ዘፀአት 12:26-27
ዘፀአት 12:26-27 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እንዲህም ይሆናል፤ ልጆቻችሁ፥ ‘ይህ አምልኮ ለእናንተ ምንድር ነው?’ ባሉአችሁ ጊዜ፥ እናንተ፦ ‘በግብፅ አገር በእስራኤል ልጆች ቤቶች ላይ አልፎ ግብፃዊያንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶቻችንን ያዳነ የእግዚአብሔር የማለፉ መሥዋዕት ይህች ናት’ ትሉአቸዋላችሁ።” ሕዝቡም ተጎነበሰ ሰገደም።
Share
ዘፀአት 12 ያንብቡዘፀአት 12:26-27 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ልጆቻችሁ፦ ‘ይህ ሥርዐት ለእናንተ ምንድር ነው?’ ባሉአችሁ ጊዜ እናንተ፦ ‘ይህ በግብፅ ሀገር የእስራኤልን ልጆች ቤቶች ሰውሮ ግብፃውያንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶቻችንን የአዳነ የእግዚአብሔር የፋሲካው መሥዋዕት ነው’ ትሉአቸዋላችሁ።” ሕዝቡም ተጐነበሱ፤ ሰገዱም።
Share
ዘፀአት 12 ያንብቡ