ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 20:8-9

ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 20:8-9 አማ2000

በተ​ና​ገ​ርሁ ቍጥር እጮ​ኻ​ለሁ፤ ግፍና ጥፋት ብዬ እጠ​ራ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ቀኑን ሁሉ ስድ​ብና ዋዛ ሆኖ​ብ​ኛ​ልና። እኔም እን​ዲህ አልሁ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም አላ​ነ​ሣም፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በስሙ አል​ና​ገ​ርም፥” በአ​ጥ​ን​ቶች ውስጥ እንደ ገባ እን​ደ​ሚ​ነ​ድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነ​ብኝ፤ ደከ​ምሁ፤ መሸ​ከ​ምም አል​ቻ​ል​ሁም።