1
የሉቃስ ወንጌል 17:19
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
እርሱንም፥ “ተነሥና ሂድ፤ እምነትህ አዳነችህ” አለው።
قارن
اكتشف የሉቃስ ወንጌል 17:19
2
የሉቃስ ወንጌል 17:4
በየቀኑ ሰባት ጊዜ ቢበድልም ሰባት ጊዜ ከተጸጸተ ይቅር በለው።”
اكتشف የሉቃስ ወንጌል 17:4
3
የሉቃስ ወንጌል 17:15-16
ከእነርሱም አንዱ እንደ ነጻ ባየ ጊዜ፥ በታላቅ ቃል እያመሰገነ ተመለሰ። በግንባሩም ወድቆ ከጌታችን ከኢየሱስ እግር በታች ሰገደና አመሰገነው፤ ሰውየውም ሳምራዊ ነበር።
اكتشف የሉቃስ ወንጌል 17:15-16
4
የሉቃስ ወንጌል 17:3
ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወንድምህ አንተን ቢበድል ብቻህን ምከረው፤ ቢጸጸት ግን ይቅር በለው።
اكتشف የሉቃስ ወንጌል 17:3
5
የሉቃስ ወንጌል 17:17
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፤ “የነጹ ዐሥር አልነበሩምን? እንግዲህ ዘጠኙ የት አሉ?
اكتشف የሉቃስ ወንጌል 17:17
6
የሉቃስ ወንጌል 17:6
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት ብትኖራችሁ ይህችን ሾላ ከሥርሽ ተነቅለሽ በባሕር ውስጥ ተተከዪ ብትሉአት ትታዘዝላችኋለች።”
اكتشف የሉቃስ ወንጌል 17:6
7
የሉቃስ ወንጌል 17:33
ነፍሱን ሊያድናት የሚወድ ይጣላት፤ ስለ እኔ ነፍሱን የሚጥላትም ያድናታል።
اكتشف የሉቃስ ወንጌል 17:33
8
የሉቃስ ወንጌል 17:1-2
ጌታችን ኢየሱስም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፥ “መሰናክል ግድ ይመጣል፤ ነገር ግን መሰናክልን ለሚያመጣት ሰው ወዮለት። ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ከሚያሰናክል ይልቅ አህያ የሚፈጭበት የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር ቢሰጥም በተሻለው ነበር።
اكتشف የሉቃስ ወንጌል 17:1-2
9
የሉቃስ ወንጌል 17:26-27
በኖኅ ዘመን እንደ ሆነው የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ እንዲሁ ይሆናል። ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ ሲበሉና ሲጠጡ፥ ሲያገቡና ሲጋቡ ነበረ፤ የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን አንድ አድርጎ አጠፋ።
اكتشف የሉቃስ ወንጌል 17:26-27
الصفحة الرئيسية
الكتاب المقدس
خطط
فيديو