1
ኢሳይያስ 41:10
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ። አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ።
Compare
Explore ኢሳይያስ 41:10
2
ኢሳይያስ 41:13
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀኝ እጅህን እይዛለሁና አትፍራ ይልሃል፤ እረዳሃለሁ።
Explore ኢሳይያስ 41:13
3
ኢሳይያስ 41:11
“እነሆ፤ የተቈጡህ ሁሉ፣ እጅግ ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉም፤ የሚቋቋሙህ፣ እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ ይጠፋሉም።
Explore ኢሳይያስ 41:11
4
ኢሳይያስ 41:9
ከምድር ዳርቻ ያመጣሁህ፣ ከአጥናፍም የጠራሁህ፣ ‘አንተ ባሪያዬ ነህ’ ያልሁህ፤ መረጥሁህ እንጂ አልጣልሁህም።
Explore ኢሳይያስ 41:9
5
ኢሳይያስ 41:12
ጠላቶችህን ብትፈልጋቸው እንኳ፣ አታገኛቸውም፤ የሚዋጉህም፣ እንዳልነበሩ ይሆናሉ።
Explore ኢሳይያስ 41:12
6
ኢሳይያስ 41:14
አንተ ትል ያዕቆብ፣ ታናሽ እስራኤል ሆይ፤ ‘አትፍራ እኔ እረዳሃለሁ’ ” ይላል እግዚአብሔር፤ የሚቤዥህ የእስራኤል ቅዱስ ነው።
Explore ኢሳይያስ 41:14
7
ኢሳይያስ 41:8
“አንተ ግን፣ ባሪያዬ እስራኤል፣ የመረጥሁህ ያዕቆብ፣ የወዳጄ የአብርሃም ዘር ሆይ፤
Explore ኢሳይያስ 41:8
8
ኢሳይያስ 41:18
በተራቈቱ ኰረብቶች ላይ ወንዞችን፣ በሸለቆዎች ውስጥ ምንጮችን አፈልቃለሁ። ምድረ በዳውን የውሃ ኵሬ፣ የተጠማውን ምድር የውሃ ምንጭ አደርጋለሁ።
Explore ኢሳይያስ 41:18
9
ኢሳይያስ 41:17
“ድኾችና ችግረኞች ውሃ ይፈልጋሉ፤ ዳሩ ግን ምንም አያገኙም፤ ጕረሯቸው በውሃ ጥም ደርቋል። ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር እመልስላቸዋለሁ፤ እኔ የእስራኤል አምላክ አልተዋቸውም።
Explore ኢሳይያስ 41:17
10
ኢሳይያስ 41:4
ይህን የሠራና ያደረገ፣ ትውልድን ከጥንት የጠራ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር ከፊተኛው፣ ከኋለኛውም ጋራ፤ እኔው ነኝ።”
Explore ኢሳይያስ 41:4
11
ኢሳይያስ 41:19-20
በምድረ በዳ፣ ዝግባን፣ ግራርን፣ ባርሰነትንና ወይራን አበቅላለሁ፤ በበረሓ፣ ጥድን፣ አስታንና ሸውሸዌን በአንድነት እተክላለሁ። ስለዚህ ሰዎች ያያሉ፤ ያውቃሉ፤ የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገ፣ የእስራኤል ቅዱስ እንደ ፈጠረው፣ በአንድነት ይገነዘባሉ፤ ያስተውላሉም።
Explore ኢሳይያስ 41:19-20
Home
Bible
Plans
Videos