1
ዘፍጥረት 37:5
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ዮሴፍም ሕልም ዐለመ፤ ሕልሙንም ለወንድሞቹ ሲነግራቸው የባሰ ጠሉት።
قارن
اكتشف ዘፍጥረት 37:5
2
ዘፍጥረት 37:3
እስራኤል ዮሴፍን በስተርጅናው ስለ ወለደው፣ ከልጆቹ ሁሉ አብልጦ ይወድደው ነበር፤ በኅብረ ቀለማት ያጌጠ እጀ ጠባብም አደረገለት።
اكتشف ዘፍጥረት 37:3
3
ዘፍጥረት 37:4
ወንድሞቹም፣ አባታቸው ከእነርሱ አብልጦ የሚወድደው መሆኑን ሲያዩ፣ ዮሴፍን ጠሉት፤ በቅን አንደበትም ሊያናግሩት አልቻሉም።
اكتشف ዘፍጥረት 37:4
4
ዘፍጥረት 37:9
እንደ ገናም ሌላ ሕልም ዐለመ፤ ለወንድሞቹም፣ “እነሆ፤ ሌላ ሕልም ዐለምሁ፤ ፀሓይና ጨረቃ፣ ዐሥራ አንድ ከዋክብትም ሲሰግዱልኝ አየሁ” ብሎ ነገራቸው።
اكتشف ዘፍጥረት 37:9
5
ዘፍጥረት 37:11
ወንድሞቹ ቀኑበት፤ አባቱ ግን ነገሩን በልቡ ያዘው።
اكتشف ዘፍጥረት 37:11
6
ዘፍጥረት 37:6-7
እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ያየሁትን ሕልም ልንገራችሁ አድምጡኝ እኛ ሁላችን በዕርሻ ውስጥ ነዶ እናስር ነበር፤ የእኔ ነዶ በድንገት ተነሥታ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእናንተም ነዶዎች ዙሪያዋን ከብበው ለእኔ ነዶ ሰገዱላት።”
اكتشف ዘፍጥረት 37:6-7
7
ዘፍጥረት 37:20
ኑ እንግደለውና ከጕድጓዶቹ በአንዱ ውስጥ እንጣለው፤ ከዚያም፣ ‘ክፉ አውሬ ነጥቆ በላው’ እንላለን፤ እስቲ ሕልሞቹ ሲፈጸሙ እናያለን።”
اكتشف ዘፍጥረት 37:20
8
ዘፍጥረት 37:28
የምድያም ነጋዴዎችም እነርሱ ዘንድ እንደ ደረሱ፣ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጕድጓድ አውጥተው ለእስማኤላውያን በሃያ ጥሬ ብር ሸጡላቸው፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት።
اكتشف ዘፍጥረት 37:28
9
ዘፍጥረት 37:19
እነርሱም እንዲህ ተባባሉ፤ “ያ ሕልም ዐላሚ መጣ፤
اكتشف ዘፍጥረት 37:19
10
ዘፍጥረት 37:18
ወንድሞቹም ዮሴፍ ወደ እነርሱ ሲመጣ በሩቅ አዩት፤ ወደ ነበሩበትም ስፍራ ከመድረሱ በፊት ሊገድሉት ተማከሩ።
اكتشف ዘፍጥረት 37:18
11
ዘፍጥረት 37:22
የሰው ደም አታፍስሱ፤ እዚህ ምድረ በዳ፣ ጕድጓድ ውስጥ ጣሉት እንጂ እጃችሁን አታንሡበት።” ሮቤል ይህን ያለው ሕይወቱን ከእጃቸው አትርፎ ወደ አባቱ ሊመልሰው አስቦ ነበር።
اكتشف ዘፍጥረት 37:22
الصفحة الرئيسية
الكتاب المقدس
خطط
فيديوهات