1
ያዕቆብ 3:17
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ከሰማይ የሆነችው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ በኋላም ሰላም ወዳድ፣ ታጋሽ፣ ዕሺ ባይ፣ ምሕረትና መልካም ፍሬ የሞላባት፣ አድልዎና ግብዝነት የሌለባት ናት።
Compare
Explore ያዕቆብ 3:17
2
ያዕቆብ 3:13
ከእናንተ መካከል ጥበበኛና አስተዋይ የሆነ ሰው ማን ነው? ሥራውን ከጥበብ በሆነ በመልካም አኗኗር ያሳይ።
Explore ያዕቆብ 3:13
3
ያዕቆብ 3:18
የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉ በሰላም ይዘራል።
Explore ያዕቆብ 3:18
4
ያዕቆብ 3:16
ቅናትና ራስ ወዳድነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ ይገኛሉ።
Explore ያዕቆብ 3:16
5
ያዕቆብ 3:9-10
በምላሳችን ጌታንና አብን እንባርካለን፤ በርሷም በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን። ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣል። ወንድሞቼ ሆይ፤ ይህ ሊሆን አይገባም።
Explore ያዕቆብ 3:9-10
6
ያዕቆብ 3:6
ምላስም እንደ እሳት ናት፤ በሰውነት ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ የክፋት ዓለም ናት፤ ሰውነትን ሁሉ ታረክሳለች፤ ደግሞም የፍጥረትን ሩጫ ታቃጥላለች፤ ራሷም በገሃነም ትቃጠላለች።
Explore ያዕቆብ 3:6
7
ያዕቆብ 3:8
ነገር ግን ምላስን መግራት የሚችል ማንም ሰው የለም፤ የሚገድል መርዝ የሞላባትና ዕረፍት የሌላት ክፉ ነገር ናት።
Explore ያዕቆብ 3:8
8
ያዕቆብ 3:1
ወንድሞቼ ሆይ፤ ከእናንተ ብዙዎች አስተማሪዎች አይሁኑ፤ ምክንያቱም እኛ አስተማሪዎች የሆንን የባሰ ፍርድ እንደምንቀበል ታውቃላችሁ።
Explore ያዕቆብ 3:1
Home
Bible
Plans
Videos