1
ኢሳይያስ 45:3
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
በስምህ የምጠራህ የእስራኤል አምላክ፣ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቅ ዘንድ፣ በተሰወረ ስፍራ የተከማቸውን ሀብት፣ በጨለማም ያለውን ንብረት እሰጥሃለሁ።
Compare
Explore ኢሳይያስ 45:3
2
ኢሳይያስ 45:2
‘በፊትህ እሄዳለሁ፤ ተራሮችን እደለድላለሁ፤ የናስ በሮችን እሰብራለሁ፤ የብረት መወርወሪያዎችንም እቈርጣለሁ።
Explore ኢሳይያስ 45:2
3
ኢሳይያስ 45:5-6
እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔ ሌላ ማንም የለም፤ ከእኔ በቀር አምላክ የለም። አንተ ባታውቀኝም እንኳ፣ እኔ አበረታሃለሁ። ይኸውም ሰዎች ከፀሓይ መውጫ፣ እስከ መጥለቂያው፣ ከእኔ በቀር ሌላ እንደሌለ እንዲያውቁ ነው፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔ ሌላ ማንም የለም።
Explore ኢሳይያስ 45:5-6
4
ኢሳይያስ 45:7
እኔ ብርሃንን ሠራሁ፤ ጨለማንም ፈጠርሁ፤ አበለጽጋለሁ፤ አደኸያለሁ፤ ይህን ሁሉ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’
Explore ኢሳይያስ 45:7
5
ኢሳይያስ 45:22
“እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፣ እኔ አምላክ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና፤ ትድኑ ዘንድ ወደ እኔ ተመለሱ።
Explore ኢሳይያስ 45:22
6
ኢሳይያስ 45:1
“ለቀባሁት፣ ቀኝ እጁን ለያዝሁት፣ ነገሥታትን ትጥቅ አስፈታ ዘንድ፣ ሕዝብን ሁሉ ላስገዛለት፣ ደጆች እንዳይዘጉ፣ በሮቹን በፊቱ ለምከፍትለት፣ ለቂሮስ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
Explore ኢሳይያስ 45:1
7
ኢሳይያስ 45:23
ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ምላስም ሁሉ በእኔ ይምላል፤ ብዬ በራሴ ምያለሁ፤ የማይታጠፍ ቃል፣ ከአፌ በጽድቅ ወጥቷል።
Explore ኢሳይያስ 45:23
8
ኢሳይያስ 45:4
ስለ ባሪያዬ ስለ ያዕቆብ፣ ስለ መረጥሁት ስለ እስራኤል፣ አንተ ባታውቀኝ እንኳ፣ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ የክብርም ስም ሰጥቼሃለሁ።
Explore ኢሳይያስ 45:4
Home
Bible
Plans
Videos