ኤርምያስ 23:5-6
ኤርምያስ 23:5-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“እነሆ ለዳዊት የጽድቅ ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥” ይላል እግዚአብሔር፤ ንጉሥ ይነግሣል፤ ያስባል፤ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል። በዘመኑም ይሁዳ ይድናል፤ እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፤ ይህም ስም እግዚአብሔር በነቢያት ኢዮሴዴቅ ብሎ የጠራው ነው።
ኤርምያስ 23:5-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“እነሆ፤ ለዳዊት፣ ጻድቅ ቅርንጫፍ የማስነሣበት ጊዜ ይመጣል፤ እርሱም ፍትሕንና ጽድቅን የሚያደርግ፣ በጥበብ የሚገዛ ንጉሥ ይሆናል” ይላል እግዚአብሔር። በርሱም ዘመን ይሁዳ ይድናል፤ እስራኤልም ያለ ሥጋት ይኖራል፤ የሚጠራበትም ስም፣ “እግዚአብሔር ጽድቃችን” የሚል ይሆናል።
ኤርምያስ 23:5-6 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እርሱም እንደ ንጉሥ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል። በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ የሚጠራበትም ስም፦ እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው።