1
የሉቃስ ወንጌል 8:15
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
በመልካም ምድር የወደቀው ግን ቃሉን በበጎና በንጹሕ ልብ የሚሰሙና የሚጠብቁት፥ ታግሠውና ጨክነውም የሚያፈሩ ናቸው።
قارن
اكتشف የሉቃስ ወንጌል 8:15
2
የሉቃስ ወንጌል 8:14
በእሾህም መካከል የወደቀው ቃሉን ሰምተው የባለጠግነት ዐሳብ፥ የኑሮም መቈርቈር የተድላና የደስታ መጣፈጥም የሚአስጨንቃቸውና ፍሬ የማያፈሩ ናቸው።
اكتشف የሉቃስ ወንጌል 8:14
3
የሉቃስ ወንጌል 8:13
በጭንጫም ላይ የወደቀው ሰምተው ነገሩን በደስታ የሚቀበሉት ናቸው፤ ነገር ግን ለጊዜው ያምናሉ እንጂ ሥር የላቸውም፤ መከራም በአገኛቸው ጊዜ ይክዳሉ።
اكتشف የሉቃስ ወንጌል 8:13
4
የሉቃስ ወንጌል 8:25
እርሱም “እምነታችሁ ወዴት አለ?” አላቸው፤ እነርሱም ፈርተው ተደነቁ፤ እርስ በርሳቸውም፥ “ውኃም ነፋስም የሚታዘዙለት ይህ ማነው?” አሉ።
اكتشف የሉቃስ ወንጌል 8:25
5
የሉቃስ ወንጌል 8:12
በመንገድ የወደቀው ቃሉን የሚሰሙ ናቸው፤ አምነውም እንዳይድኑ ሰይጣን መጥቶ ቃሉን ከልባቸው ይወስድባቸዋል።
اكتشف የሉቃስ ወንጌል 8:12
6
የሉቃስ ወንጌል 8:17
የማይገለጥ የተሰወረ የለምና፤ የማይታይም ወደ ግልጥም የማይመጣ የተከደነ የለም፤
اكتشف የሉቃስ ወንጌል 8:17
7
የሉቃስ ወንጌል 8:47-48
ሴቲቱም እንዳልተሰወረላት ባየች ጊዜ እየተንቀጠቀጠች ሄዳ ሰገደችለት፤ በሕዝቡም ሁሉ ፊት በምን ምክንያት ወደ እርሱ እንደ ቀረበችና የልብሱን ጫፍ እንደ ዳሰሰች ወዲያውም እንደ ዳነች ተናገረች። እርሱም፥ “ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አዳነችሽ፤ በሰላም ሂጂ” አላት።
اكتشف የሉቃስ ወንጌል 8:47-48
8
የሉቃስ ወንጌል 8:24
ቀርበውም፥ “መምህር ሆይ፥ መምህር ሆይ፥ ልንጠፋ ነው” ብለው ቀሰቀሱት፤ ተነሥቶም ነፋሱንና የውኃዉን ማዕበል ገሠጻቸው፤ እነርሱም ዝም አሉ፤ ታላቅ ፀጥታም ሆነ።
اكتشف የሉቃስ ወንጌል 8:24
الصفحة الرئيسية
الكتاب المقدس
خطط
فيديو