የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 71

71
ስለ ሰሎ​ሞን።
1አቤቱ፥ ፍር​ድ​ህን ለን​ጉሥ ስጠው፥
ጽድ​ቅ​ህ​ንም ለን​ጉሥ ልጅ፥
2ሕዝ​ብ​ህን በጽ​ድቅ፥
ድሆ​ች​ህ​ንም በፍ​ርድ ይዳኝ ዘንድ።
3ተራ​ሮ​ችና ኮረ​ብ​ቶች የሕ​ዝ​ብ​ህን ሰላም ይቀ​በሉ።
4ለድ​ሆች ሕዝ​ብህ በጽ​ድቅ ፍረድ፥
የድ​ሆ​ች​ንም ልጆች አድ​ና​ቸው።
ትዕ​ቢ​ተ​ኛ​ው​ንም አዋ​ር​ደው።
5ፀሐይ በሚ​ኖ​ር​በት ዘመን ሁሉ፥
በጨ​ረ​ቃም ፊት ለልጅ ልጅ ይኑር።
6እንደ ጠል በባ​ዘቶ ላይ፥
በም​ድ​ርም ላይ እን​ደ​ሚ​ን​ጠ​ባ​ጠብ ጠብታ ይወ​ር​ዳል።
7በዘ​መ​ኑም ጽድቅ ይበ​ቅ​ላል፥
ጨረ​ቃም እስ​ኪ​ያ​ልፍ ድረስ ሰላም ብዙ ነው።
8ከባ​ሕር እስከ ባሕር ድረስ፥
ከወ​ን​ዝም እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ይገ​ዛል።
9በፊ​ቱም ኢት​ዮ​ጵያ ይሰ​ግ​ዳሉ፥
ጠላ​ቶ​ቹም አፈ​ርን ይል​ሳሉ።
10የተ​ር​ሴ​ስና የደ​ሴ​ቶች ነገ​ሥ​ታት ስጦ​ታን ያመ​ጣሉ፤
የሳ​ባና የዓ​ረብ ነገ​ሥ​ታት እጅ መን​ሻን ያመ​ጣሉ፤
11የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል ፥
አሕ​ዛ​ብም ሁሉ ይገ​ዙ​ለ​ታል።
12ድሃ​ውን ከሚ​ቀ​ማው እጅ፥
ረዳት የሌ​ለ​ው​ንም ምስ​ኪን ያድ​ነ​ዋ​ልና።
13ለድ​ሃና ለም​ስ​ኪን ይራ​ራል፥
የድ​ሆ​ች​ንም ነፍስ ያድ​ናል።
14ከአ​ራ​ጣና ከቅ​ሚያ ነፍ​ሳ​ቸ​ውን ያድ​ና​ታል፤
ስሙም በፊ​ታ​ቸው ክቡር ነው።
15እርሱ ይኖ​ራል፥ ከዓ​ረ​ብም ወር​ቅን ይሰ​ጡ​ታል፤
ሁል​ጊ​ዜም ስለ እርሱ ይጸ​ል​ያሉ፥
ዘወ​ት​ርም ይመ​ር​ቁ​ታል።
16በተ​ራ​ሮች ራስ ላይ ለም​ድር ሁሉ መጠ​ጊያ ይሆ​ናል፤
ፍሬ​ውም ከሊ​ባ​ኖስ ዛፍ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል፤
እንደ ምድር ሣር በከ​ተማ ይበ​ቅ​ላል።
17ስሙ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቡሩክ ነው፥
ከፀ​ሓ​ይም አስ​ቀ​ድሞ ስሙ ነበረ፤
የም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ በእ​ርሱ ይባ​ረ​ካሉ፥
ሕዝቡ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።
18ብቻ​ውን ተአ​ም​ራ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ
የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።
19የም​ስ​ጋ​ናው ስም ለዓ​ለ​ምና ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይባ​ረክ፤
ምስ​ጋ​ና​ውም ምድ​ርን ሁሉ ይምላ።
ይሁን፤ ይሁን።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የእ​ሴይ ልጅ የዳ​ዊት መዝ​ሙር ተፈ​ጸመ” የሚል ይጨ​ም​ራሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ