የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 19

19
አንድ ሌዋ​ዊና ዕቅ​ብቱ
1በዚ​ያም ዘመን ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም። በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ማዶ የተ​ቀ​መጠ አንድ ሌዋዊ ሰው ነበረ፤ ከይ​ሁዳ ቤተ ልሔ​ምም ዕቅ​ብት አገባ። 2ዕቅ​ብ​ቱም ተጣ​ላ​ችው፤ ትታ​ውም ወደ አባቷ ቤት ወደ ይሁዳ ቤተ ልሔም ሄደች፤ በዚ​ያም አራት ወር ተቀ​መ​ጠች። 3ባል​ዋም ተነሣ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ዕርቅ ሽቶ ወደ እርሱ ሊመ​ል​ሳት ፍለ​ጋ​ዋን ተከ​ትሎ ሄደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አንድ ብላ​ቴና፥ ሁለ​ትም አህ​ዮች ነበሩ። እር​ሱም ወደ አባቷ ቤት ሄደ፤ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት ባየው ጊዜ ደስ ብሎት ተቀ​በ​ለው። 4የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት አማቱ ወደ ቤቱ አገ​ባው፤ በቤ​ቱም ሦስት ቀን ተቀ​መጠ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ በዚ​ያም አደሩ። 5በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ቀን ማል​ደው ተነሡ፤ እር​ሱም ለመ​ሄድ ተነሣ፤ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት አማ​ቹን፥ “ሰው​ነ​ት​ህን በቁ​ራሽ እን​ጀራ አበ​ርታ፤ ከዚ​ያም በኋላ ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ” አለው። 6ሁለ​ቱም በአ​ንድ ላይ ተቀ​መጡ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት ሰው​ዬ​ውን፥ “ዛሬ ደግሞ ከዚህ እደር ልብ​ህ​ንም ደስ ይበ​ለው” አለው። 7ሰው​ዬ​ውም ሊሄድ ተነሣ፤ አማቱ ግን ግድ አለው፤ ዳግ​መ​ኛም በዚያ አደረ። 8በአ​ም​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ለመ​ሄድ ማልዶ ተነሣ፤ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት፥ “እህል ብላ፤ ከዚ​ህም በኋላ ፀሐይ ሲበ​ርድ ትሄ​ዳ​ለህ” አለው። ሁለ​ቱም በሉ፤ ጠጡም። 9ሰው​ዬ​ውም ከዕ​ቅ​ብ​ቱና ከብ​ላ​ቴ​ናው ጋር ለመ​ሄድ ተነሣ፤ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪቱ አባት አማ​ቱም፥ “እነሆ፥ መሽ​ት​ዋል፤ ፀሐ​ዩም ሊጠ​ልቅ ደር​ሷል፤ ዛሬም እዚህ እደር፤ በዚ​ህም ተቀ​መጥ፤ ልብ​ህም ደስ ይበ​ለው፤ በጥ​ዋ​ትም መን​ገ​ዳ​ች​ሁን ትገ​ሠ​ግ​ሣ​ላ​ችሁ፤ ወደ ቤት​ህም ትገ​ባ​ለህ” አለው።
10ሰው​ዬው ግን በዚያ ሌሊት ለማ​ደር አል​ፈ​ቀ​ደም፤ ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወደ ተባ​ለ​ችው ወደ ኢያ​ቡስ ፊት ለፊት ደረሰ። ከእ​ር​ሱም ጋር ሁለት የተ​ጫኑ አህ​ዮች ነበሩ፤ ዕቅ​ብ​ቱም ከእ​ርሱ ጋር ነበ​ረች። 11በኢ​ያ​ቡ​ስም አን​ጻር ገና ሳሉ ፀሐ​ይዋ ተቈ​ለ​ቈ​ለች፤ ብላ​ቴ​ና​ውም ጌታ​ውን፥ “ና፤ ወደ​ዚ​ህች ወደ ኢያ​ቡ​ሳ​ው​ያን ከተማ፥ እባ​ክህ እና​ቅና፤ በእ​ር​ስ​ዋም እን​ደር” አለው። 12ጌታ​ውም፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወዳ​ል​ሆ​ነች ወደ እን​ግዳ ከተማ አን​ገ​ባም፤ እኛ ወደ ገባ​ዖን እን​ለፍ” አለው። 13ብላ​ቴ​ና​ው​ንም፥ “ና፤ ከእ​ነ​ዚህ ስፍራ ወደ አንዱ እን​ቅ​ረብ፤ በገ​ባ​ዖን ወይም በራማ እን​ደር” አለው። 14አል​ፈ​ውም ሄዱ፤ የብ​ን​ያ​ምም ነገድ በም​ት​ሆ​ነው በገ​ባ​ዖን አጠ​ገብ ሳሉ ፀሐይ ገባ​ች​ባ​ቸው። 15በገ​ባ​ዖ​ንም ገብ​ተው ያድሩ ዘንድ ወደ​ዚያ አቀኑ። ገብ​ተ​ውም በከ​ተ​ማው አደ​ባ​ባይ በተ​ቀ​መጡ ጊዜ ወደ ቤቱ የሚ​ያ​ስ​ገ​ባ​ቸ​ውና የሚ​ያ​ሳ​ድ​ራ​ቸው አል​ነ​በ​ረም።
16እነ​ሆም አንድ ሽማ​ግሌ ከእ​ር​ሻው ሥራ ወደ ማታ መጣ፤ ይህም ሰው ከተ​ራ​ራ​ማው ከኤ​ፍ​ሬም ሀገር ነበረ፤ በገ​ባ​ዖ​ንም በእ​ን​ግ​ድ​ነት ተቀ​ምጦ ነበር፤ የዚያ ሀገር ሰዎች ግን የብ​ን​ያም ልጆች ነበሩ። 17ዐይ​ኑ​ንም አን​ሥቶ መን​ገ​ደ​ኛ​ውን በከ​ተ​ማው አደ​ባ​ባይ አየ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ውም፥ “ወዴት ትሄ​ዳ​ለህ? ከወ​ዴ​ትስ መጣህ?” አለው። 18እር​ሱም፥ “እኛ ከይ​ሁዳ ቤተ ልሔም ወደ ተራ​ራ​ማው ወደ ኤፍ​ሬም ሀገር ማዶ እና​ል​ፋ​ለን፤ እኔ ከዚያ ነኝ፤ ወደ ይሁዳ ቤተ ልሔ​ምም ሄጄ ነበር፥ አሁ​ንም ወደ ቤቴ እሄ​ዳ​ለሁ፤ በቤ​ቱም የሚ​ያ​ሳ​ድ​ረኝ አጣሁ፤ 19ለአ​ህ​ዮ​ቻ​ችን ገለ​ባና ገፈራ አለን፤ ለእ​ኔና ለገ​ረ​ድህ ከባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህም ጋር ላለው ብላ​ቴና እን​ጀ​ራና የወ​ይን ጠጅ አለን፤ ከሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገን ሁሉ አን​ዳ​ችም አላ​ጣ​ንም” አለው። 20ሽማ​ግ​ሌ​ውም ሰው፥ “ሰላም ከአ​ንተ ጋር ይሁን፤ የም​ት​ሻ​ው​ንም ሁሉ እኔ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ በአ​ደ​ባ​ባይ ግን አት​ደር” አለው። 21ወደ ቤቱም አስ​ገ​ባው፤ ለአ​ህ​ዮ​ቹም ገፈራ ጣለ​ላ​ቸው፤ እግ​ራ​ቸ​ው​ንም ታጠቡ፤ በሉም፤ ጠጡም።
የኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎን ሰዎች በደል
22ሰው​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ደስ ባሰኙ ጊዜ የኃ​ጥ​ኣን ልጆች የሆኑ የከ​ተ​ማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ፤ በሩ​ንም ይደ​በ​ድቡ ነበር፤ ባለ​ቤ​ቱ​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ውን ሰው፥ “ወደ ቤትህ የገ​ባ​ውን ሰው እን​ድ​ን​ደ​ር​ስ​በት አው​ጣ​ልን” አሉት። 23ባለ​ቤ​ቱም ሽማ​ግ​ሌው ወደ እነ​ርሱ ወጥቶ፥ “ወን​ድ​ሞቼ ሆይ! ይህን ክፉ ነገር ታደ​ርጉ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ች​ሁም፤ ይህ ሰው ወደ ቤቴ ከገባ በኋላ እን​ደ​ዚህ ያለ ስን​ፍና አት​ሥሩ። 24ድን​ግል ልጄና የእ​ር​ሱም ዕቅ​ብት እነሆ፥ አሉ፤ አሁ​ንም አወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አዋ​ር​ዱ​አ​ቸው፤ በዐ​ይ​ና​ች​ሁም ፊት ደስ የሚ​ላ​ች​ሁን አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ ነገር ግን በዚህ ሰው ላይ እን​ደ​ዚህ ያለ የስ​ን​ፍና ሥራ አታ​ድ​ርጉ” አላ​ቸው። 25ሰዎቹ ግን ሊሰ​ሙት አል​ፈ​ቀ​ዱም፤ ሰው​የ​ውም ዕቅ​ብ​ቱን ይዞ ወደ እነ​ርሱ አወ​ጣ​ላ​ቸው፤ አዋ​ረ​ድ​ዋ​ትም፤ ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ እስ​ኪ​ነጋ ድረስ አመ​ነ​ዘ​ሩ​ባት፤ ጎህም በቀ​ደደ ጊዜ ለቀ​ቁ​አት። 26ሴቲ​ቱም ማለዳ መጣች፤ ጌታ​ዋም ባለ​በት በሰ​ው​ዬው ቤት ደጅ ወድቃ እስ​ኪ​ነጋ ድረስ በዚያ ቀረች።
27ጌታ​ዋም ማለዳ ተነሣ፤ የቤ​ቱ​ንም ደጅ ከፈተ፤ መን​ገ​ዱ​ንም ለመ​ሄድ ወጣ፤ እነ​ሆም፥ ዕቅ​ብቱ ሴት በቤቱ ደጃፍ ላይ ወድቃ፥ እጆ​ች​ዋም በመ​ድ​ረኩ ላይ ወድ​ቀው አገ​ኛት። 28እር​ሱም፥ “ተነሺ እን​ሂድ” አላት፤ እር​ስዋ ግን ሞታ ነበ​ርና አል​መ​ለ​ሰ​ችም፤ በዚያ ጊዜም በአ​ህ​ያው ላይ ጫናት፤ ተነ​ሥ​ቶም ወደ ስፍ​ራው ተመ​ለሰ። 29ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ ካራ አነሣ፤ ዕቅ​ብ​ቱ​ንም ይዞ ከአ​ጥ​ን​ቶ​ችዋ መለ​ያያ ላይ ለዐ​ሥራ ሁለት ቈራ​ርጦ ወደ እስ​ራ​ኤል ሀገር ሁሉ ሰደደ። 30ከዚ​ያም በኋላ ያያት ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ ከወጡ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ዲህ ያለ ነገር የሆ​ነ​በት ጊዜ የለም፤ የታ​የ​በ​ትም ጊዜ የለም፤” #ቀጣዩ በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።ያም ሰው እነ​ዚ​ያን የላ​ካ​ቸ​ውን ሰዎች እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰዎች እን​ዲህ በሏ​ቸው፦ እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ ከወጡ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ እን​ዲህ የሆ​ነ​በት ጊዜ አለን? እና​ንተ ተመ​ካ​ከ​ሩ​በት፤ የሚ​በ​ጀ​ው​ንም ተነ​ጋ​ገሩ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ