1
ማርቆስ 13:13
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ስለ ስሜ በሰው ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻው የሚጸና ግን ይድናል።
Compare
Explore ማርቆስ 13:13
2
ማርቆስ 13:33
ስለዚህ ጊዜው መቼ እንደሚሆን ስለማታውቁ ተጠንቀቁ! ትጉ! ጸልዩም!
Explore ማርቆስ 13:33
3
ማርቆስ 13:11
ይዘው ለፍርድ አሳልፈው በሚሰጧችሁ ጊዜ ሁሉ፣ በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ እንጂ ምን እንናገራለን በማለት አስቀድማችሁ አትጨነቁ፤ የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ እንጂ እናንተ አይደላችሁምና።
Explore ማርቆስ 13:11
4
ማርቆስ 13:31
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፣ ቃሌ ግን አያልፍም።
Explore ማርቆስ 13:31
5
ማርቆስ 13:32
“ነገር ግን ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ከአብ በቀር፣ የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ፣ ወልድም ቢሆን ማንም አያውቅም።
Explore ማርቆስ 13:32
6
ማርቆስ 13:7
ስለ ጦርነትና ጦርነትን የሚያናፍስ ወሬ በምትሰሙበት ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህማ መሆን አለበት፤ ፍጻሜው ግን ገና ነው።
Explore ማርቆስ 13:7
7
ማርቆስ 13:35-37
“እንግዲህ የቤቱ ባለቤት በምሽት ወይም በውድቅት፣ በዶሮ ጩኸት ወይም ጎሕ ሲቀድድ እንደሚመጣ አታውቁምና ተግታችሁ ጠብቁ፤ ድንገት ሲመጣ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ፤ ለእናንተ የምነግራችሁን ለሰው ሁሉ እናገራለሁ፤ ‘ተግታችሁ ጠብቁ!’ ”
Explore ማርቆስ 13:35-37
8
ማርቆስ 13:8
ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣል፤ በብዙ ቦታም የመሬት መንቀጥቀጥና ራብ ይሆናል፤ እነዚህ ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።
Explore ማርቆስ 13:8
9
ማርቆስ 13:10
አስቀድሞ ግን ወንጌል ለሕዝብ ሁሉ መሰበክ አለበት።
Explore ማርቆስ 13:10
10
ማርቆስ 13:6
ብዙዎች፣ ‘እኔ እርሱ ነኝ’ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።
Explore ማርቆስ 13:6
11
ማርቆስ 13:9
“ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ለአካባቢ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ በምኵራቦቻቸውም ይገርፏችኋል፤ ምስክር ትሆኑም ዘንድ በእኔ ምክንያት በገዦችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ።
Explore ማርቆስ 13:9
12
ማርቆስ 13:22
ሐሰተኛ ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነቢያት ተነሥተው፣ ምልክቶችንና ድንቆችን በማድረግ፣ ቢቻላቸው የተመረጡትን እንኳ ያስታሉ።
Explore ማርቆስ 13:22
13
ማርቆስ 13:24-25
“በዚያ ጊዜ፣ ከመከራው በኋላ ‘ፀሓይ ትጨልማለች፣ “ ‘ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፤ ከዋክብት ከሰማይ ይረግፋሉ፤ የሰማይ ኀይላትም ይናወጣሉ።’
Explore ማርቆስ 13:24-25
Home
Bible
Plans
Videos