1
ሉቃስ 5:4
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ስምዖንን፣ “ወደ ጥልቁ ውሃ ፈቀቅ በልና ዓሣ ለመያዝ መረባችሁን ጣሉ” አለው።
Compare
Explore ሉቃስ 5:4
2
ሉቃስ 5:5-6
ስምዖንም መልሶ፣ “መምህር ሆይ፤ ሌሊቱን ሙሉ ስንደክም ዐድረን ምንም አልያዝንም፤ አንተ ካልህ ግን መረቦቹን እጥላለሁ” አለው። እንደዚያም ባደረጉ ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ፤ መረባቸውም ይበጣጠስ ጀመር።
Explore ሉቃስ 5:5-6
3
ሉቃስ 5:16
ኢየሱስ ግን ብዙ ጊዜ ወደ ገለልተኛ ስፍራ ወጥቶ ይጸልይ ነበር።
Explore ሉቃስ 5:16
4
ሉቃስ 5:32
እኔም ኀጢአተኞችን ወደ ንስሓ ልመልስ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም።”
Explore ሉቃስ 5:32
5
ሉቃስ 5:8
ስምዖን ጴጥሮስም ይህን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ጕልበት ላይ ወድቆ፣ “ጌታ ሆይ፤ እኔ ኀጢአተኛ ሰው ነኝና ከእኔ ተለይ” አለው።
Explore ሉቃስ 5:8
6
ሉቃስ 5:31
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች ሐኪም አያስፈልጋቸውም፤
Explore ሉቃስ 5:31
7
ሉቃስ 5:11
እነርሱም ጀልባዎቹን ወደ ምድር ካስጠጉ በኋላ፣ ሁሉን ትተው ተከተሉት።
Explore ሉቃስ 5:11
8
ሉቃስ 5:12-13
ኢየሱስ ከከተሞች በአንዱ በነበረበት ጊዜ፣ አንድ ለምጽ የወረሰው ሰው በዚያው ከተማ ነበር፤ ይህ ሰው ኢየሱስን ባየው ጊዜ በፊቱ ተደፋና፣ “ጌታ ሆይ፤ ብትፈቅድ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” ብሎ ለመነው። ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና፣ “እፈቅዳለሁ፤ ንጻ!” አለው፤ ወዲያውም ለምጹ ጠፋለት።
Explore ሉቃስ 5:12-13
9
ሉቃስ 5:15
ይሁን እንጂ ስለ እርሱ የሚወራው ወሬ ይበልጥ እየሰፋ ሄደ፤ እጅግ ብዙ ሰዎችም እርሱ የሚናገረውን ለመስማትና ካለባቸው ደዌ ለመፈወስ ይሰበሰቡ ነበር።
Explore ሉቃስ 5:15
Home
Bible
Plans
Videos