ትንቢተ ኤርምያስ 25
25
ስለ ባቢሎን ምርኮ የተነገረ ትንቢት
1በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት፥ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በመጀመሪያው ዓመት፥#“በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በመጀመሪያው ዓመት” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ስለ ይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው። 2ይህንም ቃል ነቢዩ ኤርምያስ ለይሁዳ ሕዝብ ሁሉና በኢየሩሳሌም ለተቀመጡ ሁሉ እንዲህ ሲል ተናገረ፦ 3“ከይሁዳ ንጉሥ ከአሞጽ#ዕብ. “ከአሞን” ይላል። ልጅ ከኢዮስያስ ከዐሥራ ሦስተኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባሉት በእነዚህ በሃያ ሦስቱ ዓመታት፥ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ መጣ፤ እኔም ማልጄ ተነሥቼ ተናገርኋችሁ፤ ነገር ግን አልሰማችሁኝም።” 4እግዚአብሔርም ባሪያዎቹን ነቢያትን ወደ እናንተ ላከ፤ እነርሱም ማልደው ገሠገሡ፤ እናንተም አልሰማችኋቸውም፤ ለመስማትም ጆሮአችሁን አላዘነበላችሁም። 5እርሱም፥ “ሁላችሁ እናንተ ከክፉ መንገዳችሁና ከሥራችሁ ክፋት ተመለሱ፤ እግዚአብሔርም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣችሁ ምድር ትቀመጣላችሁ አለ። 6ትገዙላቸውና ትሰግዱላቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፤ ክፉም እንዳላደርግባችሁ በእጃችሁ ሥራ አታስቈጡኝ። 7ለእናንተ ጕዳት እንዲሆን በእጃችሁ ሥራ ታስቈጡኝ ዘንድ#“ለእናንተ ጕዳት እንዲሆን በእጃችሁ ሥራ ታስቈጡኝ ዘንድ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። አልሰማችሁኝም፥” ይላል እግዚአብሔር። 8ስለዚህ ኀያል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ቃሌን አልሰማችሁምና፤ 9እነሆ ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ፤ ባሪያዬንም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርን#“ባሪያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። እወስዳለሁ፤ በዚችም ምድርና በሚቀመጡባትም ሰዎች ላይ፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ለጥፋትና ለፉጨት ለዘለዓለምም ዕፍረት ባድማ አደርጋቸዋለሁ። 10ከእነርሱም የሐሤትን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራን ድምጽና የሴት ሙሽራን ድምፅ፥ የወፍጮንም ድምፅ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሽታ መዓዛ” ይላል። የመብራትንም ብርሃን አስቀራለሁ። 11ይህችም ምድር ሁሉ ትጠፋለች፤ ለእነዚህም አሕዛብና ለባቢሎን ንጉሥ ሰባ ዓመት ይገዛሉ።
12“ሰባው ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ፥ የባቢሎንን ንጉሥና#“የባቢሎን ንጉሥና” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ያን ሕዝብ ስለ ኀጢአታቸው#“ስለ ኃጢአታቸው” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። እቀጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ የከለዳውያንንም ምድር#“የከለዳውያንንም ምድር” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ለዘለዓለም አጠፋቸዋለሁ። 13በእርስዋም ላይ የተናገርሁትን ቃሌን ሁሉ፥ ኤርምያስ በአሕዛብ ሁሉ ላይ በትንቢት የተናገረውን በዚች መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ፥ በዚያች ምድር ላይ አመጣለሁ። 14ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት እነርሱን ይገዙአቸዋል፤ እኔም እንደ አደራረጋቸውና እንደ እጃቸው ሥራ እከፍላቸዋለሁ።”#ምዕ. 25 ቍ. 14 በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
የእግዚአብሔር ፍርድ በአሕዛብ ላይ
15የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፥ “ያልተበረዘ የዚህን ቍጣ የወይን ጠጅ ጽዋ ከእጄ ውሰድ፤ አንተን የምሰድድባቸውን አሕዛብን ሁሉ አጠጣቸው። 16ከምሰድድባቸውም ሰይፍ የተነሣ ይጠጣሉ፤ ይወላገዳሉ፤ ያብዳሉም።” 17ከእግዚአብሔርም እጅ ጽዋውን ወሰድሁ፤ እግዚአብሔርም እኔን የላከባቸውን አሕዛብ ሁሉ አጠጣኋቸው። 18ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ፈጽሞ ምድረ በዳ ይሆኑ ዘንድ፥ ለርግማንም አደርጋቸው ዘንድ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች፥ ነገሥታቷንም፥ አለቆችዋንም አጠጣኋቸው። 19የግብፅንም ንጉሥ ፈርዖንን፥ አገልጋዮቹንም፥ መሳፍንቱንና መኳንንቱን፤ ሕዝቡንም ሁሉ፥ 20የተደባለቀውንም ሕዝብ ሁሉ፥ የዖፅ ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፥ የፍልስጥኤም ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፤ አስቀሎናንም፥ ጋዛንም፥ አቃሮንንም፥ የአዛጦንንም ቅሬታ፤ 21ኤዶምያስንም፥ ሞዓብንም፥ የአሞንንም ልጆች፤ 22የጢሮስንም ነገሥታት ሁሉ፥ የሲዶናንም ነገሥታት ሁሉ፥ በባሕር ማዶ ያሉ የደሴት ነገሥታትንም፤ 23ድዳንንም፥ ቴማንንም፥ ሮስንም፥#ዕብ. “ቡዝንም” ይላል። ፊታቸውን የሚከተቡትን ሁሉ፤ 24የዓረብ ነገሥታትንም#“የዐረብ ነገሥታትንም” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ሁሉ፥ በምድረ በዳ የሚቀመጡ የድብልቅ ሕዝብ ነገሥታትንም#“ነገሥታትንም” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ሁሉ፤ 25የዘምሪ ነገሥታትንም ሁሉ፥#“የዘምሪ ነገሥታትንም ሁሉ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። የኤላም ነገሥታትንም ሁሉ፥ የሜዶን ነገሥታትንም ሁሉ፤ 26የቀረቡና የራቁ፥ አንዱ ከሌላው ጋር ያሉ የሰሜን ነገሥታትንም ሁሉ፥ በምድር ፊት ላይ ያሉ የዓለም መንግሥታትንም ሁሉ አጠጣኋቸው፤ የሲሳርም ንጉሥ ከእነርሱ በኋላ ይጠጣል።#“የሲሳርም ንጉሥ ከእነርሱ በኋላ ይጠጣል” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
27አንተም፥ “የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመካከላችሁ ከምሰድደው ሰይፍ የተነሣ ጠጡ፤ ስከሩም፤ ተፍገምገሙ፤ ውደቁም፤ ከእንግዲህም ወዲህ አትነሡም በላቸው። 28ይጠጡም ዘንድ ጽዋውን ከእጅህ ለመቀበል እንቢ ቢሉ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ፈጽማችሁ ትጠጣላችሁ” በላቸው። 29እነሆ ስሜ የተጠራባትን ከተማ አስጨንቃት ዘንድ እጀምራለሁ፤ በውኑ እናንተ መንጻትን ትነጻላችሁን? በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ሰይፍን እጠራለሁና አትነጹም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
30“ስለዚህም ይህን ቃል ሁሉ ትንቢት ትናገርባቸዋለህ፤ እንዲህም ትላቸዋለህ፦ እግዚአብሔር በላይ ሆኖ እንደ አንበሳ ያገሣል፤ በቅዱስ ማደሪያውም ሆኖ ድምፁን ያሰማል፤ በበረቱ ላይ እጅግ ያገሣል፤ ወይንም እንደሚጠምቁ በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ይጮኻል። 31እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ክርክር አለውና ጥፋት እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደርሳል፤ ከሥጋ ለባሽ ሁሉም ጋር ይፋረዳል፤ ኀጢአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።”
32የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ ክፉ ነገር ከሕዝብ ወደ ሕዝብ ይወጣል፤ ጽኑም ዐውሎ ነፋስ ከምድር ዳርቻ ይነሣል። 33በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ግዳዮች ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ በምድር ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ እንጂ አይሰበሰቡም፤ አይቀበሩምም። 34ትታረዱና ትበተኑ ዘንድ ቀናችሁ ደርሶአልና፥ እንደ ተወደደ የሸክላ ዕቃ#ዕብ. “እንደ ተመረጡ አውራ በጎች” ይላል። ትወድቃላችሁና እናንተ እረኞች! አልቅሱ፤ እናንተም የበጎች አውራዎች! ጩኹ።#ዕብ. “በአመድ ውስጥ ተንከባለሉ” ይላል። 35ከእረኞች የማይጠፋ የለም፤ የበጎች አውራዎችም አይድኑም። 36እግዚአብሔር ማሰማርያቸውን አጥፍቶአልና የእረኞች ጩኸት ድምፅ፥ የበጎች አውራዎችም ልቅሶ ሆኖአል። 37ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የተነሣ የሰላም ውበት ፈርሶአል። 38እንደ አንበሳ መደቡን ለቅቆአል፤ ከአረማውያን ሰልፍና ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የተነሣ ምድራቸው ምድረ በዳ ሆናለችና።”#ምዕ. 25 ከቍ. 15 እስከ 38 ያለው በግሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 33 ከቍ. 13 እስከ 38 ነው።
Currently Selected:
ትንቢተ ኤርምያስ 25: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ