መጽሐፈ መሳፍንት 19
19
አንድ ሌዋዊና ዕቅብቱ
1በዚያም ዘመን ለእስራኤል ንጉሥ አልነበራቸውም። በተራራማውም በኤፍሬም ሀገር ማዶ የተቀመጠ አንድ ሌዋዊ ሰው ነበረ፤ ከይሁዳ ቤተ ልሔምም ዕቅብት አገባ። 2ዕቅብቱም ተጣላችው፤ ትታውም ወደ አባቷ ቤት ወደ ይሁዳ ቤተ ልሔም ሄደች፤ በዚያም አራት ወር ተቀመጠች። 3ባልዋም ተነሣ፤ ከእርስዋም ዕርቅ ሽቶ ወደ እርሱ ሊመልሳት ፍለጋዋን ተከትሎ ሄደ፤ ከእርሱም ጋር አንድ ብላቴና፥ ሁለትም አህዮች ነበሩ። እርሱም ወደ አባቷ ቤት ሄደ፤ የብላቴናዪቱም አባት ባየው ጊዜ ደስ ብሎት ተቀበለው። 4የብላቴናዪቱም አባት አማቱ ወደ ቤቱ አገባው፤ በቤቱም ሦስት ቀን ተቀመጠ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ በዚያም አደሩ። 5በአራተኛውም ቀን ማልደው ተነሡ፤ እርሱም ለመሄድ ተነሣ፤ የብላቴናዪቱም አባት አማቹን፥ “ሰውነትህን በቁራሽ እንጀራ አበርታ፤ ከዚያም በኋላ ትሄዳላችሁ” አለው። 6ሁለቱም በአንድ ላይ ተቀመጡ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ የብላቴናዪቱም አባት ሰውዬውን፥ “ዛሬ ደግሞ ከዚህ እደር ልብህንም ደስ ይበለው” አለው። 7ሰውዬውም ሊሄድ ተነሣ፤ አማቱ ግን ግድ አለው፤ ዳግመኛም በዚያ አደረ። 8በአምስተኛውም ቀን ለመሄድ ማልዶ ተነሣ፤ የብላቴናዪቱም አባት፥ “እህል ብላ፤ ከዚህም በኋላ ፀሐይ ሲበርድ ትሄዳለህ” አለው። ሁለቱም በሉ፤ ጠጡም። 9ሰውዬውም ከዕቅብቱና ከብላቴናው ጋር ለመሄድ ተነሣ፤ የብላቴናዪቱ አባት አማቱም፥ “እነሆ፥ መሽትዋል፤ ፀሐዩም ሊጠልቅ ደርሷል፤ ዛሬም እዚህ እደር፤ በዚህም ተቀመጥ፤ ልብህም ደስ ይበለው፤ በጥዋትም መንገዳችሁን ትገሠግሣላችሁ፤ ወደ ቤትህም ትገባለህ” አለው።
10ሰውዬው ግን በዚያ ሌሊት ለማደር አልፈቀደም፤ ተነሥቶም ሄደ፤ ኢየሩሳሌምም ወደ ተባለችው ወደ ኢያቡስ ፊት ለፊት ደረሰ። ከእርሱም ጋር ሁለት የተጫኑ አህዮች ነበሩ፤ ዕቅብቱም ከእርሱ ጋር ነበረች። 11በኢያቡስም አንጻር ገና ሳሉ ፀሐይዋ ተቈለቈለች፤ ብላቴናውም ጌታውን፥ “ና፤ ወደዚህች ወደ ኢያቡሳውያን ከተማ፥ እባክህ እናቅና፤ በእርስዋም እንደር” አለው። 12ጌታውም፥ “ከእስራኤል ልጆች ወዳልሆነች ወደ እንግዳ ከተማ አንገባም፤ እኛ ወደ ገባዖን እንለፍ” አለው። 13ብላቴናውንም፥ “ና፤ ከእነዚህ ስፍራ ወደ አንዱ እንቅረብ፤ በገባዖን ወይም በራማ እንደር” አለው። 14አልፈውም ሄዱ፤ የብንያምም ነገድ በምትሆነው በገባዖን አጠገብ ሳሉ ፀሐይ ገባችባቸው። 15በገባዖንም ገብተው ያድሩ ዘንድ ወደዚያ አቀኑ። ገብተውም በከተማው አደባባይ በተቀመጡ ጊዜ ወደ ቤቱ የሚያስገባቸውና የሚያሳድራቸው አልነበረም።
16እነሆም አንድ ሽማግሌ ከእርሻው ሥራ ወደ ማታ መጣ፤ ይህም ሰው ከተራራማው ከኤፍሬም ሀገር ነበረ፤ በገባዖንም በእንግድነት ተቀምጦ ነበር፤ የዚያ ሀገር ሰዎች ግን የብንያም ልጆች ነበሩ። 17ዐይኑንም አንሥቶ መንገደኛውን በከተማው አደባባይ አየ፤ ሽማግሌውም፥ “ወዴት ትሄዳለህ? ከወዴትስ መጣህ?” አለው። 18እርሱም፥ “እኛ ከይሁዳ ቤተ ልሔም ወደ ተራራማው ወደ ኤፍሬም ሀገር ማዶ እናልፋለን፤ እኔ ከዚያ ነኝ፤ ወደ ይሁዳ ቤተ ልሔምም ሄጄ ነበር፥ አሁንም ወደ ቤቴ እሄዳለሁ፤ በቤቱም የሚያሳድረኝ አጣሁ፤ 19ለአህዮቻችን ገለባና ገፈራ አለን፤ ለእኔና ለገረድህ ከባሪያዎችህም ጋር ላለው ብላቴና እንጀራና የወይን ጠጅ አለን፤ ከሚያስፈልገን ሁሉ አንዳችም አላጣንም” አለው። 20ሽማግሌውም ሰው፥ “ሰላም ከአንተ ጋር ይሁን፤ የምትሻውንም ሁሉ እኔ እሰጥሃለሁ፤ በአደባባይ ግን አትደር” አለው። 21ወደ ቤቱም አስገባው፤ ለአህዮቹም ገፈራ ጣለላቸው፤ እግራቸውንም ታጠቡ፤ በሉም፤ ጠጡም።
የኢያቡሴዎን ሰዎች በደል
22ሰውነታቸውንም ደስ ባሰኙ ጊዜ የኃጥኣን ልጆች የሆኑ የከተማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ፤ በሩንም ይደበድቡ ነበር፤ ባለቤቱንም ሽማግሌውን ሰው፥ “ወደ ቤትህ የገባውን ሰው እንድንደርስበት አውጣልን” አሉት። 23ባለቤቱም ሽማግሌው ወደ እነርሱ ወጥቶ፥ “ወንድሞቼ ሆይ! ይህን ክፉ ነገር ታደርጉ ዘንድ አይገባችሁም፤ ይህ ሰው ወደ ቤቴ ከገባ በኋላ እንደዚህ ያለ ስንፍና አትሥሩ። 24ድንግል ልጄና የእርሱም ዕቅብት እነሆ፥ አሉ፤ አሁንም አወጣቸዋለሁ፤ አዋርዱአቸው፤ በዐይናችሁም ፊት ደስ የሚላችሁን አድርጉባቸው፤ ነገር ግን በዚህ ሰው ላይ እንደዚህ ያለ የስንፍና ሥራ አታድርጉ” አላቸው። 25ሰዎቹ ግን ሊሰሙት አልፈቀዱም፤ ሰውየውም ዕቅብቱን ይዞ ወደ እነርሱ አወጣላቸው፤ አዋረድዋትም፤ ሌሊቱንም ሁሉ እስኪነጋ ድረስ አመነዘሩባት፤ ጎህም በቀደደ ጊዜ ለቀቁአት። 26ሴቲቱም ማለዳ መጣች፤ ጌታዋም ባለበት በሰውዬው ቤት ደጅ ወድቃ እስኪነጋ ድረስ በዚያ ቀረች።
27ጌታዋም ማለዳ ተነሣ፤ የቤቱንም ደጅ ከፈተ፤ መንገዱንም ለመሄድ ወጣ፤ እነሆም፥ ዕቅብቱ ሴት በቤቱ ደጃፍ ላይ ወድቃ፥ እጆችዋም በመድረኩ ላይ ወድቀው አገኛት። 28እርሱም፥ “ተነሺ እንሂድ” አላት፤ እርስዋ ግን ሞታ ነበርና አልመለሰችም፤ በዚያ ጊዜም በአህያው ላይ ጫናት፤ ተነሥቶም ወደ ስፍራው ተመለሰ። 29ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ ካራ አነሣ፤ ዕቅብቱንም ይዞ ከአጥንቶችዋ መለያያ ላይ ለዐሥራ ሁለት ቈራርጦ ወደ እስራኤል ሀገር ሁሉ ሰደደ። 30ከዚያም በኋላ ያያት ሁሉ እንዲህ አለ፥ “እስራኤል ከግብፅ ከወጡ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር የሆነበት ጊዜ የለም፤ የታየበትም ጊዜ የለም፤” #ቀጣዩ በዕብ. እና በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።ያም ሰው እነዚያን የላካቸውን ሰዎች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፥ “የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ በሏቸው፦ እስራኤል ከግብፅ ከወጡ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ እንዲህ የሆነበት ጊዜ አለን? እናንተ ተመካከሩበት፤ የሚበጀውንም ተነጋገሩ።”
Currently Selected:
መጽሐፈ መሳፍንት 19: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ