ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 24

24
የበ​ለስ ፍሬ የተ​ሞሉ ሁለት ቅር​ጫ​ቶች
1የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ቄ​ምን ልጅ ኢኮ​ን​ያ​ንን፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም አለ​ቆች፥ ብል​ሃ​ተ​ኞ​ች​ንና እስ​ረ​ኞ​ችን፥ ጓደ​ኞ​ቻ​ቸ​ው​ንም#ዕብ. “ጠራ​ቢ​ዎ​ች​ንና ብረት ሠራ​ተ​ኞች” ይላል። ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ማርኮ ወደ ባቢ​ሎን ከአ​ፈ​ለ​ሳ​ቸው በኋላ፥ እነሆ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ፊት የተ​ቀ​መጡ ሁለት የበ​ለስ ቅር​ጫ​ቶ​ችን አሳ​የኝ። 2በአ​ን​ደ​ኛ​ዪቱ ቅር​ጫት አስ​ቀ​ድሞ እንደ ደረሰ በለስ የሚ​መ​ስል እጅግ መል​ካም በለስ ነበ​ረ​ባት፤ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ቅር​ጫት ከክ​ፋቱ የተ​ነሣ ይበላ ዘንድ የማ​ይ​ቻል እጅግ ክፉ በለስ ነበ​ረ​ባት። 3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ኤር​ም​ያስ ሆይ! የም​ታ​የው ምን​ድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “በለ​ስን አያ​ለሁ፤ እጅግ መል​ካም የሆነ መል​ካም በለስ፥ ከክ​ፋ​ቱም የተ​ነሣ ይበላ ዘንድ የማ​ይ​ቻል እጅግ ክፉ የሆነ ክፉ በለስ ነው” አልሁ።
4የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 5“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እን​ደ​ዚህ እንደ መል​ካሙ በለስ፥ እን​ዲሁ ከዚህ ስፍራ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን ምድር የሰ​ደ​ድ​ሁ​ትን የይ​ሁ​ዳን ምርኮ ለበ​ጎ​ነት እመ​ለ​ከ​ተ​ዋ​ለሁ። 6ዐይ​ኔ​ንም ለበ​ጎ​ነት በእ​ነ​ርሱ ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ወደ​ዚ​ህ​ችም ምድር ለመ​ል​ካም እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እሠ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ አላ​ፈ​ር​ሳ​ቸ​ውም፤ እተ​ክ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ አል​ነ​ቅ​ላ​ቸ​ውም። 7እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ የሚ​ያ​ውቅ ልብ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በፍ​ጹ​ምም ልባ​ቸው ወደ እኔ ይመ​ለ​ሳ​ሉና ሕዝቤ ይሆ​ኑ​ኛል፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።”
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላል፥ “ከክ​ፋቱ የተ​ነሣ ይበላ ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ቻል እንደ ክፉው በለስ፥ እን​ዲሁ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስን፤ አለ​ቆ​ቹ​ንም፥ በዚች ሀገር የሚ​ቀ​ሩ​ት​ንም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ቅሬታ፥ በግ​ብ​ጽም ሀገር የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን እን​ዲሁ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ። 9በማ​ሳ​ድ​ዳ​ቸ​ውም ስፍራ ሁሉ ለስ​ድ​ብና ለም​ሳሌ፥ ለጥ​ላ​ቻና ለር​ግ​ማን ይሆኑ ዘንድ በም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ እን​ዲ​በ​ተኑ አደ​ር​ጋ​ለሁ። 10ለእ​ነ​ርሱ፥ ለዘ​ራ​ቸ​ውና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከሰ​ጠ​ኋ​ቸው ምድር እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ሰይ​ፍ​ንና ራብን ቸነ​ፈ​ር​ንም እሰ​ድ​ዳ​ለሁ።”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ