ኤርምያስ 20:8-9
ኤርምያስ 20:8-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በተናገርሁ ቍጥር እጮኻለሁ፤ ግፍና ጥፋት ብዬ እጠራለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ቀኑን ሁሉ ስድብና ዋዛ ሆኖብኛልና። እኔም እንዲህ አልሁ፥ “የእግዚአብሔርን ስም አላነሣም፤ ከእንግዲህ ወዲህ በስሙ አልናገርም፥” በአጥንቶች ውስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ፤ ደከምሁ፤ መሸከምም አልቻልሁም።
ኤርምያስ 20:8-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በተናገርሁ ቍጥር እጮኻለሁ፤ “ሁከትና ጥፋት!” ብዬ ዐውጃለሁ፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል፣ ቀኑን ሙሉ ስድብና ነቀፋ አስከተለብኝ። ነገር ግን፣ “ከእንግዲህ የርሱን ስም አላነሣም፤ በስሙም አልናገርም” ብል፣ ቃሉ በልቤ እንደ እሳት፣ በዐጥንቴም ውስጥ እንደ ረመጥ ሆነብኝ፤ ዐፍኜ መያዝ አቃተኝ፤ ጨርሶ መቋቋም አልቻልሁም።
ኤርምያስ 20:8-9 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በተናገርሁ ቍጥር እጮኻለሁ፥ ግፍና ጥፋት ብዬ እጮኻለሁ፥ የእግዚአብሔር ቃል ቀኑን ሁሉ ስድብና ዋዛ ሆኖብኛልና። እኔም፦ የእግዚአብሔርን ስም አላነሣም፥ ከእንግዲህ ወዲህም በስሙ አልናገርም ብል፥ በአጥንቶቼ ውስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ፥ ደከምሁ፥ መሸከምም አልቻልሁም።