መዝሙረ ዳዊት 67
67
ለመዘምራን አለቃ የዳዊት የምስጋና መዝሙር።
1እግዚአብሔር ይነሣ፥ ጠላቶቹም ይበተኑ፥
የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።
2ጢስ እንደሚበንን እንዲሁ ይብነኑ፤
ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፥
እንዲሁ ኃጥኣን ከአግዚአብሔር ፊት ይጥፉ።
3ጻድቃን ግን ደስ ይበላቸው፥
በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤትን ያድርጉ፥
በደስታም ደስ ይበላቸው።
4እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ለስሙም ዘምሩ፤
ወደ ምዕራብ ለወጣው መንገድን አብጁ፤
ስሙ እግዚአብሔር ነው፥ በፊቱም ደስ ይበላችሁ፤
ከፊቱም የተነሣ ይደነግጣሉ።
5እግዚአብሔር በቅዱስ ቦታው
ለድሃ አደጎች አባት፥ ለባልቴቶችም ዳኛ ነው።
6እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤቱ ያሳድራቸዋል፥
እስረኞችንም በኀይሉ ያወጣቸዋል፤
በመቃብር የሚኖሩ ኀዘንተኞችንም#ዕብ. “ዐመፀኞች” ይላል። እንዲሁ።
7አቤቱ፥ በሕዝብህ ፊት በወጣህ ጊዜ፥
በምድረ በዳም ባለፍህ ጊዜ፥
8ከሲና አምላክ ፊት፥ ከእስራኤል አምላክ ፊት
ምድር ተናወጠች፥
ሰማያትም አንጠባጠቡ።
9አቤቱ፥ በፈቃድህ ዝናብን ለርስትህ ለየህ፥
በደከመም ጊዜ አንተ ታጸናዋለህ።
10እንስሶችህ በውስጡ ያድራሉ፤
አቤቱ፥ በቸርነትህ ለድሆች አዘጋጀህ።
11ብዙ ኀይልን ለሚያወሩ
እግዚአብሔር ቃሉን ሰጠ፤
12ለኀያላን ንጉሥ ለወዳጁ፤
ለወዳጁና ለቤትህ ውበት#ዕብ. “የሠራዊት ነገሥታት ፈጥነው ይሸሻሉ በቤትም የምትኖር” ይላል። ምርኮን ተካፈልን።
13በርስቶች መካከል ብታድሩ፥
ከብር እንደ ተሠሩ እንደ ርግብ ክንፎች፥
በቅጠልያ ወርቅም እንደ ተለበጡ ላባዎችዋ ትሆናላችሁ።
14ሰማያዊ ንጉሥ በላይዋ ባዘዘ ጊዜ፥#ዕብ. “ሁሉን ቻይ ሰማያዊ በላይዋ ነገሥታትን በበተነ ጊዜ” ይላል።
በሰልሞን ላይ በረዶ ይዘንማል።
15የእግዚአብሔር ተራራ የለመለመ ተራራ ነው፤
የጸና ተራራና የለመለመ ተራራ ነው።
16የጸኑ ተራራዎች ለምን ይነሣሉ?
እግዚአብሔር ያድርበት ዘንድ የወደደው ተራራ ይህ ነው፤
እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያድርባቸዋልና።#ዕብ. “ያድርባታል” ይላል።
17የብዙ ብዙ ሺህ የእግዚአብሔር ሰረገላዎች ደስተኞች ናቸው።
እግዚአብሔር በመቅደሱ በሲና በመካከላቸው ነው።
18ምርኮን ማርከህ ወደ ሰማይ ወጣህ
ስጦታህንም ለሰዎች ሰጠህ፥ ያድሩ ዘንድ ይክዱ ነበርና።#ዕብ. “ዳግምም ለዐመፀኞች በዚያ ያድሩ ዘንድ” ይላል።
19እግዚአብሔር አምላክ ቡሩክ ነው፤
እግዚአብሔር በየዕለቱ ቡሩክ ነው፤
አምላካችንና መድኃኒታችን ይረዳናል።
20አምላካችንስ የማዳን አምላክ ነው፤
የሞት መንገድ የእግዚአብሔር ነው።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከሞት መውጣት ከጌታ ከእግዚአብሔር ነው” ይላል።
21ነገር ግን እግዚአብሔር የጠላቶቹን ራስ ይሰብራል፥
በጠጉራቸው ጫፍም በደላቸው ይሄዳል።
22እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ ወጥቼ እመለሳለሁ፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከባሳን አመጣቸዋለሁ” ይላል።
በባሕሩም ጥልቅ እመለሳለሁ፥
23እግሮችህ በደም ይነከሩ ዘንድ፥
የውሾችህ ምላስ በጠላቶችህ ላይ ነው።
24አቤቱ፥ መንገድህ ተገለጠ።
የአምላካችን የንጉሡ መንገድ በመቅደሱ
25አለቆች ደረሱ፥ መዘምራንም አሏቸው
ከበሮን በሚመቱ በደናግል መካከል።
26እግዚአብሔርን በጉባኤ፥
አምላካችንንም በእስራኤል ምንጮች አመሰገኑት።
27ወጣቱ ብንያም በጉልበቱ በዚያ አለ፥
ገዦቻቸው የይሁዳ አለቆች፥
የዛብሎን አለቆችና የንፍታሌምም አለቆች።
28አቤቱ፥ በኀይልህ እዘዝ፤
አቤቱ፥ ይህን ለእኛ የሠራኸውን አጽናው።
29በኢየሩሳሌም ባለው መቅደስህ
ነገሥታት እጅ መንሻን ለአንተ ያመጣሉ።
30በቀርካሃ ውስጥ ያሉትን አራዊት፥
በሕዝብ ጊደሮች መካከል የበሬዎችን ጉባኤ ገሥጽ፥
እንደ ብር የተፈተኑት አሕዛብ እንዳይዘጉ፤
ሰልፍን የሚወድዱትን አሕዛብን በትናቸው።
31መልእክተኞች ከግብፅ ይምጡ፤
ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።
32የምድር ነገሥታት እግዚአብሔርን አመስግኑት፥
ለአምላካችንም ዘምሩ።
33በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤
የኀይል ቃል የሆነ ቃሉን፥ እነሆ፥ ይሰጣል።
34ለእግዚአብሔር ምስጋናን ስጡ፤
ግርማው በእስራኤል ላይ፥
ኀይሉም እስከ ደመናት ነው።
35እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው፤
የእስራኤል አምላክ እርሱ ኀይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል፤
እግዚአብሔር ይመስገን።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 67: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 67
67
ለመዘምራን አለቃ የዳዊት የምስጋና መዝሙር።
1እግዚአብሔር ይነሣ፥ ጠላቶቹም ይበተኑ፥
የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።
2ጢስ እንደሚበንን እንዲሁ ይብነኑ፤
ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፥
እንዲሁ ኃጥኣን ከአግዚአብሔር ፊት ይጥፉ።
3ጻድቃን ግን ደስ ይበላቸው፥
በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤትን ያድርጉ፥
በደስታም ደስ ይበላቸው።
4እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ለስሙም ዘምሩ፤
ወደ ምዕራብ ለወጣው መንገድን አብጁ፤
ስሙ እግዚአብሔር ነው፥ በፊቱም ደስ ይበላችሁ፤
ከፊቱም የተነሣ ይደነግጣሉ።
5እግዚአብሔር በቅዱስ ቦታው
ለድሃ አደጎች አባት፥ ለባልቴቶችም ዳኛ ነው።
6እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤቱ ያሳድራቸዋል፥
እስረኞችንም በኀይሉ ያወጣቸዋል፤
በመቃብር የሚኖሩ ኀዘንተኞችንም#ዕብ. “ዐመፀኞች” ይላል። እንዲሁ።
7አቤቱ፥ በሕዝብህ ፊት በወጣህ ጊዜ፥
በምድረ በዳም ባለፍህ ጊዜ፥
8ከሲና አምላክ ፊት፥ ከእስራኤል አምላክ ፊት
ምድር ተናወጠች፥
ሰማያትም አንጠባጠቡ።
9አቤቱ፥ በፈቃድህ ዝናብን ለርስትህ ለየህ፥
በደከመም ጊዜ አንተ ታጸናዋለህ።
10እንስሶችህ በውስጡ ያድራሉ፤
አቤቱ፥ በቸርነትህ ለድሆች አዘጋጀህ።
11ብዙ ኀይልን ለሚያወሩ
እግዚአብሔር ቃሉን ሰጠ፤
12ለኀያላን ንጉሥ ለወዳጁ፤
ለወዳጁና ለቤትህ ውበት#ዕብ. “የሠራዊት ነገሥታት ፈጥነው ይሸሻሉ በቤትም የምትኖር” ይላል። ምርኮን ተካፈልን።
13በርስቶች መካከል ብታድሩ፥
ከብር እንደ ተሠሩ እንደ ርግብ ክንፎች፥
በቅጠልያ ወርቅም እንደ ተለበጡ ላባዎችዋ ትሆናላችሁ።
14ሰማያዊ ንጉሥ በላይዋ ባዘዘ ጊዜ፥#ዕብ. “ሁሉን ቻይ ሰማያዊ በላይዋ ነገሥታትን በበተነ ጊዜ” ይላል።
በሰልሞን ላይ በረዶ ይዘንማል።
15የእግዚአብሔር ተራራ የለመለመ ተራራ ነው፤
የጸና ተራራና የለመለመ ተራራ ነው።
16የጸኑ ተራራዎች ለምን ይነሣሉ?
እግዚአብሔር ያድርበት ዘንድ የወደደው ተራራ ይህ ነው፤
እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያድርባቸዋልና።#ዕብ. “ያድርባታል” ይላል።
17የብዙ ብዙ ሺህ የእግዚአብሔር ሰረገላዎች ደስተኞች ናቸው።
እግዚአብሔር በመቅደሱ በሲና በመካከላቸው ነው።
18ምርኮን ማርከህ ወደ ሰማይ ወጣህ
ስጦታህንም ለሰዎች ሰጠህ፥ ያድሩ ዘንድ ይክዱ ነበርና።#ዕብ. “ዳግምም ለዐመፀኞች በዚያ ያድሩ ዘንድ” ይላል።
19እግዚአብሔር አምላክ ቡሩክ ነው፤
እግዚአብሔር በየዕለቱ ቡሩክ ነው፤
አምላካችንና መድኃኒታችን ይረዳናል።
20አምላካችንስ የማዳን አምላክ ነው፤
የሞት መንገድ የእግዚአብሔር ነው።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከሞት መውጣት ከጌታ ከእግዚአብሔር ነው” ይላል።
21ነገር ግን እግዚአብሔር የጠላቶቹን ራስ ይሰብራል፥
በጠጉራቸው ጫፍም በደላቸው ይሄዳል።
22እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ ወጥቼ እመለሳለሁ፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከባሳን አመጣቸዋለሁ” ይላል።
በባሕሩም ጥልቅ እመለሳለሁ፥
23እግሮችህ በደም ይነከሩ ዘንድ፥
የውሾችህ ምላስ በጠላቶችህ ላይ ነው።
24አቤቱ፥ መንገድህ ተገለጠ።
የአምላካችን የንጉሡ መንገድ በመቅደሱ
25አለቆች ደረሱ፥ መዘምራንም አሏቸው
ከበሮን በሚመቱ በደናግል መካከል።
26እግዚአብሔርን በጉባኤ፥
አምላካችንንም በእስራኤል ምንጮች አመሰገኑት።
27ወጣቱ ብንያም በጉልበቱ በዚያ አለ፥
ገዦቻቸው የይሁዳ አለቆች፥
የዛብሎን አለቆችና የንፍታሌምም አለቆች።
28አቤቱ፥ በኀይልህ እዘዝ፤
አቤቱ፥ ይህን ለእኛ የሠራኸውን አጽናው።
29በኢየሩሳሌም ባለው መቅደስህ
ነገሥታት እጅ መንሻን ለአንተ ያመጣሉ።
30በቀርካሃ ውስጥ ያሉትን አራዊት፥
በሕዝብ ጊደሮች መካከል የበሬዎችን ጉባኤ ገሥጽ፥
እንደ ብር የተፈተኑት አሕዛብ እንዳይዘጉ፤
ሰልፍን የሚወድዱትን አሕዛብን በትናቸው።
31መልእክተኞች ከግብፅ ይምጡ፤
ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።
32የምድር ነገሥታት እግዚአብሔርን አመስግኑት፥
ለአምላካችንም ዘምሩ።
33በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤
የኀይል ቃል የሆነ ቃሉን፥ እነሆ፥ ይሰጣል።
34ለእግዚአብሔር ምስጋናን ስጡ፤
ግርማው በእስራኤል ላይ፥
ኀይሉም እስከ ደመናት ነው።
35እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው፤
የእስራኤል አምላክ እርሱ ኀይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል፤
እግዚአብሔር ይመስገን።