውን ብሎ በታ​ላቅ አገ​ዳ​ደል መታ​ቸው፤ ወር​ዶም ኢጣም በም​ት​ባል ዋሻ በወ​ንዝ ዳር ተቀ​መጠ።
ሶም​ሶን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ድል እን​ዳ​ደ​ረገ
9ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ወጡ፤ በይ​ሁ​ዳም ሰፈሩ፤ የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ንት በተ​ባለ ቦታም ተበ​ታ​ት​ነው ተቀ​መጡ። 10የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሁሉ፥ “በእኛ ላይ የወ​ጣ​ች​ሁት ለም​ን​ድን ነው?” አሉ። እነ​ር​ሱም፥ “ሶም​ሶ​ንን ልና​ስር፥ እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ብ​ንም ልና​ደ​ር​ግ​በት መጥ​ተ​ናል” አሏ​ቸው። 11ከይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሦስት ሺህ የሚ​ያ​ህሉ በኢ​ጣም ዓለት ወዳ​ለው ዋሻ ወር​ደው ሶም​ሶ​ንን፥ “ገዢ​ዎ​ቻ​ችን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እን​ደ​ሆኑ አታ​ው​ቅ​ምን? ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ይህ ምን​ድን ነው?” አሉት። ሶም​ሶ​ንም፥ “እን​ዳ​ደ​ረ​ጉ​ባ​ችሁ እን​ዲሁ አደ​ረ​ግ​ሁ​ባ​ቸው” አላ​ቸው። 12እነ​ር​ሱም፥ “አስ​ረን በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ አሳ​ል​ፈን ልን​ሰ​ጥህ መጥ​ተ​ናል” አሉት። ሶም​ሶ​ንም፥ “እና​ንተ እን​ዳ​ት​ገ​ድ​ሉኝ ማሉ​ልኝ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም አሳ​ል​ፋ​ችሁ ስጡኝ፤ እና​ንተ ግን ከእኔ ጋር አትዋጉ” አላ​ቸው። 13እነ​ር​ሱም፥ “በገ​መድ አስ​ረን በእ​ጃ​ቸው አሳ​ል​ፈን እን​ሰ​ጥ​ሃ​ለን እንጂ አን​ገ​ድ​ል​ህም” ብለው ማሉ​ለት። በሁ​ለ​ትም አዲስ ገመድ አስ​ረው ከዓ​ለቱ ውስጥ አወ​ጡት።
14የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ንት ወደ ተባለ ቦታም ደረሰ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ደን​ፍ​ተው ተቀ​በ​ሉት፤ ወደ እር​ሱም ሮጡ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ አደረ፤ በክ​ን​ዱም ያሉ እነ​ዚያ ገመ​ዶች በእ​ሳት ላይ እንደ ተጣለ ገለባ ሆኑ፤ ማሰ​ሪ​ያ​ውም ከክ​ንዱ ተፈታ፤ 15የወ​ደቀ የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ን​ት​ንም በመ​ን​ገድ አገኘ። እጁ​ንም ዘር​ግቶ ወሰ​ደው፤ በእ​ር​ሱም አንድ ሺህ ሰው ገደለ። 16ሶም​ሶ​ንም፥ “በአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ንት ክምር በክ​ምር ላይ አድ​ር​ጌ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ንት አንድ ሺህ ሰው ገድ​ያ​ለ​ሁና” አለ። 17መና​ገ​ሩ​ንም በፈ​ጸመ ጊዜ መን​ጋ​ጋ​ውን ከእጁ ጣለ፤ የዚ​ያ​ንም ስፍራ ስም “ቀትለ አጽመ መን​ሰክ” ብሎ ጠራው። 18እር​ሱም እጅግ ተጠ​ምቶ ነበ​ርና፥ “አንተ ይህ​ችን ታላቅ ማዳን በባ​ሪ​ያህ እጅ ሰጥ​ተ​ሃል፤ አሁ​ንም በጥም እሞ​ታ​ለሁ፤ ባል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትም እጅ እወ​ድ​ቃ​ለሁ” ብሎ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ። 19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የዚ​ያ​ችን የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ንት ስን​ጥ​ቃት ከፈተ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ውኃ ወጣ፤ እር​ሱም ጠጣ፤ ነፍ​ሱም ተመ​ለ​ሰች፤ ከውኃ ጥሙም ዐረፈ። ስለ​ዚ​ህም የዚያ ቦታ ስም እስከ ዛሬ ድረስ “ነቅዐ አጽመ መን​ሰክ” ተብሎ ተጠራ። 20በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ዘመን እስ​ራ​ኤ​ልን ሃያ ዓመት ገዛ​ቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ