መዝሙረ ዳዊት 68
68
ለመዘምራን አለቃ በመለከቶች የዳዊት መዝሙር
1አቤቱ፥ ውኃ እስከ ነፍሴ ደርሶብኛልና አድነኝ።
2በጥልቅ ረግረግ ጠለቅሁ ኀይልም የለኝም፤
ወደ ጥልቁ ባሕርም ደረስሁ ማዕበሉም አሰጠመኝ።
3በጩኸት ደከምሁ፥ ጉሮሮዬም ሻከረ፤#ዕብ. “ሰለለ” ይላል።
አምላኬን ተስፋ ሳደርግ ዐይኖቼ ፈዘዙ።
4በከንቱ የሚጠሉኝ ከራሴ ጠጉር በዙ፤
በዐመፅ የሚከብቡኝ#ዕብ. “የሚያሳድዱኝ” ይላል። ጠላቶቼ በረቱ፤
ያልወሰድሁትን ይከፈሉኛል።
5አቤቱ፥ አንተ ስንፍናዬን ታውቃለህ፥
ኃጢአቴም ከአንተ አልተሰወረም።
6አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ፥ የሚሹህ በእኔ አይፈሩ፤
የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ ተስፋ የሚያደርጉህ በእኔ አይነወሩ።
7ስለ አንተ ስድብን ታግሻለሁና፥
እፍረትም ፊቴን ሸፍኖኛልና።
8ለወንድሞቼ እንደ ባዕድ፥
ለአባቴና#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እናቴ ብቻ” ይላል። ለእናቴም ልጆች እንደ እንግዳ ሆንሁባቸው።
9የቤትህ ቅንዓት በልቶኛልና፥
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና።
10ሰውነቴን በጾም አደከምኋት፥
ስድብንም ሆነብኝ።
11ማቅ ለበስሁ መተረቻም ሆንሁላቸው።
12በደጅ የሚቀመጡ በእኔ ይጫወታሉ፤
ወይን የሚጠጡም በእኔ ይዘፍናሉ።
13እኔስ በጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ነኝ#ዕብራይስጥ ከግእዙና ከግሪኩ የአነጋገር ልዩነት አለው።
የእግዚአብሔር ይቅርታው በጊዜው ነው፤
ይቅርታህ ብዙ ሲሆን መድኃኒቴ ሆይ፥ በእውነት አድነኝ።
14እንዳይውጠኝ ከረግረግ አውጣኝ፤
ከጠላቶችና ከጥልቅ ውኃ አስጥለኝ።
15የውኃ ማዕበል አያስጥመኝ፥ ጥልቁም አይዋጠኝ፥
ጕድጓዶችም አፋቸውን በኔ ላይ አይክፈቱ፤
16አቤቱ፥ ምሕረትህ መልካም ናትና ስማኝ፤
እንደ ይቅርታህም ብዛት ወደ እኔ ተመልከት፤
17ከባሪያህም ፊትህን አትመልስ፤
ተጨንቄአለሁና ፈጥነህ ስማኝ።
18ነፍሴን ተመልክተህ ተቤዣት፤
ስለ ጠላቶችም አድነኝ።
19አንተ ስድቤን፥ እፍረቴንም፥
ነውሬንም ታውቃለህ፤
በሚያስጨንቁኝ ሁሉ ፊት።#ዕብ. “የሚያስጨንቁኝ ሁሉ በፊትህ ናቸው” ይላል።
20ሰውነቴ ስድብንና ውርደትን ታገሠች፤
አዝኜ ተቀመጥሁ፥ የሚያጽናናኝም አጣሁ።
21በመብሌ ውስጥ ሐሞትን ጨመሩ፥
ለጥማቴም ሆምጣጤን አጠጡኝ።
22ማዕዳቸው በፊታቸው
ለወጥመድ፥ ለፍዳና ለዕንቅፋት ትሁንባቸው፤
23ዐይኖቻቸው እንዳያዩ ይጨልሙ፥
ጀርባቸውም ዘወትር ይጉበጥ።
24መዓትህን በላያቸው አፍስስ፥
የቍጣህ መቅሠፍትም ያግኛቸው።
25ከተማቸው በረሃ ትሁን፥
በድንኳኖቻቸውም የሚቀመጥ አይገኝ፤
26አንተ የቀሠፍኸውን እነርሱ ተከትለዋልና፥
በቍስሌም ላይ ቍስልን ጨመሩብኝ።
27በኀጢአታቸው ላይ ኃጢአትን ጨምርባቸው፥
በጽድቅህም አይግቡ።
28ከሕያዋን መጽሐፍ ይደምሰሱ፥
ከጻድቃንም ጋር አይጻፉ።
29እኔ ድሃና ቍስለኛ ነኝ፤
የፊቴ፥ መድኀኒት እግዚአብሔር ተቀበለኝ።#ዕብ. “የፊትህ መድኀኒት ይቀበለኝ” ይላል።
30የእግዚአብሔርን ስም በዝማሬ አመሰግናለሁ፥
በምስጋናም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።
31ቀንድና ጥፍር ካላበቀለ ከእምቦሳ ይልቅ
እግዚአብሔርን ደስ አሰኘዋለሁ።
32ድሆች ይዩ ደስም ይበላቸው፤
እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ነፍሳችሁም ትድናለች።
33እግዚአብሔር ድሆችን ሰምቶእቸዋልና፥
እስረኞችንም አልናቃቸውምና።
34ሰማይና ምድር፥ ባሕርም፥
በእርስዋም የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ያመሰግኑታል።
35እግዚአብሔር ጽዮንን አድኗታልና፥#ዕብ. “ያድናታልና” ይላል።
የይሁዳም ከተሞች ይሠራሉና፤
በዚያም ይቀመጣሉ ይወርሷታልም።
36የባሪያዎችህ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የባሪያዎቹ” ይላል። ዘሮች ይኖሩባታል፥
ስምህን#ስሙን። የሚወድዱ በውስጧ ይቀመጣሉ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 68: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 68
68
ለመዘምራን አለቃ በመለከቶች የዳዊት መዝሙር
1አቤቱ፥ ውኃ እስከ ነፍሴ ደርሶብኛልና አድነኝ።
2በጥልቅ ረግረግ ጠለቅሁ ኀይልም የለኝም፤
ወደ ጥልቁ ባሕርም ደረስሁ ማዕበሉም አሰጠመኝ።
3በጩኸት ደከምሁ፥ ጉሮሮዬም ሻከረ፤#ዕብ. “ሰለለ” ይላል።
አምላኬን ተስፋ ሳደርግ ዐይኖቼ ፈዘዙ።
4በከንቱ የሚጠሉኝ ከራሴ ጠጉር በዙ፤
በዐመፅ የሚከብቡኝ#ዕብ. “የሚያሳድዱኝ” ይላል። ጠላቶቼ በረቱ፤
ያልወሰድሁትን ይከፈሉኛል።
5አቤቱ፥ አንተ ስንፍናዬን ታውቃለህ፥
ኃጢአቴም ከአንተ አልተሰወረም።
6አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ፥ የሚሹህ በእኔ አይፈሩ፤
የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ ተስፋ የሚያደርጉህ በእኔ አይነወሩ።
7ስለ አንተ ስድብን ታግሻለሁና፥
እፍረትም ፊቴን ሸፍኖኛልና።
8ለወንድሞቼ እንደ ባዕድ፥
ለአባቴና#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እናቴ ብቻ” ይላል። ለእናቴም ልጆች እንደ እንግዳ ሆንሁባቸው።
9የቤትህ ቅንዓት በልቶኛልና፥
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና።
10ሰውነቴን በጾም አደከምኋት፥
ስድብንም ሆነብኝ።
11ማቅ ለበስሁ መተረቻም ሆንሁላቸው።
12በደጅ የሚቀመጡ በእኔ ይጫወታሉ፤
ወይን የሚጠጡም በእኔ ይዘፍናሉ።
13እኔስ በጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ነኝ#ዕብራይስጥ ከግእዙና ከግሪኩ የአነጋገር ልዩነት አለው።
የእግዚአብሔር ይቅርታው በጊዜው ነው፤
ይቅርታህ ብዙ ሲሆን መድኃኒቴ ሆይ፥ በእውነት አድነኝ።
14እንዳይውጠኝ ከረግረግ አውጣኝ፤
ከጠላቶችና ከጥልቅ ውኃ አስጥለኝ።
15የውኃ ማዕበል አያስጥመኝ፥ ጥልቁም አይዋጠኝ፥
ጕድጓዶችም አፋቸውን በኔ ላይ አይክፈቱ፤
16አቤቱ፥ ምሕረትህ መልካም ናትና ስማኝ፤
እንደ ይቅርታህም ብዛት ወደ እኔ ተመልከት፤
17ከባሪያህም ፊትህን አትመልስ፤
ተጨንቄአለሁና ፈጥነህ ስማኝ።
18ነፍሴን ተመልክተህ ተቤዣት፤
ስለ ጠላቶችም አድነኝ።
19አንተ ስድቤን፥ እፍረቴንም፥
ነውሬንም ታውቃለህ፤
በሚያስጨንቁኝ ሁሉ ፊት።#ዕብ. “የሚያስጨንቁኝ ሁሉ በፊትህ ናቸው” ይላል።
20ሰውነቴ ስድብንና ውርደትን ታገሠች፤
አዝኜ ተቀመጥሁ፥ የሚያጽናናኝም አጣሁ።
21በመብሌ ውስጥ ሐሞትን ጨመሩ፥
ለጥማቴም ሆምጣጤን አጠጡኝ።
22ማዕዳቸው በፊታቸው
ለወጥመድ፥ ለፍዳና ለዕንቅፋት ትሁንባቸው፤
23ዐይኖቻቸው እንዳያዩ ይጨልሙ፥
ጀርባቸውም ዘወትር ይጉበጥ።
24መዓትህን በላያቸው አፍስስ፥
የቍጣህ መቅሠፍትም ያግኛቸው።
25ከተማቸው በረሃ ትሁን፥
በድንኳኖቻቸውም የሚቀመጥ አይገኝ፤
26አንተ የቀሠፍኸውን እነርሱ ተከትለዋልና፥
በቍስሌም ላይ ቍስልን ጨመሩብኝ።
27በኀጢአታቸው ላይ ኃጢአትን ጨምርባቸው፥
በጽድቅህም አይግቡ።
28ከሕያዋን መጽሐፍ ይደምሰሱ፥
ከጻድቃንም ጋር አይጻፉ።
29እኔ ድሃና ቍስለኛ ነኝ፤
የፊቴ፥ መድኀኒት እግዚአብሔር ተቀበለኝ።#ዕብ. “የፊትህ መድኀኒት ይቀበለኝ” ይላል።
30የእግዚአብሔርን ስም በዝማሬ አመሰግናለሁ፥
በምስጋናም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።
31ቀንድና ጥፍር ካላበቀለ ከእምቦሳ ይልቅ
እግዚአብሔርን ደስ አሰኘዋለሁ።
32ድሆች ይዩ ደስም ይበላቸው፤
እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ነፍሳችሁም ትድናለች።
33እግዚአብሔር ድሆችን ሰምቶእቸዋልና፥
እስረኞችንም አልናቃቸውምና።
34ሰማይና ምድር፥ ባሕርም፥
በእርስዋም የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ያመሰግኑታል።
35እግዚአብሔር ጽዮንን አድኗታልና፥#ዕብ. “ያድናታልና” ይላል።
የይሁዳም ከተሞች ይሠራሉና፤
በዚያም ይቀመጣሉ ይወርሷታልም።
36የባሪያዎችህ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የባሪያዎቹ” ይላል። ዘሮች ይኖሩባታል፥
ስምህን#ስሙን። የሚወድዱ በውስጧ ይቀመጣሉ።