1
2 ቆሮንቶስ 5:17
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር ዐልፏል፤ እነሆ፤ አዲስ ሆኗል።
Compare
Explore 2 ቆሮንቶስ 5:17
2
2 ቆሮንቶስ 5:21
እኛ በርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን፣ ኀጢአት የሌለበትን እርሱን እግዚአብሔር ስለ እኛ ኀጢአት አደረገው።
Explore 2 ቆሮንቶስ 5:21
3
2 ቆሮንቶስ 5:7
ምክንያቱም የምንኖረው በእምነት እንጂ በማየት አይደለም።
Explore 2 ቆሮንቶስ 5:7
4
2 ቆሮንቶስ 5:18-19
ይህ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ እርሱ በክርስቶስ አማካይነት ከራሱ ጋራ አስታረቀን፤ የማስታረቅንም አገልግሎት ሰጠን፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋራ ሲያስታርቅ የሰዎችን በደል አይቈጥርባቸውም ነበር፤ ለእኛም ደግሞ የማስታረቅ ቃል ሰጠን።
Explore 2 ቆሮንቶስ 5:18-19
5
2 ቆሮንቶስ 5:20
ስለዚህ እኛ የክርስቶስ እንደራሴዎች ነን፤ እግዚአብሔርም በእኛ አማካይነት ጥሪውን ያቀርባል፤ እኛም ከእግዚአብሔር ጋራ ታረቁ ብለን በክርስቶስ እንለምናችኋለን።
Explore 2 ቆሮንቶስ 5:20
6
2 ቆሮንቶስ 5:15-16
በሕይወት ያሉትም ለሞተላቸውና ከሙታን ለተነሣላቸው እንጂ ከእንግዲህ ለራሳቸው እንዳይኖሩ እርሱ ስለ ሁሉ ሞተ። ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በውጫዊ ነገር አንመዝንም፤ ከዚህ ቀደም ክርስቶስን በዚህ መልክ መዝነነው ነበር፤ ከእንግዲህ ግን እንደዚህ አናደርግም።
Explore 2 ቆሮንቶስ 5:15-16
7
2 ቆሮንቶስ 5:14
የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ ምክንያቱም አንዱ ስለ ሁሉ እንደ ሞተ ርግጠኞች ሆነናል፣ ከዚህም የተነሣ ሁሉ ሞተዋል።
Explore 2 ቆሮንቶስ 5:14
Home
Bible
Plans
Videos