ትንቢተ ኤርምያስ 23
23
የሚመጣው ተስፋ
1“የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው!” ይላል እግዚአብሔር። 2ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፥ “በጎችን በትናችኋል፤ አባርራችኋቸውማል፥ አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ! እንደ ሥራችሁ ክፋት እጐበኛችኋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር። 3የሕዝቤን#ዕብ. “የመንጋዬንም” ይላል። ቅሬታ ከበተንኋቸው ምድር ሁሉ ወደ መሰማሪያቸው ሰብስቤ እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም ይበዛሉ፤ ይባዛሉም። 4የሚጠብቋቸውን እረኞች አስነሣላቸዋለሁ፤ ዳግመኛም አይፈሩም፤ አይደነግጡምም፥#ዕብ. “ከእነርሱም አንድ አይጐድልም” የሚል ይጨምራል። ይላል እግዚአብሔር።
5“እነሆ ለዳዊት የጽድቅ ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥” ይላል እግዚአብሔር፤ ንጉሥ ይነግሣል፤ ያስባል፤ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል። 6በዘመኑም ይሁዳ ይድናል፤ እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፤ ይህም ስም እግዚአብሔር በነቢያት ኢዮሴዴቅ ብሎ የጠራው ነው።#ዕብ. “የሚጠራበትም ስም እግዚአብሔር ጽድቃችን ነው ተብሎ ነው” ይላል።
7ስለዚህ እነሆ፥ “የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን! ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥” ይላል እግዚአብሔር፤ 8ነገር ግን፥ “የእስራኤልን ቤት ዘር ከሰሜን ሀገርና ካሳደዷቸውም ሀገር ሁሉ ያወጣና የመራ ሕያው እግዚአብሔርን!” ይባላል፤ በምድራቸውም መልሶ ያኖራቸዋል።
ኤርምያስ በሐሰተኞች ነቢያት ላይ የተናገረው ትንቢት
9ስለ ነቢያት ልቤ በውስጤ ተሰብሮአል፤ አጥንቶችም ሁሉ ታውከዋል፤ ከእግዚአብሔር ፊት የተነሣ፤ ከጌትነቱም ክብር የተነሣ እኔም በመከራ እንደ ተቀጠቀጠ ሰው፥ የወይን ጠጅ እንዳሸነፈውም እንደ ሰካራም ሰው ሆኛለሁ። 10ዝሙታቸው ምድርን ሞልትዋልና፥ ከመርገም ፊት የተነሣ ምድር አልቅሳለች፤ የምድረ በዳ ማሰሪያው ሁሉ ደርቆአል፤ ሥራቸውና ድካማቸው ከንቱ ሆነ።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “መንገዳቸው ክፉ ነው ፤ ብርታታቸውም ቅን አይደለም” ይላሉ። 11“ነቢዩና ካህኑም ረክሰዋልና፥ በቤቴም ውስጥ ክፋታቸውን አግኝቻለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። 12ስለዚህ መንገዳቸው ድጥና ጨለማ ትሆንባቸዋለች፤ እነርሱም ፍግምግም ብለው ይወድቁባታል፤ እኔም በምጐበኛቸው ዓመት ክፉ ነገርን አመጣባቸዋለሁና፥” ይላል እግዚአብሔር።
13በበዓል ትንቢት የተናገሩበትን የሰማርያን ነቢያት ኀጢአታቸውን አይቻለሁ፤ ሕዝቤን እስራኤልንም አሳትዋቸው። 14በኢየሩሳሌምም ነቢያት ላይ የሚያስደነግጥን ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ፤ በሐሰትም ይሄዳሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ሁሉም እንደ ሰዶም፥ የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ። 15ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ ከኢየሩሳሌም ነቢያት ዘንድ ርኵሰት በምድር ሁሉ ላይ ወጥቶአልና ሕማምን#ዕብ. “እሬትን” ይላል። አበላቸዋለሁ፤ መራራ ውኃንም አጠጣቸዋለሁ።”
16ኀያል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ትንቢት የሚናገሩላችሁን የነቢያትን ቃል አትስሙ፤ ከንቱነትን ያስተምሩአችኋል፤ ከእግዚአብሔር አፍ ሳይሆን ከገዛ ልባቸው የወጣውን ራእይ ይናገራሉ። 17የእግዚአብሔርን ቃል ለሚያቃልሉ ሰላም ይሆንላችኋል፥ በፍላጎታቸውና በልቡናቸው ክፋት ለሚሄዱም ሁሉ፦ ክፉ ነገር አያገኛችሁም” ይላሉ። 18በእግዚአብሔር ምክር የሚቆም፥ ቃሉን የሚያይና የሚሰማ ማን ነው? ቃሉንስ ያዳመጠ፥ የሰማስ ማንነው?
19እነሆ ከእግዚአብሔር ዘንድ ንውጽውጽታ ይመጣል፤ ኃጥኣንን ያነዋውጣቸውና ይገለብጣቸው ዘንድ መቅሠፍት ይመጣባቸዋል፤ የዐመፀኞችን ራስ ይገለባብጣል። 20የእግዚአብሔር ቍጣ የልቡን ዐሳብ ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ አይመለስም፤ በኋለኛውም ዘመን ያውቁታል። 21“እኔ ሳልልካቸው እነዚህ ነቢያት ሮጡ፤ እኔም ሳልነግራቸው ትንቢትን ተናገሩ። 22በቃሌ ቢቆሙና ምክሬን ቢሰሙ ኖሮ ግን ሕዝቤን ከክፉ ሥራቸው በመለሱአቸው ነበር።
23“እኔ ቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ ሩቅ አምላክ አይደለሁም ይላል እግዚአብሔር። 24ሰው በስውር ቦታ ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል እግዚአብሔር። 25ሕልምን አለምን እያሉ በስሜ ሐሰተኛ ትንቢት የሚናገሩትን የነቢያትን ነገር ሰምቻለሁ። 26ትንቢትን በሐሰት በሚናገሩ፥ የልባቸውንም ሽንገላ በሚናገሩ በነቢያት ልብ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው? 27አባቶቻቸው ስለ በዓል ስሜን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሕጌን” ይላል። እንደ ረሱ፥ እያንዳንዱ ለባልንጀራው በሚናገራት ሕልማቸው ሕዝቤን ስሜን ለማስረሳት ያስባሉ። 28የሚያልም ነቢይ ሕልምን ይናገር፤ ቃሌም ያለበት ቃሌን በእውነት ይናገር። ገለባ ከስንዴ ጋር ምን አለው? ይላል እግዚአብሔር። 29በውኑ ቃሌ እንደ እሳት፥ ድንጋዩንም እንደሚያደቅቅ መዶሻ አይደለምን? ይላል እግዚአብሔር። 30ስለዚህ እነሆ እያንዳንዱ ከባልንጀራው ዘንድ ቃሌን በሚሰርቁ ነቢያት ላይ ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር። 31እነሆ ከምላሳቸው ትንቢትን አውጥተው፦ እርሱ የእግዚአብሔር ሸክም ነው በሚሉ ነቢያት ላይ ነኝ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ 32እነሆ ሐሰትን በሚያልሙ፥ በሚናገሩም፥ በሐሰታቸውና በድፍረታቸውም ሕዝቤን በሚያስቱ በነቢያት ላይ ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እኔም አልላክኋቸውም፤ አላዘዝኋቸውምም፤ ለእነዚህ ሕዝብ በማናቸውም አይረቡአቸውም፥” ይላል እግዚአብሔር።
33ይህ ሕዝብ ወይም ነቢይ ወይም ካህን፥ “የእግዚአብሔር ሸክም ምንድር ነው?” ብሎ ቢጠይቅህ፥ አንተ፥ “ሸክሙ እናንተ ናችሁ፤ እጥላችሁማለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር” ትላቸዋለህ። 34የእግዚአብሔር ሸክም የሚለውን ነቢይንና ካህንን፥ ሕዝብንም ያን ሰውና ቤቱን እቀጣለሁ። 35አንዱም አንዱ ለባልንጀራው፥ አንዱም አንዱ ለወንድሙ እንዲህ ይበል፥ “እግዚአብሔር የመለሰው ምንድን ነው? እግዚአብሔርስ ምን ነገር ተናገረ?” 36ለሰው ሁሉ ቃሉ ሸክም ይሆንበታልና የእግዚአብሔር ሸክም ብላችሁ ከእንግዲህ ወዲህ አትጥሩ፤ የሠራዊትን ጌታ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን የሕያውን አምላክ ቃል ለውጣችኋልና።#“የሰራዊትን ጌታ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን የሕያውን አምላክ ቃል ለውጣችኋልና” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 37ለነቢዩ፥ “እግዚአብሔር ምን መለሰልህ እግዚአብሔርስ የተናገረው ምንድን ነው?” በሉ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አምላካችን እግዚአብሔር ምን ተናገረ” ይላል። ምን ተናገረ? 38ነገር ግን፥ “የእግዚአብሔር ሸክም” ብትሉ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እኔ፦ የእግዚአብሔር ሸክም አትበሉ ብዬ ልኬባችኋለሁና፥ እናንተም ይህን ቃል፦ የእግዚአብሔር ሸክም ብላችኋልና፥ 39ስለዚህ፥ እነሆ- ፈጽሜ እረሳችኋለሁ#“እነሆ ፈጽሜ እረሳችኋለሁ” የሚለው በዕብ. ብቻ። እናንተንም፥ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም የሰጠኋትን ከተማ ከፊቴ አንሥቼ እጥላለሁ። 40የዘለዓለምንም ስድብና ከቶ ተረስቶ የማይጠፋውን የዘለዓለምን ውርደት አመጣባችኋለሁ።”
Currently Selected:
ትንቢተ ኤርምያስ 23: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ