1
ዘፀአት 6:6
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
“ስለዚህ ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‘እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ፤ ከግብፃውያን ቀንበር አወጣችኋለሁ። ለእነርሱ ባሪያ ከመሆን ነጻ አወጣችኋለሁ፤ በተዘረጋች ክንድና በታላቅ ፍርድ እቤዣችኋለሁ።
قارن
اكتشف ዘፀአት 6:6
2
ዘፀአት 6:7
የራሴ ሕዝብ አደርጋችኋለሁ፤ እኔም አምላክ (ኤሎሂም) እሆናችኋለሁ ከግብፃውያን ቀንበር ያላቀቅኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) መሆኔንም ታውቃላችሁ።
اكتشف ዘፀአት 6:7
3
ዘፀአት 6:8-9
ከዚያም ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ እሰጣችኋለሁ ብዬ ወደማልሁላቸው ምድር አመጣችኋለሁ፤ ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ። እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ” ሙሴ ይህን ለእስራኤላውያን ነገራቸው፤ ተስፋ ከመቍረጣቸውና ከአስከፊ እስራታቸው የተነሣ ግን አላዳመጡትም።
اكتشف ዘፀአት 6:8-9
4
ዘፀአት 6:1
ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “አሁን በፈርዖን ላይ የማደርገውን ታያለህ፤ ከኀያሉ እጄ የተነሣ እንዲሄዱ ይለቅቃቸዋል፤ ከኀያሉም እጄ የተነሣ ከአገሩ ያስወጣቸዋል” አለው።
اكتشف ዘፀአት 6:1
الصفحة الرئيسية
الكتاب المقدس
خطط
فيديوهات