ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 21

21
ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መያዝ የተ​ነ​ገረ ትን​ቢት
1የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ የመ​ል​ክ​ያን ልጅ ጳስ​ኮ​ር​ንና የካ​ህ​ኑን የመ​ዕ​ሴ​ይን ልጅ ሶፎ​ን​ያ​ስን ወደ ኤር​ም​ያስ በላከ ጊዜ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦ እን​ዲ​ህም አለ፦ 2“የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ይወ​ጋን ዘንድ መጥ​ቶ​አ​ልና ከእኛ ይመ​ለስ ዘንድ፥ ምና​ል​ባ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር እንደ ተአ​ም​ራቱ ሁሉ ያደ​ርግ እንደ ሆነ ስለ እኛ፥ እባ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠይቅ።” 3ኤር​ም​ያ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስን እን​ዲህ በሉት፦ 4የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ በቅ​ጥ​ርም ውጭ የከ​በ​ቡ​አ​ች​ሁን ከለ​ዳ​ው​ያ​ንን የም​ት​ወ​ጉ​በ​ትን በእ​ጃ​ችሁ ያለ​ውን የጦር መሣ​ሪ​ያ​ች​ሁን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እነ​ዚ​ያ​ንም በዚ​ህች ከተማ መካ​ከል እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ። 5እኔም በተ​ዘ​ረ​ጋች እጅና በብ​ርቱ ክንድ፥ በቍ​ጣና በመ​ዓት፥ በታ​ላ​ቅም መቅ​ሠ​ፍት አወ​ጋ​ች​ኋ​ለሁ። 6በዚ​ህ​ችም ከተማ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ሰዎ​ች​ንና እን​ስ​ሶ​ችን እመ​ታ​ለሁ፤ በጽ​ኑም ቸነ​ፈር ይሞ​ታሉ። 7ከዚህ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስ​ንና አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ ከቸ​ነ​ፈ​ርና ከሰ​ይፍ፥ ከራ​ብም በዚ​ህች ከተማ የቀ​ሩ​ትን ሕዝ​ቡ​ንም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ፥ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም በሚ​ሹት እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም በሰ​ይፍ ስለት ይመ​ታ​ቸ​ዋል፤ አያ​ዝ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ም​ራ​ቸ​ውም።”
8ለዚ​ህም ሕዝብ እን​ዲህ በል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በፊ​ታ​ችሁ የሕ​ይ​ወ​ትን መን​ገ​ድና የሞ​ትን መን​ገድ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ። 9በዚ​ህች ከተማ ውስጥ የሚ​ቀ​መጥ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ይሞ​ታል፤ ወጥቶ ወደ ከበ​ቡ​አ​ችሁ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን የሚ​ገባ ግን በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤ ሰው​ነ​ቱም ምርኮ ትሆ​ና​ለች። 10ለመ​ል​ካም ሳይ​ሆን ለክፉ ፊቴን በዚ​ህች ከተማ ላይ አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና፤ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ ትሰ​ጣ​ለች፤ እር​ሱም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላ​ታል።”
11የይ​ሁዳ ንጉሥ ቤት ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ። 12የዳ​ዊት ቤት ሆይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ስለ ሥራ​ችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እን​ዳ​ይ​ነ​ድ​ድና ማንም ሳያ​ጠ​ፋው እን​ዳ​ያ​ቃ​ጥል፥ በማ​ለዳ ፍር​ድን አድ​ርጉ፤ የተ​ነ​ጠ​ቀ​ው​ንም ከአ​ስ​ጨ​ና​ቂው እጅ አድኑ። 13እነሆ በሜዳ ላይ ባለው ድን​ጋ​ያማ ሸለቆ የም​ት​ቀ​መጥ ሆይ! እኔ በአ​ንተ ላይ ነኝ፤ እና​ን​ተም፦ የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጠን#ዕብ. “በእኛ ላይ የሚ​ወ​ርድ” ይላል። ወይም ወደ መኖ​ሪ​ያ​ችን የሚ​ገባ ማን ነው? የም​ትሉ ሆይ! እኔ በእ​ና​ንተ ላይ ነኝ፤ 14እንደ ሥራ​ች​ሁም ፍሬ እቀ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር#“እንደ ሥራ​ች​ሁም ፍሬ እቀ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በዱ​ር​ዋም ውስጥ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ያለ​ውን ሁሉ ይበ​ላል።”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ