1
ዘፍጥረት 35:11-12
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ደግሞም እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “እኔ ሁሉን ማድረግ የሚችል አምላክ ነኝ፤ ብዛ ተባዛ፤ ሕዝብና የሕዝቦች ማኅበር ከአንተ ይወጣሉ፤ ነገሥታትም ከአብራክህ ይከፈላሉ። ለአብርሃምና ለይስሐቅ የሰጠኋትን ምድር ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ ከአንተም በኋላ ይህችኑ ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ።”
قارن
اكتشف ዘፍጥረት 35:11-12
2
ዘፍጥረት 35:3
ተነሥተን ወደ ቤቴል እንውጣ፤ እዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፣ በሄድሁበትም ስፍራ ሁሉ ላልተለየኝ አምላክ (ኤል) መሠዊያ እሠራለሁ።”
اكتشف ዘፍጥረት 35:3
3
ዘፍጥረት 35:10
እግዚአብሔርም (ኤሎሂም)፣ “እስካሁን ስምህ ያዕቆብ ነበረ፤ ከእንግዲህ ያዕቆብ ተብለህ አትጠራም፤ ነገር ግን ስምህ እስራኤል ይባላል” አለው። ስለዚህም እስራኤል ብሎ ጠራው።
اكتشف ዘፍጥረት 35:10
4
ዘፍጥረት 35:2
ስለዚህም ያዕቆብ ለቤቱ ሰዎችና አብረውት ለነበሩት ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “በእናንተ ዘንድ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ሰውነታችሁን አንጹ፤ ልብሳችሁንም ለውጡ።
اكتشف ዘፍጥረት 35:2
5
ዘፍጥረት 35:1
እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ያዕቆብን፣ “ተነሥና ወደ ቤቴል ውጣ፤ እዚያም ተቀመጥ፤ ከወንድምህ ከዔሳው ሸሽተህ በሄድህ ጊዜ ለተገለጠልህ አምላክ (ኤል) በዚያ መሠዊያ ሥራ” አለው።
اكتشف ዘፍጥረት 35:1
6
ዘፍጥረት 35:18
እርሷ ግን ሕይወቷ ልታልፍ በማጣጣር ላይ ሳለች፣ ልጇን ቤንኦኒ አለችው፤ አባቱ ግን ብንያም አለው።
اكتشف ዘፍጥረት 35:18
الصفحة الرئيسية
الكتاب المقدس
خطط
فيديوهات