የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 21

21
ለሌ​ዋ​ው​ያን የተ​ሰጡ ከተ​ሞች
1የሌዊ ልጆች አለ​ቆች ወደ ካህኑ ወደ አል​ዓ​ዛር፥ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ሕዝብ አባ​ቶች ነገ​ዶች አለ​ቆች መጡ፤ 2በከ​ነ​ዓን ምድር ባለ​ችው በሴሎ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ የም​ን​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸ​ውን ከተ​ሞች፥ ለከ​ብ​ቶ​ቻ​ች​ንም መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎች ትሰ​ጡን ዘንድ አዝ​ዞ​አል” ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው። 3የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ከር​ስ​ታ​ቸው እነ​ዚ​ህን ከተ​ሞ​ችና መሰ​ማ​ር​ያ​ቸ​ውን ለሌ​ዋ​ው​ያን ሰጡ​አ​ቸው።
4ለቀ​ዓ​ትም ወገ​ኖች ልጆች ዕጣ ወጣ፤ ሌዋ​ው​ያ​ንም ለነ​በሩ ለካ​ህኑ ለአ​ሮን ልጆች ከይ​ሁዳ ነገድ፥ ከስ​ም​ዖ​ንም ነገድ፥ ከብ​ን​ያ​ምም ነገድ ዐሥራ ሦስት ከተ​ሞች በዕጣ ተሰ​ጡ​አ​ቸው።
5ለቀ​ሩ​ትም ለቀ​ዓት ልጆች ከኤ​ፍ​ሬም ነገድ፥ ከዳ​ንም ነገድ፥ ከም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ዐሥር ከተ​ሞች በዕጣ ተሰ​ጡ​አ​ቸው።
6ለጌ​ድ​ሶ​ንም ልጆች ከይ​ሳ​ኮር ነገድ፥ ከአ​ሴ​ርም ነገድ፥ ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምም ነገድ፥ በባ​ሳ​ንም ካለው ከም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ዐሥራ ሦስት ከተ​ሞች በዕጣ ተሰ​ጡ​አ​ቸው።
7ለሜ​ራ​ሪም ልጆች በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ከሮ​ቤል ነገድ፥ ከጋ​ድም ነገድ፥ ከዛ​ብ​ሎ​ንም ነገድ ዐሥራ ሁለት ከተ​ሞች ተሰ​ጡ​አ​ቸው።
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እነ​ዚ​ህን ከተ​ሞ​ችና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ለሌ​ዋ​ው​ያን በዕጣ ሰጡ። 9የይ​ሁ​ዳም ልጆች ነገድ፥ የስ​ም​ዖ​ንም ልጆች ነገድ፥ የብ​ን​ያ​ምም ልጆች ነገድ በስ​ማ​ቸው የተ​ጠ​ሩ​ትን እነ​ዚ​ህን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። 10የፊ​ተ​ኛው ዕጣ ለእ​ነ​ርሱ ስለ​ወጣ የሌዊ ልጆች የቀ​ዓት ወገን ለሆኑ ለአ​ሮን ልጆች ሆኑ። 11የኤ​ናቅ ልጆች ከተማ ቅር​ያ​ት​ያ​ር​ቦ​ቅ​ንና በዙ​ሪ​ያዋ ያሉ መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ችን ሰጡ​አ​ቸው፤ ይህ​ች​ውም በይ​ሁዳ ተራራ ያለች ኬብ​ሮን ናት። 12ኢያ​ሱም የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱን እርሻ መን​ደ​ሮ​ች​ዋ​ንም ለዮ​ፎኒ ልጅ ለካ​ሌብ ልጆች ርስት አድ​ርጎ ሰጣ​ቸው።
13ለካ​ህ​ኑም ለአ​ሮን ልጆች እነ​ዚ​ህን ሰጡ፤ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን ኬብ​ሮ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሌም​ና​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ 14ኤቴ​ር​ንና#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ኤሎም” ይላል። መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኤታ​ም​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ 15ሄሎ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ዳቤ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ 16አሳ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ዮጣ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቤት​ሳ​ሚ​ስ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ከእ​ነ​ዚህ ከሁ​ለቱ ነገ​ዶች ዘጠኝ ከተ​ሞ​ችን ሰጡ። 17ከብ​ን​ያ​ምም ነገድ ገባ​ዖ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ጋቲ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ 18ዓና​ቶ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ አል​ሞ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራት ከተ​ሞ​ችን ሰጡ። 19የካ​ህ​ናቱ የአ​ሮን ልጆች ከተ​ሞች ከመ​ሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ጋር ዐሥራ ሦስት ናቸው፤
20ለቀ​ሩ​ትም ለሌ​ዋ​ው​ያኑ ለቀ​ዓት ልጆች የዕ​ጣ​ቸው ከተ​ሞች ከኤ​ፍ​ሬም ነገድ ደረ​ሱ​አ​ቸው። 21#ዕብ. “በኤ​ፍ​ሬም ተራ​ራማ ሀገር” ይላል።ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን ሴኬ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ጌዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ 22ቄብ​ጻ​ይ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥#“ቄብ​ጻ​ይ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ቤቶ​ሮ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። 23ከዳ​ንም ነገድ ኤል​ቆ​ታ​ይ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ገባ​ቶ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ 24ኤሎ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ጌቴ​ራ​ሞ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። 25ከም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ጠና​ሕ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ዬባ​ታ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሁለ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። 26የቀ​ሩት የቀ​ዓት ልጆች ወገ​ኖች ከተ​ሞች ሁሉ ከመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ቸው ጋር ዐሥር ናቸው።
27ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ወገ​ኖች ለጌ​ድ​ሶን ልጆች ከም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ በባ​ሳን ውስጥ የሆ​ነ​ች​ውን ጎላ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቦሶ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሁለ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። 28ከይ​ሳ​ኮ​ርም ነገድ ቂሶ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ዳብ​ራ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ 29ሬማ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ዓይ​ን​ጋ​ኒ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። 30ከአ​ሴ​ርም ነገድ መሴ​ላ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ አቤ​ዶ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ 31ሔል​ቃ​ት​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ረዓ​ብ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱ​ንም ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። 32ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምም ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን በገ​ሊላ ውስጥ ቃዴ​ስ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኤማ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃር​ቴ​ን​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፤ ሦስ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው። 33የጌ​ድ​ሶን ልጆች ከተ​ሞች ሁሉ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ዐሥራ ሦስት ከተ​ሞች ከመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ቸው ጋር ናቸው።
34ከሌ​ዋ​ው​ያን ለቀ​ሩት ለሜ​ራሪ ልጆች ወገን ከዛ​ብ​ሎን ነገድ ዮቅ​ና​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃዴ​ስ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ 35ዲም​ና​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ሴላ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ። 36በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል ከሮ​ቤል ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ በሚ​ሶን ምድረ በዳ ቦሶ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኢያ​ዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ 37ቄዴ​ሞ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ሜፍ​ዐ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ። 38ከጋ​ድም ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን በገ​ለ​ዓድ ውስጥ ራሞ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃሚ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ 39ሐሴ​ቦ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኢያ​ዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ። 40ከሌዊ ወገ​ኖች የቀ​ሩት የሜ​ራሪ ልጆች ከተ​ሞች ሁሉ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ነበሩ፤ ዕጣ​ቸ​ውም ዐሥራ ሁለት ከተማ ነበረ።
41በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስት መካ​ከል የነ​በ​ሩት የሌ​ዋ​ው​ያን ከተ​ሞች ሁሉ በእ​ነ​ዚህ ከተ​ሞች ዙሪያ ካሉ ከመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ጋር አርባ ስም​ንት ከተ​ሞች ነበሩ። 42እነ​ዚ​ህም ከተ​ሞች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ቸው ጋር ነበሩ፤ እነ​ዚ​ህም ከተ​ሞች ሁሉ እን​ዲሁ ነበሩ። [ኢያ​ሱም በየ​ድ​ን​በ​ሮ​ቻ​ቸው ምድ​ርን ማካ​ፈ​ልን ጨረሰ። የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ለኢ​ያሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ድር​ሻ​ውን ሰጡት፤ እርሱ የሚ​ፈ​ል​ጋ​ትን ከተማ በኤ​ፍ​ሬም ተራራ የም​ት​ገ​ኘ​ውን ቴም​ና​ሴ​ራን ሰጡት፤ ከተ​ማም ሠራ​ባት፤ በው​ስ​ጧም ተቀ​መጠ። ኢያ​ሱም በም​ደረ በዳ በመ​ን​ገድ የተ​ወ​ለ​ዱ​ትን የገ​ረ​ዘ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ባል​ጩ​ቶች ወስዶ በቴ​ም​ና​ሴራ አኖ​ራ​ቸው።]#በቅ​ንፍ ውስጥ ያለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ብቻ።
እስ​ራ​ኤል ምድ​ሪ​ቱን ወር​ሰው ዕረ​ፍት እን​ዳ​ገኙ
43እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ምድር ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሰጠ፤ ወረ​ሱ​አ​ትም፥ ተቀ​መ​ጡ​ባ​ትም። 44እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው እንደ ማለ​ላ​ቸው በዙ​ሪ​ያ​ቸው ካሉት አሳ​ረ​ፋ​ቸው፤ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ይቋ​ቋ​ማ​ቸው ዘንድ ማንም ሰው አል​ቻ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ በእ​ጃ​ቸው አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው። 45እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ከተ​ና​ገ​ረው መል​ካም ነገር ሁሉ ተፈ​ጸመ እንጂ ምንም አል​ቀ​ረም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ