መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 7
7
የአካን በደል
1የእስራኤል ልጆች ግን እርም በሆነው ነገር ታላቅ በደል በደሉ፤ ከይሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እርሱም የከርሚ ልጅ፥ የዘንበሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ እርም ከሆነው ነገር ወሰደ፤ እግዚአብሔርም በእስራኤል ልጆች ላይ ተቈጣ።
2ኢያሱም ከቤቴል በምሥራቅ በኩል በቤትአዊን አጠገብ#“በቤት አዊን አጠገብ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ወዳለችው ወደ ጋይ ሰዎችን ከኢያሪኮ ልኮ፥ “ውጡ፤ ጋይንም ሰልሉ” ብሎ ተናገራቸው፤ ሰዎቹም ወጡ፤ ጋይንም ሰለሉ። 3ወደ ኢያሱም ተመልሰው፥ “ሁለት ወይም ሦስት ሺህ ያህል ሰው ወጥተው ጋይን ይምቱ እንጂ ሕዝቡ ሁሉ አይውጣ፤ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ሁሉ ግን ወደዚያ አትውሰድ፤ ጥቂቶች ናቸውና” አሉት። 4ሦስት ሺህ ያህል ሰዎችም ወደዚያ ወጡ፤ የጋይም ሰዎች አባረሩአቸው፤ ከፊታቸውም ሸሹ። 5የጋይ ሰዎችም ከእነርሱ ሠላሳ ስድስት ሰዎችን ገደሉ፤ ከበሩ ጀምረው እስከ አጠፉአቸው ድረስ አባረሩአቸው፤ በቍልቍለቱም ገደሉአቸው፤ የሕዝቡም ልብ ደነገጠ፤ እንደ ውኃም ሆነ።
6ኢያሱም ልብሱን ቀደደ፤ እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግንባራቸው ተደፉ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ። 7ኢያሱም አለ፥ “ወዮ! ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! በአሞሬዎናውያን እጅ አሳልፈህ ትሰጠን፥ ታጠፋንም ዘንድ አገልጋይህ ይህን ሕዝብ ዮርዳኖስን ለምን አሻገረ? በዮርዳኖስ ማዶ ተቀምጠን በኖርን ነበር እኮ! 8ጌታ ሆይ! እስራኤል ጀርባውን ወደ ጠላቶቹ ከመለሰ እንግዲህ ምን እላለሁ? 9ከነዓናውያንም፥ በምድሪቱም የሚኖሩ ሁሉ ሰምተው ይከብቡናል፤ ከምድርም ያጠፉናል፤ ለታላቁ ስምህም የምታደርገው ምንድር ነው?”
10እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው፥ “ለምን በግንባርህ ተደፍተሃል? ተነሥ! 11ሕዝቡ በድለዋል፤ ከእነርሱም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል፤ እርም ከሆነውም ነገር ሰርቀው ወሰዱ፤ በዕቃቸውም ውስጥ ሸሸጉት። 12ስለዚህም የእስራኤል ልጆች በጠላቶቻቸው ፊት መቆም አይችሉም፤ የተረገሙ ስለሆኑ በጠላቶቻቸው ፊት ይሸሻሉ፤ እርም የሆነውንም ነገር ከመካከላችሁ ካላጠፋችሁ ከዚህ በኋላ ከእናንተ ጋር አልሆንም። 13ተነሣና ሕዝቡን ቀድስ እንዲህም በላቸው፦ ‘እስራኤል ሆይ! እርም የሆነ ነገር በመካከልህ አለ፤ እርምም የሆነውን ነገር ከመካከላችሁ እስክታጠፉ ድረስ በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም’ ብሎ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ተናግሮአልና እስከ ነገ ራሳችሁን አንጹ። 14ነገም በየነገዳችሁ ትቀርባላችሁ፤ እግዚአብሔርም የሚለየው ነገድ በየወገኖቹ ይቀርባል፤ እግዚአብሔርም የሚለየው ወገን በየቤተ ሰቦቹ ይቀርባል፤ እግዚአብሔርም የሚለየው ቤተ ሰብ በየሰዉ ይቀርባል። 15ምልክት የታየበት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል አድርጎአልና፥ እርሱና ያለው ሁሉ በእሳት ይቃጠላሉ።”
16ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፤ እስራኤልንም በየነገዶቻቸው ሰበሰባቸው፤ በይሁዳም ነገድ ላይ ምልክት ታየ፤ 17የይሁዳም ወገኖች ተለዩ፤ በዛራም ወገን ምልክት ታየ፤ የዛራም ወገን በየቤተ ሰቡ ተለየ፤ 18በዘንበሪም ወገን ምልክት ታየ፤ የዘንበሪም ቤተ ሰብ እያንዳንዱ ተለየ፤ ከይሁዳም ወገን በሆነ በከርሚ ልጅ በዘንበሪ ልጅ በዛራ ልጅ በአካን ላይ ምልክት ታየ። 19ኢያሱም አካንን፥ “ልጄ ሆይ! ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብር ስጥ፤ ለእርሱም ተናዘዝ፤ ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ አትሸሽገኝም” አለው። 20አካንም መልሶ ኢያሱን፥ “በእውነት በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ፊት በድያለሁ፤ እንዲህና እንዲህም አድርጌአለሁ። 21በዘረፋ መካከል አንድ ያማረ ካባ፥ ሁለት መቶ ሰቅል ብር፥ ሚዛኑም አምሳ ሰቅል የሆነ ወርቅ አይቼ ተመኘኋቸው፤ ወሰድኋቸውም፤ እነሆም በድንኳኔ ውስጥ በመሬት ተሸሽገዋል፤ ብሩም ከሁሉ በታች ነው” አለው።
22ኢያሱም መልእክተኞችን ላከ፤ ወደ ሰፈርም ወደ ድንኳኑ ሮጡ፤ እነሆም እርሱ በድንኳኑ ውስጥ ተደብቆ፥ ብሩም በበታቹ ነበረ። 23ከድንኳኑም ውስጥ አውጥተው ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ አመጡት፤ በእግዚአብሔርምፊት አኖሩት። 24ኢያሱም#ዕብ. “እስራኤልም ሁሉ” የሚል ይጨምራል። የዛራን ልጅ አካንን፥ ብሩንም፥ ልብሱንም፥ ልሳነ ወርቁንም ወደ አኮር ሸለቆ ወሰዳቸው፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹንም፥ በሬዎቹንም፥ አህያዎቹንም፥ በጎቹንም፥ ድንኳኑንም፥ ንብረቱንም ሁሉ ወደ ዔሜቃኮር ወሰደ።#“ዔሜቃኮር” በዕብ. የአኮር ሽለቆ ማለት ነው። 25ኢያሱም፥ “ለምን አጠፋኸን? ዛሬ እንዳጠፋኸን እግዚአብሔር ዛሬ ያጥፋህ” አለው፤ እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፤ በእሳትም አቃጠሉት፤#“በእሳትም አቃጠሉት በድንጋይም ወገሩአቸው” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በድንጋይም ወገሩአቸው። 26በላዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩ፤ እግዚአብሔርም ከቍጣው መቅሠፍት ተመለሰ። ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ዔሜቃኮር ተብሎ ተጠራ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 7: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ