መጽ​ሐፈ ኢዮብ 40

40
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መለሰ፥ ኢዮ​ብ​ንም እን​ዲህ አለው፦
2“በውኑ የሚ​ከ​ራ​ከር ሰው
ሁሉን ከሚ​ችል አም​ላክ ጋር ይከ​ራ​ከ​ራ​ልን?
ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር የሚ​ዋ​ቀስ እርሱ ይመ​ል​ስ​ለት።”#ግእዝ “ምስለ ቢጽ​ከኑ ዘትትዋ​ቀስ አንተ ከመ ትትዋ​ሣእ እንዘ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይዘ​ል​ፈከ” ይላል።
የኢ​ዮብ መልስ
3ኢዮ​ብም መለሰ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም እን​ዲህ አለው፦
4“አንተ ስታ​ስ​ተ​ም​ረኝ እኔ የም​መ​ል​ሰው ምን አለኝ?
ይህ​ንስ እየ​ሰ​ማሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር እከ​ራ​ከር ዘንድ እኔ ምን​ድን ነኝ?
እጄን በአፌ ላይ ከማ​ኖር በቀር የም​መ​ል​ሰው ምን​ድን ነው?
5አንድ ጊዜ ተና​ገ​ርሁ፥
ሁለ​ተኛ ጊዜም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አል​ና​ገ​ርም።”
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለኢ​ዮብ እንደ መለ​ሰ​ለት
6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ደ​ገና በደ​መና ውስጥ ሆኖ ለኢ​ዮብ መለ​ሰ​ለት፥ እን​ዲ​ህም አለ፦
7“እን​ግ​ዲህ እንደ ወንድ ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፤
እጠ​ይ​ቅ​ሃ​ለሁ፥ አን​ተም መል​ስ​ልኝ።
8ወይም ፍር​ዴን መቃ​ወ​ም​ህን ተው፥
ጽድ​ቅህ እን​ድ​ት​ገ​ለጥ እንጂ እኔ በሌላ መን​ገድ የም​ፈ​ር​ድ​ብህ ይመ​ስ​ል​ሃ​ልን?
9እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክንድ ያለ ክንድ አለ​ህን?
ወይስ እንደ እርሱ ባለ ድምፅ ታን​ጐ​ደ​ጕ​ዳ​ለ​ህን?
10እስኪ ልዕ​ል​ና​ንና ኀይ​ልን ተላ​በስ፤
በክ​ብ​ርና በግ​ር​ማም ተጐ​ና​ጸፍ።
11የቍ​ጣ​ህን መላ​እ​ክት ላክ፤
ትዕ​ቢ​ተ​ኛ​ው​ንም ሁሉ አዋ​ር​ደው።
12ትዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውን ሰው ዝቅ ዝቅ አድ​ር​ገው፤
ዝን​ጉ​ዎ​ች​ንም በአ​ንድ ጊዜ አጥ​ፋ​ቸው።
13በአ​ፈር ውስጥ በአ​ን​ድ​ነት ሰው​ራ​ቸው፤
ፊታ​ቸ​ው​ንም በኀ​ፍ​ረት ሙላ።
14በዚ​ያን ጊዜ ቀኝ እጅህ ታድ​ንህ ዘንድ እን​ድ​ት​ችል፥
እኔ ደግሞ እመ​ሰ​ክ​ር​ል​ሃ​ለሁ።
15“እነሆ፥ በአ​ንተ ዘንድ የዱር አውሬ አለ፤
እንደ በሬ ሣር ይበ​ላል።
16እነሆ፥ ብር​ታቱ በወ​ገቡ ውስጥ ነው፤
ኀይ​ሉም በሆዱ እን​ብ​ርት ውስጥ ነው።
17ጅራ​ቱን እንደ ጥድ ዛፍ ያወ​ዛ​ው​ዛል፤
የወ​ር​ቹም ጅማት የተ​ጐ​ነ​ጐነ ነው።
18የጐ​ድን አጥ​ንቱ እንደ ናስ ነው፤
የጀ​ር​ባው አጥ​ን​ቶ​ችም እንደ ብረት ዘን​ጎች ናቸው።
19ይህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፍ​ጥ​ረቱ አውራ ነው።
ከተ​ፈ​ጠ​ረም በኋላ መላ​እ​ክት ሣቁ​በት።#ዕብ. “ሠሪ​ውም ሰይ​ፍን ሰጠው” ይላል።
20 # በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ይለ​ያል። ወደ ረዥም ተራራ በወጣ ጊዜም
በሜ​ዳው ላሉ እን​ስ​ሳት በጥ​ልቁ ስፍራ ደስ​ታን ያደ​ር​ጋል።
21ጥላ ካለው ዛፍ በታች፥ በደ​ን​ገል፥
በቄ​ጠ​ማና በሸ​ን​በቆ ሥር ይተ​ኛል።
22ጥላ ያለው ዛፍ በጥ​ላው ይሰ​ው​ረ​ዋል፤
የወ​ንዝ አኻያ ዛፎ​ችም ይከ​ብ​ቡ​ታል።
23እነሆ፥ ወንዙ ቢጐ​ርፍ አይ​ደ​ነ​ግ​ጥም፤
ዮር​ዳ​ኖ​ስም እስከ አፉ ድረስ ቢፈ​ስስ እርሱ ይተ​ማ​መ​ናል።
24ዐይኑ እያየ በገ​መድ ይያ​ዛ​ልን?
አፍ​ን​ጫ​ውስ ይበ​ሳ​ልን?
25“በውኑ ዘን​ዶ​ውን በመ​ቃ​ጥን ታወ​ጣ​ለ​ህን?
በአ​ፍ​ን​ጫ​ውስ ገመድ ታስ​ራ​ለ​ህን?
26ወይስ ስናጋ በጕ​ንጩ ታደ​ር​ጋ​ለ​ህን?
ወይስ በች​ን​ካር ከን​ፈ​ሩን ትበ​ሳ​ለ​ህን?
27በውኑ ወደ አንተ እጅግ ይለ​ም​ና​ልን?
በጣ​ፈጠ ቃልስ ይና​ገ​ር​ሃ​ልን?
28በውኑ ከአ​ንተ ጋር ቃል ኪዳን ይገ​ባ​ልን?
ወይስ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባሪያ ይሆን ዘንድ ትወ​ስ​ደ​ዋ​ለ​ህን?
29ከዎፍ ጋር እን​ደ​ም​ት​ጫ​ወት ከእ​ርሱ ጋር ትጫ​ወ​ታ​ለ​ህን?
ወይስ እንደ ልጆች መጫ​ወቻ ዎፍ ታስ​ረ​ዋ​ለ​ህን?
30 # በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ይለ​ያል። አሕ​ዛብ ይመ​ገ​ቡ​ታ​ልን?
ወይስ የፊ​ንቄ ሰዎች ይካ​ፈ​ሉ​ታ​ልን?#ግእዝ “ወአ​ሕ​ዛ​ብኒ ይት​ጋ​ነዩ ሎቱ ...” ይላል።
31ጀል​ባ​ዎች#ግእዝ “አዕ​ዋፍ” ይላል። ሁሉ ቢሰ​በ​ሰቡ የጅ​ራ​ቱን ቍር​በት ሊሸ​ከ​ሙት አይ​ች​ሉም።
አጥ​ማ​ጆ​ችም ራሱን በመ​ረብ መያዝ አይ​ች​ሉም።
32እጅ​ህን በላዩ ጫን፤
በአፉ#ግእዝ “በሥ​ጋሁ” ይላል። የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ጦር​ነት አስብ፥
እን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አት​ድ​ገም፥
አላ​የ​ህ​ምን? ስለ እር​ሱስ የተ​ባ​ለ​ውን አላ​ደ​ነ​ቅ​ህ​ምን?

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ